የሼህ አላሙዲን አጎት ባለቤት በድጋሜ ታስረው ተፈቱ  

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሼህ ሙሃመድ አላሙዲን አጎት ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ኬርያ  አህመድ  አደም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኘ ግዜ ለሶስት ቀናት ታስረው ተፈትተዋል።

አቶ መርዱፍ የሳውዲይ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ  የሼክ አላሙዲን  ንብረት የሆነው  የማምኮም ፋብረካ ስራስኪያጅ ናቸው:: ወ/ሮ ኬርያ አህመድ አደም  ኬር ፊትነስ ሴንተር የሚባል የንግድ ድርጅት አዲስ አበባ  ቺቺንያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢና በወሎ ሰፈር ሲኖራቸው በካዛንችስ አካባቢ በሚገኘው በኢሲኤ  ሁለት የሪል ስቴት  ድርጅቶች አላቸው::  ባለሃብቷ ከሙስና ጋር በተያያዘ  በተደጋጋሚ ቢታሰሩም፣ ስለተከሰሱበት የሙስና አይነት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት አልተቻለም።

ግለሰቧ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የታሰሩ ሲሆን ከመጀመሪያው እስር እንዴት እንደወጡ ሳይታወቅ በድጋሜ ታስረው ከሶስት ቀናት በሁዋላ ተለቀዋል።