.የኢሳት አማርኛ ዜና

አንድ በጥብቅና ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩ ሰው ለተቃዋሚ አባል ጥብቅና በመቆማቸው እየተሳደዱ ነው

ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ሊበን ታየ የተባሉ አርሶ አደር የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ በወረዳው ፖሊሶች ተደብድበውና ጭንቅላታቸው ላይ በሽጉጥ ተመትተው በሞትና በህይወት መካከል ወድቀው መገኘታቸውን ተከትሎ ፣ አርሶ አደሩ ከህመማቸው ሲያገግሙ ለወረዳው ጠበቃ ይገርማል መልካሙ አሰፋ ጉዳያቸውን ማመልከታቸውን ተከትሎ ችግሩ መጀመሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሙጩ ዳኔ፣ አቶ ...

Read More »

በሁለት ዙር የሰለጠኑ 235 የድረ ገፅ መረጃ ማዛባት የሚችሉ ፕሮፓጋንዲስቶች በስራ ላይ መሆናቸው ታወቀ፡፡

ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በመላ ሐገሪቱ በኢንተርኔት ድረ ገፅ መንግስት እየደረሰበት ያለውን ትችት ለመቀነስና ፤ የተደበቁ መረጃዎች ተጋላጭነታቸውን ለመቆጣጠር በማሰብ የሰለጠኑ ወጣቶች ስራ መጀመራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡ ኢህአዴግ በአዳማ ናዝሬት በሁለት ዙር ያሰለጠናቸው 235 ብሎገሮች በፊስ ቡክና በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች፣ተቃዋሚ የሚመስሉ ስያሜዎችን በማውጣት ህዝብ የማደናገር፤ መንግስትን በሚቃወሙ መረጃዎች ላይ ምላሽ የመስጠት ፤ መንግስትን ...

Read More »

መንግስት አንድ የአልሸባብ ልኡክን መያዙን አስታወቀ

ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊፈጽም ይችላል በሚል ምእራባዊያን አገራት ማስጠንቀቂያ ማውጣታቸውን ተከትሎ፣ ምንም ይፋዊ መግለጫ ሳይሰጥ የቆየው መንግስት፣ ዘግይቶ አንድ የአልሸባብ የጥቃት አቀነባባሪ የሆነ ግለሰብ መያዙን አስታውቋል። መንግስት የግለሰቡን ማንነት ይፋ አላዳረገም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ መንግስት 70 የሚደርሱ የአልሸባብ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። ከሶማሊያ የሚወጡ ዘገባዎች በበኩላቸው በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል በተደረገው ከፍተኛ ...

Read More »

ኢትዮጴያዊት የቤት ሰራተኛ በባርነት  ለ 15 ዐመታት መገዛቱዋ ከፍተኛ ትኩረት ከመሳቡም በላይ ጥብቅ የሆነው የቤት ሰራተኞች ህግ መሻሻል እንዳለበት ያመላከተ እንደሆነ ተገለጸ።

ግንቦት ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳንዲፕ ሲን ግሪዋል እንደዘገበው፤ ኢትዮጰያዊቱ ሰብለ አበበ ተሰማ  በባህሬይን በቤት ሰራተኝነት  ለ 15 ዓመታት ብታገለግልም፤  የተከፈላት ደመወዝ ከ 18 ወራት ያነሰ መሆኑ  ትናንት የስደተኛ ሰራተኞች ተካላካይ ማህበር  በአድሊያ  በሰጠው ጋሴጣዊ መግለጫ ተወስቱዋል። በምህጻረ-ቃል “ ኤም.ደብሊው፣ ፒ ኤስ”  የተሰኘው ይህ የስደተኞች ተንከባካቢ ድርጅት እንዳለው፤ ሰብለ በመጀመሪያ ባህሬን የገባችው  እ.አ.አ በ 1999 ዓመተ ምህረት የ ...

Read More »

ከ30 በላይ የኢትዮጵያ ታጣቂ ሚሊሺያዎች በአልሸባብ መገደላቸውን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደህንነት ክፍል የተገኘ መረጃ አመለከተ

ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰራተኞቹ በላከው ማስጠንቀቂያ ላይ በሶማሊ ክልል ባሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ 33 የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች በአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጾ ሰራተኞቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄና ጥበቃ እንዲያደርጉ መክሯል። የኢትዮጵያ የብሄራዊ የደህንነት ጥበቃ መስሪያ ቤት አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊፈጽም ይችላል የሚለውን ስጋት እንደሚጋራ የገለጸው ድርጅቱ ፣ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች ቦታዎች በጥንቃቄ እንዲጠበቁ አዟል። ...

Read More »

በምዕራብ ኦሮምያ ዞን የፌደራል ፖሊሶች ከህዝብ ጋር መጋጨታቸው ተሰማ

ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ አቡና  በሚባል ወረዳ የፌደራል ፖሊሶች ነዋሪዎችን መደብደባቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁትንም ይዘው ማሰራቸውን የአካባቢዎች ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የግጭቱ መነሻ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ አስተባብሮአል የተባለው መንጌ ጉደታ እንዲፈታ ህዝቡ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። ወጣቱ እግሩ በድብደባ ብዛት መሰበሩን የሚገልጹት አካባቢው ነዋሪዎች፣ ነዋሪዎች ወጣቱ ካልተለቀቀ ፖሊስ ጣቢያውን እናቃጥላለን ...

Read More »

ግብጽ 77 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መለሰች።

ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “መና” የተባለው የግብጽ ዜና አገልግሎት እና “አል አህራምስ” የተባለው የአረብኛ ድረ ገጽ እንደገዘቡት፤ ወደ ሀገራቸው “ዲፖርት” የተደረጉት ኢትዮጰያውያን  በህገ ወጥ መንገድ ወደ ግብጽ በመግባት ወደ እስራኤል ለመሻገር ሲሞክሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው። ተመላሾቹ ኢትዮጰያውያን ግብጽ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት ደቡባዊ ድንበር በኩል አድርገው ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ አስዋን ሲገቡ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን ...

Read More »

ብርሃንና ሰላም የጋዜጦችን ይዘት ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ፊርማ አሳታሚዎች እንዲፈርሙ አስገደደ

ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተመሰረተ 92ኛ ዓመቱን የደፈነው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የጋዜጦችን ይዘት ለመቆጣጠር የሚያስችለውን የስምምነት ውል አሳታሚዎች እንዲፈርሙለት አስገዳጅ ሰርኩላር አሰራጭቷል፡ ማተሚያቤቱበማሽንእርጅናምክንያትጋዜጦችንበቀናቸውማተምየማይችልበትደረጃላይየሚገኝሲሆንበዚህምምክንያትጋዜጦችከመውጫቀናቸውከአንድእስከሶስትቀናትዘግይተውበመውጣትላይመሆናቸውንለጉዳዩቅርበትያላቸውወገኖችይገልጻሉ፡፡በዚህምምክንያትአቅምእያዳበሩየመጡጋዜጦችሳይቀርለኪሳራእየተዳረጉየመጡበትሁኔታእየተፈጠረሲሆንአቅምየሌላቸውከገበያለመውጣትእየተገደዱነው፡፡ ማተሚያቤቱባለፈውዓመትየህትመትሥራንበተመለከተየጋራየስምምነትውልይኑረንበሚልያሰራጨውረቂቅገዳቢሕግየጋዜጦችንይዘትአስቀድሞእንዲቆጣጠርዕድልየሚሰጠውናየማይስማማውንጋዜጦችአላትምምለማለትየሚያስችለውበመሆኑበአሳታሚዎችበኩልበተነሳተቃውሞሳይፈረምመቆየቱየሚታወስነው፡፡ በአሁኑወቅትይህንኑ ተቃውሞየገጠመውንውልአሳታሚዎችእንዲፈርሙለት፣ይህካልሆነጋዜጦችንማተምእንደሚያቆምበመግለጽሰሞኑንያሰራጨውደብዳቤበቅርቡበተመሰረተውየአሳታሚዎችማህበርበኩልተቃውሞገጥሞታል፡፡ አሳታሚዎቹከዚህይልቅ ማተሚያቤቱየመንግስትጋዜጦችንካተመበሃላበማሽንተበላሽቶአልስምየግልጋዜጦችበቀናቸውእንዳይወጡየሚያደርገውሃላፊነትየጎደለውአድሎአዊ  አሰራርለማረምናአዳዲስማሽኖችንለማስገባትቅድሚያሰጥቶእንዲሠራበመጠየቅላይናቸው፡፡በሁለቱወገኖችበኩልያለውአለመግባባትይህዜናእስከተጠናቀረበትቀንድረስእልባትአላገኘም፡፡ 90 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖሩባት ኢትዮጵያጋዜጦችን በተሻለ ሁኔታ ለማተም የሚያስችል ብቸኛው ማተሚያ ቤት ብርሃንና ሰላም ነው።

Read More »

የአንበጣ መንጋ በሰሜን ጎንደር አካባቢ መታየቱን ነዋሪዎች  ገለጹ

ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያን እየጎበኘ የሚመስለው የአንበጣ መንጋ በደብረ ብርሃን አካባቢ ከታየ በሁዋላ ትናንት እና ዛሬ ሰሜን ጎንደር አካባቢ ባሉ ወረዳዎች መታየቱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ወቅቱ የሰብል አዝመራ የሌለበት በመሆኑ አንበጣው ጉዳት አለማድረሱን ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው በአዲስ አበባም የተወሰኑ አካባቢዎች ታይቶ እንደነበር ይታወሳል።

Read More »

በአዲስ አበባከ ሚገኙነዋሪዎች መካከል ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ከ70 ሺ በላይ ዜጎች የጎልማሶች ትምህርት ቢያስፈልጋቸውም እያገኙ ያሉት 49ሺ ያህሉ  መሆናቸውንከክልሉትምህርትቢሮየተገኘመረጃአመለከተ፡፡

ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጼኃ/ስላሴ ዘመን የፊደል ሰራዊት፣ በዘመነ ደርግ የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ ተብሎ የሚታወቀውና በአሁኑ ወቅት የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት በአዲስ አበባ ደረጃ በ2003 ዓ.ም የተጀመረ ቢሆንም የተማሪውን ፍላጎት ያላማከለ በመሆኑ ውጤታ ማመሆን አልቻለም ፡፡ በነዚህ ወቅቶች አፈጻጸሙ ከ26  እስከ 29 ሺ የነበረ ሲሆን በ2006 ዓ.ም ይህተሻሽሎ ወደ 49 ሺ 272 ጎልማሶችን እንዲማሩ ማድረግ መቻሉን ...

Read More »