የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን በበንቲው ግዛት የተካሄደውን የዘር ማጽዳት ዘመቻን በጥብቅ አወገዘ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ እርዳታ ተጠሪ ቶቢ ላንዘር: በደቡብ ሱዳን የተካሄደው ዘግናኝ ግድያ በጣም እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል::

ቶቢይ ላንዘር  አንዳንድ ግለሰቦች የራዲዮ ጣብያን በመጠቀም ላደረጉት የጥላቻ ቅስቀሳ ተጠያቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ችግሩ በዚህ  ከቀጠለ በመጪው የፈረንጆች አዲስ  አመት ከዚህ የበለጠ አሰቃቂ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ስጋታቸውን  ገልጸዋል::

ይህ በዚህ እያለ የዑጋንዳ መከላከያ ሃይል ቦር የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት ከአምስት ሺህ በላይ የሚገኙትን ስደተኞች ከሚሊሻዎች ጥቃት  ለመከላከል ከመንግስታቱ የሰላም አስከባረ ሃይል መረከቡን አስታውቋል:።