ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን አጠናክሮ ቀጥሎአል

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ‹‹የተነጠቁመብቶቻችንእናስመልስ›› በሚልመሪቃልታላቅናደማቅሰላማዊሰልፍበጃንሜዳ የሚያካሂድ ሲሆን፣ የፓርቲው ወጣት አባላት ወደ ተለያዩ የአዲስ አበባ ቦታዎች እየዞሩ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው።

ፓርቲው ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ ገልጿል።

ፓርቲው መምህራንና ነጋዴዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ፓርቲውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።