ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሶሲየትድ ፕሬስን በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው ኢባሎ ሳይዱ ዶሳ የተባለው ተከሳሽ የ10 ኣመቷን ታዳጊ ወጣት እንደደፈረ ያመነ ሲሆን፤”ድርጊቱን የፈፀምኩት ሰይጣን አሣስቶኝ ነው ብሏል። ዾሳ ሁለት ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም፤ሁለቱም ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር በተያያዘ ህመም መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። የሰሜን ናይጀሪያ እስላማዊ ፍርድ ቤት በበርካታ ተከሳሾች ላይ በድንጋይ ተወግረው እንዲሞቱ በተለያዩ ጊዜያት ፍርድ ያሳለፈ ቢሆንም፤ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሰመራ ከፍተኛ ተቃውሞ ተካሄደ
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል መስተዳደር መቀመጫ ሰመራ ዛሬ በተካሄደው የተማሪዎች ተቃውሞ የልዩ ሃይል አባላት በተማሪዎች ላይ ድበደባ ፈጽመዋል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ተደብድበው ሆስፒታል ሲገቡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደግሞ ታስረዋል። የኮሌጅና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጧት ላይ መኪኖችን አግደው ከዋሉ በሁዋላ ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ እገታውን ቆሟል። ተማሪዎች ከሰአት በሁዋላ ወደ ክልሉ ጽህፈት ቤት በመሄድ ...
Read More »የፌዴራልዋናኦዲተር በትምህርት ተቋማት፣ በውጭጉዳይና በመከላከያ ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት መኖሩን አመለከተ
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመ/ቤቱዋናኦዲተርየሆኑትአቶገመቹዱቢሶየ2005 ዓ.ምየኦዲትሪፖርታቸውን ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት በ132 የመንግሥትመ/ቤቶችላይበተካሄደውኦዲትከፋይናንስሥርዓት፣ደንብናመመሪያጋር የሚጋጩበርካታግድፈቶችመታየታቸውንአመልክተዋል፡፡ የትምህርት ተቋማትና መከላከያ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት ከተገኘባቸው መስሪያ ቤቶች መካከል በቀዳሚነት ተጠቅሰዋል። ዋናኦዲተሩባቀረቡትና 54 ያህል ገጾችንበያዘውበዚሁሪፖርታቸውሂሳብበወቅቱያለማወራረድችግር፣የተሟላየወጪማስረጃሳይቀርብበወጪ ተመዝግቦመገኘት፣ደንብናመመሪያሳይከተሉግዥዎችንመፈጸም፣የጥሬገንዘብጉድለቶች፣በብልጫየተከፈሉ ሂሳቦች፣ቀረጥተከፍሎባቸውገቢለመሆናቸውማስረጃያልቀረበባቸውሂሳቦች፣ከበጀትበላይወጪማውጣትና የመሳሰሉየሂሳብአሠራርግድፈቶችበበርካታመ/ቤቶች ታይተዋል፡፡ የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ አያያዝና አጠባበቅ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በ5 መ/ቤቶች ብር 1 ሚሊዮን ,272,ሺ 93ብር ከ33 ሳንቲም የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ሲገኝ፣ ጉድለት የተገኘባቸው ዩኒቨርስቲዎች ተብለው የተጠቀሱት ደግሞ ጂማ፣ ሰመራ፣ ወሎ፣ ባህርዳርና ጅጅጋ ናቸው፡ በጉድለት የታየው የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ ተገቢው እርምጃ ተወስዶ እንዲተካ ለየመ/ቤቶቹ በተላከው የስራ አመራር ሪፖርት ማሳሰባቸውን ዋና ኦዲተሩ አመልክተዋል። በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት የተደረገውና በቆጠራ የተገኘው ጥሬ ገንዘብ መካከል በ3 መ/ቤቶች ማለትም ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን አጠናክሮ ቀጥሎአል
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ‹‹የተነጠቁመብቶቻችንእናስመልስ›› በሚልመሪቃልታላቅናደማቅሰላማዊሰልፍበጃንሜዳ የሚያካሂድ ሲሆን፣ የፓርቲው ወጣት አባላት ወደ ተለያዩ የአዲስ አበባ ቦታዎች እየዞሩ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው። ፓርቲው ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ ገልጿል። ፓርቲው መምህራንና ነጋዴዎች በሰልፉ ላይ ...
Read More »የአፍረካ ህብረት የመርማሪዎች ቡድን ወደ ደቡብ ሱዳን መሄዱ ታወቀ::
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ህብረት የተሰየመ በቀድሞ የናይጄረያ ፕሬዘዳንት ኦለሰንጎ ኦበሳጆ የሚመራ የልኡካን ቡድን ወደደቡብ ሱዳን ያመራ ሲሆን ስራውም በደቡብ ሱዳን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት መመርመርና ለአፍሪካ ህብረት አስፈላጊውን የመፍተሄ ሃሳብ ማቅረብ ይሆናል:: የልዑካን ቡድኑ ፕረዜዳንት ሳልቫኪርንና የተቃዋሚውን መሪ ሬክ ማቻርን እንደሚያነጋግር ሲታወቅ በጦርነቱም ስቃይ የደረሰባቸውን ሰዎች እንደሚያነጋግር ታውቋል:: ይህ በዚህ እያለ በዛሬው እለት ፕሬዝዳንት ሳልቫኬርና በተቃዋሚው መሪ በሬክ ማቻር መካከል ይካሄዳል የተባለው ...
Read More »በሃረር ልጃቸው በእስር ቤት ውስጥ የተገደለባቸው አባት ፍትህ እንደላገኙ ገለጹ
ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው መጋቢት ወር በሃረር የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ እቃ ሰርቀሃል በሚል የ21 ዓመቱ ወጣት ዳንኤል ጎሳ በእስር ቤት ውስጥ ለብቻው እንዲታሰር ተደርጎ ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞበት መሞቱን ኢሳት የእስር ቤት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ከዘገበ በሁዋላ ወላጅ አባቱ አቶ ጎሳ አበበ ፣ የልጃቸውን አሟሟት ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን እንዳልተሳካለቸው ገልጸዋል። አቶ ጎሳ ...
Read More »ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን የመንግስት ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታወቀ
ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌድራልዋናኦዲተርለተወካዮች ምክር ቤት የ2005 በጀት አመት ሪፖርትን ባቀረረበት ወቅት በ77 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ 8 መቶ 87 ሚሊዮን 45 ሺ 264 ብር ከ60 ሳንቲምያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን ይፋ አድርጓል። የገንዘብ አያያዝን በተመለከተ በአምስትመስሪያቤቶች ውስጥ በተደረገ የናሙና ጥናት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ጉድለት መገኘቱም ተገልጿል። አምና መከላከያን ጨምሮ በተደረገው ምርመራ ከ3 ቢሊዮን ብር ...
Read More »በደቡብ ምእራብ ሃገረ ስብከት ከ35 በላይ ካህናት ተባረሩ
ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት አዲሱን ጳጳስ አቡነ ማቲያስን እንዲሁም የሀገረ ሰብከቱን ዋና አስተዳዳሪ አቡነ ሳዊሮስን አትደግፉም የተባሉ ከ35 በላይ ካህናት ከሃላፊነት የተነሱ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም የሆሳእና በአል እለት በወሊሶ ረብሻ ተነስቶ ነበር። ምእመናኑ የተባረሩት የሃይማኖት አባቶች እንዲመለሱ እንዲሁም አዳዲስ ሹሞች እንዲወርዱ ጠይቀዋል። የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ለማረጋጋት ሞክሯል። አቡነ ሳዊሮስ ለጸሎት ...
Read More »የሼህ አላሙዲን አጎት ባለቤት በድጋሜ ታስረው ተፈቱ
ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሼህ ሙሃመድ አላሙዲን አጎት ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ኬርያ አህመድ አደም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኘ ግዜ ለሶስት ቀናት ታስረው ተፈትተዋል። አቶ መርዱፍ የሳውዲይ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ የሼክ አላሙዲን ንብረት የሆነው የማምኮም ፋብረካ ስራስኪያጅ ናቸው:: ወ/ሮ ኬርያ አህመድ አደም ኬር ፊትነስ ሴንተር የሚባል የንግድ ድርጅት አዲስ አበባ ቺቺንያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢና በወሎ ሰፈር ሲኖራቸው በካዛንችስ አካባቢ በሚገኘው በኢሲኤ ሁለት ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን በበንቲው ግዛት የተካሄደውን የዘር ማጽዳት ዘመቻን በጥብቅ አወገዘ
ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ እርዳታ ተጠሪ ቶቢ ላንዘር: በደቡብ ሱዳን የተካሄደው ዘግናኝ ግድያ በጣም እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል:: ቶቢይ ላንዘር አንዳንድ ግለሰቦች የራዲዮ ጣብያን በመጠቀም ላደረጉት የጥላቻ ቅስቀሳ ተጠያቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ችግሩ በዚህ ከቀጠለ በመጪው የፈረንጆች አዲስ አመት ከዚህ የበለጠ አሰቃቂ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል:: ይህ በዚህ እያለ የዑጋንዳ መከላከያ ሃይል ቦር የሚገኘውን ...
Read More »