መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መቀሌ/ ወልድያ፣ ሰመራ ታጁራ የሚባለውን የባቡር ሃዲድ ፕሮጀክት ግንባታን ለመስራት ኢትዮጵያ 34 ቢሊዮን ብር የሚሆን ገንዘብ የመደበች ሲሆን ፣ መስመሩ አሰብን ለማለፍ ሲባል ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ብር ወይም 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣት ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። አገሪቱ ይህን ያክል ገንዘብ ለመክፈል የተገደደችው ባበሩ የሚያልፍበትን የተወሰነ የአሰብ አካባቢ ሳይነካ ለማሳለፍ በመገደዱዋ ነው። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃን በማዳረስ በኩል የሚሊኒየም ግቦችን ብታሳካም በንጽህና በኩል ወደ ሁዋላ መቅረቷን ዩኒሴፍ ገለጸ
መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ አመታዊውን የውሃ ቀን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ በሚሊኒየም የልማት ግቦች የተቀመጠውን ለ62 በመቶ የሚሆነው ህዝብ እስከሚቀጥለው አመት የንጹህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የማድረጉን እቅድ ተሳካለች። ይሁን እንጅ ይላል ድርጅቱ ህዝቡ ንጹህ መጸዳጃዎችን እንዲያገኝ በማድረግ በኩል አገሪቱ በእጅጉ ወደ ሁዋላ ቀርታለች። የሚሊኒየም የልማት ግቡ 51 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ንጹፍ መጸዳጃ እንዲያገኝ ...
Read More »በጅጅጋ አንድ የልዩ ሃይል አባል የዩኒቨርስቲ ተማሪ ገጭቶ በመግደል አመለጠ
መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነውና ስሙ ለጊዜው ያልታወቀው ወጣት የተገደለው ጧት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አስቀድሶ ሲመለስ ነው። የልዩ ሃይል ንብረት የሆነችውን መኪና የሚያሽከረክረው ሰው ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ በፍጥነት በማሽከርከር ተሰውሯል። ልዩ ሚሊሺያው ሆን ብሎ ይግጨው ወይም በድንገት በተፈጠረ አደጋ ባይታወቅም፣ አደጋውን ከፈጸመ በሁዋላ ምንም እንዳልተፈጠረ ማምለጡ የአካባቢውን ሰው አስቆጥቷል። ከሶስት ቀናት በፊትም እንዲሁም ...
Read More »በሻኪሶ ተነስቶ ለነበረበው ብጥብጥ ህዝቡ መንግስትን ተጠያቂ እያደረገ ነው
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአስር ቀናት በፊት በሻኪሶ ከተማ ጎሳን ማእከል አድርጎ በተማሪዎች መካከል በተነሳው ብጥብጥ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማው ባለስልጣናት በግጭቱ ዙሪያ ህዝቡን በማወያየት ላይ ሲሆኑ፣ የከተማው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ለሚነሳው ግጭት የአካባቢው አስተዳዳሪዎች እጅ አለበት ማለታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለኢሳት ገልጸዋል። ከተማዋ መረጋጋት ቢታይባትም፣ ተመሳሳይ ችግር ሊከሰት ...
Read More »ከሳውዲ አረቢያ የተመሰሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተመልሰው እየተሰደዱ ነው
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በአስከፊ ሁኔታ ከሳውድ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ዜጎች ተመልሰው እየተሰደዱ እንደሆን መረጃዎች አመለከቱ። ኢትዮጵያውያውያኑ ስደትን እንደ አማራጭ የሚጠቀሙበት በአገራቸው ለመስራት ሁኔታዎች እንዳልተመቻቹላቸው በመግልጽ ነው። በተለይ ወደ ትግራይና አማራ ክልሎች እንዲሄዱ የተደረጉ ስደተኞች በሁመራ በኩል ወደ ሱዳን በብዛት እየጎረፉ መሆኑን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ። አንዳንድ ወጣቶች ከሳውድ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለቀን ...
Read More »ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ አሁንም በእስር ላይ ነው
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ችግር ለጀርመን ሬዲዮ በመዘገብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በውል ባልታወቀ ምክንያት ሳምንታትን በእስር ለማሳለፍ መገደዱ ታውቋል። ነብዩ በተለይም ከወራት በፊት ከሳውድ አረቢያ በሚፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ሚዛናዊ ዘገባዎችነ በማቅረብ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ስሜት ለመግዛት ቻለብዙዎች በድፍረቱ የሚያደንቁት ጋዜጠኛ ነው። የነብዩን ቤተሰቦችም ሆነ የጀርመን ድምጽ የአማራኛው ክፍል ሃላፊን ለማግኘት በተደጋጋሚ ...
Read More »በኬንያ ወንዶች ተጨማሪ ሚስቶች እንዲኖራቸው የሚያዘው ህግ በፓርላማው ጸደቀ
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአመታት ሲያወዛግብ የነበረው ወንዶች ባለ ብዙ ሚስቶች የሚያደርጋቸው ህግ ትናንት በፓርላማ አባላት ሲጸድቅ፣ 30 የሚሆኑ ሴት የፓርላማ አባላት ክርክሩን ረግጠው ወጥተዋል። አንድ የፓርላማ አባል ” ይህ አፍሪካ ነው፣ በአፍሪካ ባህል የአፍሪካ ሴት ስታገባ ፣ ባለቤትህ ሌሎች በመምጣት ላይ ያሉ ሁለት ወይም ሶስት ሴቶች እንዳሉ ታውቃለች፣ ምንም አዲስ ነገር የለውም” ብለዋል። አብዛኞቹ ...
Read More »በሀረር በህዝቡና በአስተዳደሩ መካከል ያለው አለመተማመን መስፋት ወደ ብሄር ግጭት እንዳያመራ ተስግቷል
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የንግድ ቤቶች መቃጠላቸውን ተከትሎ፣ በህዝቡና ክልሉን በሚመራው የሃረሪ ሊግ መካከል የተፈጠረው ከፍተት እየሰፋ መሄድ የብሄር ግጭት ሊያስነሳ ይችላል በማለት ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት ክልሉን የሚያስተዳድረው የሃረሪ ሊግ ” መጤዎች ከከተማችን ውጡ” የሚሉ ቅስቀሳዎችን ከጀርባ ሆኖ በማሰራጨትና የንግድ ቤቶችን በማቃጠል ለዘመናት ...
Read More »አንድነት ፓርቲ የእሪታ ቀን በሚል በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው የተቃውሞ ሰልፉን የሚጠራው በዋና ከተማዋ የሚታዩትን የማህበራዊ አገልግሎቶችን ችግሮች ለመቃወም ነው። “በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት መፍረሳቸው፣ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱ ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉን፣ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ መዳከሙን፣ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት ...
Read More »የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሽቆልቆል አሳሳቢ ሆኗል
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስአበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በታሪኩ አይቶ የማያውቀው የአገልግሎት አሰጣጥ መጨናነቅ እንዳጋጠመውና በዚህም ምክንያት ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንጻር የአገልግሎት ጥራቱ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱን አንድ ከድርጅቱ የተገኘ ጥናታዊ ጽሁፍ አመለከተ፡፡ አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ለሃያ ዓመታት በዓመት 6 ሚሊየን መንገደኞችን በብቃት ሊያስተናግድ ይችላል ተብሎ የተገነባ ቢሆንም በአስረኛ ዓመቱ የመንገደኞች ...
Read More »