.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢህአዴግ የ2007 ምርጫ ማሸነፊያ ስትራቴጂዎችን አወጣ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢህአዴግ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት የተላከው የ2007 ዓም ምርጫ ማስፈጸሚያ እቅድ እንደሚያሳየው ለአርሶ አደሩ የማዳበሪያ እዳ እፎይታ በ2006/2007 የመኸር ምርት ዘመን የሚሰጥ ሲሆን፣ ለከተማ ነዋሪዎች ደግሞ  በ20 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውሉ ቦታዎችን ይሰጣል። 20 ሺ ብር የቅድመ ክፍያ ገንዘብ ለማቅረብ ለማይችሉት የከተማ ነዋሪዎች  የምርጫ ቅስቀሳ በሚካሄድባቸው ወራት ከባንክ በብድር ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ” ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን፡” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈጽሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶች የሠብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ለመንግስት አካላት በተደጋጋሚ ጊዜያት ጥሪ ቢያቀርብም የሚሰማው ማጣቱን ገልጿል። በአገሪቱ የሚታዩ ችግሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ለማድረግ  እሁድ ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት የሚቆይ ...

Read More »

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ከስልጣን የምነሳ ከሆነ ክልሉ የራሱን እድል በራሱ ይወስናል አሉ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ምክር ቤት በሶማሊ ክልል የሚፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት በክልሉ ያሉትን ባለስልጣኖች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የኢህአዴግን ባለስልጣኖችን በአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የሚያስጠይቅ መሆኑን ድምዳሜ ላይ የደረሰው ኢህአዴግ፣  ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ኡመርን ለማውረድ እንቅስቃሴ መጀመሩ  ፕሬዚዳንቱ ይህንን ንግግር እንዲናገሩ እንዳደረጋቸው ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አብዲ   የእርሳቸው ታማኝ ደጋፊ የሆኑ በውጭ አገራት የሚኖሩ የክልሉን ...

Read More »

በምርጥ ዘር ጥራት መጓደል ምክንያት ከፍተኛ ሃብት እየባከነ ነው ተባለ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት እንዳስታወቀው ባለፉት አመታት ለአርሶደሩ የቀረቡ የምርጥ ዘር ማሻሻያ ዝርያዎች የመብቀልና ምርት የማፍራት ችግር ገጥሞአቸዋል። በዚህም የተነሳ በየአመቱ ከ150 ሺ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለብክነት እየተዳረገ ነው። በዚህ አመት ብቻ 25 ሺ 97 ኩንታል ምርት ዘር ባክኖ መቅረቱን ድርጅቱ አስታውቋል። በየዓመቱ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ዝርያዎች ያለአግባብ እየቀረቡ ከ2ዐሽ ሄከታር በላይ ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው ጦርነት እንደገና አገረሸ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ውጤት አለማምጣቱን የሚያሳይ ጦርነት በነዳጅ ሃብቷ በበለጸገቸው የቤንቲዩ ግዛት መጀመሩን ዘገባዎች የመለክታሉ። በሪክ ማቻር የሚመራው የአማጽያኑ ሃይል ቤንቲዩን መቆጣጠሩን ሲያስታውቅ፣ የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር መንግስት ደግሞ ዜናውን አስተባብሎአል። እንደገና ባገረሸው ጦርነት አመጽያኑ ድል እንዳገኙና በመሸሽ ላይ ያሉትን የመንግስት ወታደሮች እየተከታተሉ በመውጋት ላይ መሆናቸውን እየገለጹ ነው። የተባበሩት ...

Read More »

በጋምቤላ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ተሰማ

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ተባባሪ ዘጋቢ እንደገለጸው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በክልሉ ያለው ውጥረት ጨምሮአል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እየሰራ ባለው የዋንኬ መንገድ አካባቢ ከደቡብ ሱዳን የተፈናቀሉ ስደተኞች በሰፈሩ አካባቢ አንድ ሾፌር እና አንድ የልዩ ፖሊስ አባል መገደላቸውን ተከትሎ አካባቢው በፌደራል ፖሊስ መወረሩ ታውቋል፡፡ የግድያው መንስኤ በውል ባይታወቅም የክልሉ ፖሊስ ከኤርትራ ሰርገው የገቡ አሸባሪዎች የፈጸሙት ...

Read More »

በአፋር በተነሳ የጎሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሃዊያ እየተባሉ በሚጠሩ የሶማሌ ጎሳዎችና በአፋሮች መካከል በተነሳ የእርስ በርስ ግጭት 6 ሰዎች መሞታቸውን በርካቶች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የጠቡ መነሻ ከግጦሽ መሬት ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ከትናንት ጀምሮ የቆመ ቢሆን ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለትንዳሆ የሸንኮራ ምርት ማስፋፊያ በሚል ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተነስተው ...

Read More »

በጉጅና በቦረናዎች መካከል ግጭት ማገርሸቱ ተሰማ

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግርማየ ፣ ቦቢላ ፣ መደር እና ቦኪዳዋ ቀበሌዎች ሚያዚያ 4 ቀን 2006 ዓም በተነሳ ግጭት  ከ5 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ከአካካቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ውጥረቱ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው። በጉጂ የወረዳ ሹማምንት እርስ በርስ ግምገማ ላይ መቀመጣቸውም ተሰምቷል። የኦሮምያ ክልል የጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዳ ሮቤ ከስልጣን መነሳታቸው ችግሩን ያበርደዋል ተብሎ ቢጠበቅም ...

Read More »

በናይጀሪያ-አቡጃ በሚገኝ አንድ አውቶቡስ ማረፊያ በደረሱ ሁለት የቦንብ ፍንዳታዎች ከ 40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ሰገበ።

ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቢቢሲዋ ወኪል  ሀሩና ታንጋሳ ከአቡጃ እንዳጠናቀረችው ሪፖርት ፤ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት የትራፊክ መጨናነቅ በነበረበት  ሰዓት ሲሆን፣ አብሳኞቹ ሟቾች እና ተጎጂዎች ወደ ሥራ ለመግባት አውቶቡስ እና ታክሲ ለመሳፈር ከቤታቸው ማልደው የሚገሰግሱ ነበሩ። የዓይን ምስክሮች የበርካታ ሟቾች አስከሬን ጎዳናውን ሞልቶት ማየታቸውን ገልጸዋል።  ጥቃቱን የፈፀመው “ቦኮ ሀራም” የተሰኘው  የእስላሚስት ሚሊሺያ ቡድን ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ባዳምሲ ኒያንያ  የተባሉ የ ...

Read More »

የአገውና የጃን አሞራ አካባቢ አርሶ አደሮች በረሃብ ምክንያት ወደ ትግራይ ከተሞች እየተሰደዱ መሆኑን አንድ ታዋቂ ፖለቲከኛ ተናገሩ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የህወሃት አመራርና ነባር ታጋይ በአሁኑ ጊዜ በአረና ፓርቲ ውስጥ በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የሚገኙት ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አቶ አስገደ ገብረስላሴ ለኢሳት እንደገለጹት በሰሜን ወሎ ዞን በሰቆጣ፣ ላሌበላ፣ ዋግና ሌሎችም አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች በአካባቢያቸው በተነሳው ከፍተኛ ረሃብ የተነሳ  ቀያቸውን ጥለው ወደ መቀሌ፣ ሽሬ፣ አክሱምና ሁመራ መሰደዳቸውን ገልጸዋል። “አርሶደሮችን ሲያነጋግሩ ከፍተኛ ረሃብ ...

Read More »