በሰሜን ናይጄሪያ የሚገኝ እስላማዊ ፍርድ ቤት የ10 ዓመቷን ታዳጊ ወጣት በመድፈር በኤች አይ ቪ/ኤድስ ቫይረስ እንድትያዝ ያደረጋትን የ 63 ዓመት ጎልማሳ በድንጋይ ተወግሮ እንዲገደል ውሳኔ አሳለፈ።

ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሶሲየትድ ፕሬስን በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው ኢባሎ ሳይዱ ዶሳ የተባለው ተከሳሽ የ10 ኣመቷን ታዳጊ ወጣት እንደደፈረ ያመነ ሲሆን፤”ድርጊቱን የፈፀምኩት ሰይጣን አሣስቶኝ ነው ብሏል።

ዾሳ ሁለት ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም፤ሁለቱም ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር በተያያዘ ህመም  መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

የሰሜን ናይጀሪያ እስላማዊ ፍርድ ቤት በበርካታ ተከሳሾች ላይ በድንጋይ ተወግረው እንዲሞቱ በተለያዩ ጊዜያት ፍርድ ያሳለፈ ቢሆንም፤ እስካሁን በአንዳቸውም ላይ ፍርዱ ተግባራዊ አልሆነም።

የካኖ ግዛት  የፍትህ ኮሚሽነር ማሊኪ ኩሊቫ ለቢቢሲ እንደገለፁት የሞት ፍርደኛው ዶሳ ለፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ የመጠየቅ መብት አለው።

ይሁንና የይግባኝ ሂደቱ ብዙ ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል ነው የተመለከተው።