ኔልሰን ማንዴላ 4 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት እንደነበራቸው ተዘገበ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ እውቁ የነጻነት ታጋይና በቅርቡ ከዚህ አለም የተለዩት ኔልሰን ማንዴላ ሀብቱን ያፈሩት በጆሀንስበርግ እና በኬፕ ታውን ከነበራቸው ቤት ሽያጭ እንዲሁም ከመጽሃፋቸው ከተገኘ ገቢ ነው።

ማንዴላ ከእርሳቸው ጋር ሲሰሩ ለነበሩት ለእያንዳንዳቸው 50 ሺ የደቡብ አፍሪካ ገንዘብ እንዲሁም እርሳቸው የተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች 100 ሺ ራንድ እንዲሰጣቸው ተናዘዋል። ለአራት የትምህርት ተቋማትም ለእያንዳንዳቸው 100 ሺ ራንድ እንዲሰጥ ወስነው አልፈዋል።

በቤተሰባቸው የሚተዳደረው የማንዴላ ፋውንዴሽን ደግሞ 1 ሚሊዮን 500 ሺ ራንድ ያገኛል። ፓርቲያቸውም እንዲሁ የተወሰነ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተገልጿል።