በደቡብ ምእራብ ሃገረ ስብከት ከ35 በላይ ካህናት ተባረሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት አዲሱን ጳጳስ አቡነ ማቲያስን እንዲሁም የሀገረ ሰብከቱን ዋና አስተዳዳሪ አቡነ ሳዊሮስን አትደግፉም የተባሉ ከ35 በላይ ካህናት ከሃላፊነት የተነሱ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም የሆሳእና በአል እለት በወሊሶ ረብሻ ተነስቶ ነበር።

ምእመናኑ የተባረሩት የሃይማኖት አባቶች እንዲመለሱ እንዲሁም አዳዲስ ሹሞች እንዲወርዱ ጠይቀዋል። የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ለማረጋጋት ሞክሯል።

አቡነ ሳዊሮስ ለጸሎት እየሩሳሌም የሚገኙ በመሆናቸው ስለተፈጠረው ችግር ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።