.የኢሳት አማርኛ ዜና

ማህበረ ቅዱሳን ለሚካሄድበት የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠየቀ

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው ማህበሩ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለሁሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ  ማህበሩ” በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት በተጠሩ ስብሰባዎች የተፈጸምበት የስም ማጥፋት ...

Read More »

በደቡብና ጋምቤላ ድንበር አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ሌሎችም የጋምቤላ አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ50 በላይ የመንግስት ፖሊሶች፣ ወታደሮችና ታጣቂዎች የተገደሉበት የደቡብ እና ጋምቤላ ድንበሮች አዋሳኝ በሆነው ጉራፈርዳ ወረዳ አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ጋምቤላ ከተማና አቦቦ ወረዳ መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት ከ3 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ከተማዋ በመከላከያና ፖሊሶች ተወራለች። የመንግስት ስራና ትምህርትቤቶች ዝግ ሆነው የዋሉ ሲሆን፣ በአብዛኛው አካባቢዎች ከቦታ ...

Read More »

በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ በርካታ ዜጎች ጉዳት ደረሰባቸው

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የተነሳ የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ በአሚባራና ዱላሳ ወረዳዎች ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎች እንደሚሉት በአሚባራ አካባቢ ከ5 ሺ ሄክታር በላይ የታረሰ መሬት መውደሙን፣ የ7 ቀበሌ ሰዎች በውሃ መከበባቸውንና ንብረታቸው በውሃ መወሰዱን እንዲሁም አንድ የእርሻ ምርምር ማእከል በውሃ መወሰዱን ገልጸዋል። እስካሁን የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ በአይቻልም፣ አንዳንድ ...

Read More »

የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ችሎት ቢጀምርም የችሎት መጓተት እየተፈታተነው ነው ሲል ድምጻን ይሰማ ገለጸ

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት የችሎት መቋረጥ በሁዋላ ስራ የጀመረው ፍርድ ቤቱ፣ አንድ ምስክር እንካ በአግባቡ ሳያዳምጥ መብራት ሄደ በሚል ምክንያት እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጿል። ሰኞ በነበረው ችሎት አቶ አህመድ ኡመር የተባሉ ምስክር እየተናገሩ ባለበት ጊዜ  ምስክርነታቸው ሳይጠናቀቅ መብራት በመሄዱ ለማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥም ዛሬ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሁኔታ ችሎቱ ሳይካሄድ መቅረቱን ድምጻችን ይሰማ ገልጿል፡፡ ለዛሬው ችሎት መቆረጥ የቀረበው ...

Read More »

እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከፍተኛ ቅጣት ሊጠብቀው ይችላል

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ” በሚል ወንጀል የተከሰሰው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ከተባለ በሁዋላ፣ ውሳኔውን በእስር ላይ ሆኖ እንዲሰማ ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት ወደ እስር ቤት ተልኳል። ጋዜጠኛ ተመስገን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሲሰራ ” ድህረ ምርጫ 1997 ዓምን ተከትሎ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስ በተደረገው የአደባባይ አመጽ እንዲሁም ...

Read More »

ስድስት ወታደራዊ መኮንንኖች ተሾሙ

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ3 ወታደራዊ አዛዦች የሌተናል ጄኔራል ማእረግ ሲሰጥ ለቀሪዎቹ ደግሞ የሜጀር ጄኔራል መእረግ ሰጥቷል። ማእረጉ ከተሰጣቸው ጄኔራሎች ውስጥ 4ቱ የትግራይ አንዱ የአማራና አንዱ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኮንኖቹ ባስመዘገቡት ውጤት ማእረግ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ግንቦት7 ከአራት አመት በፊት ያወጣውን የወታደራዊ መኮንኖች የብሄር ተዋጽኦ ጥናት ክለሳ መሰረት አድርጎ ይፋ ባደረገው መረጃ ከ10ሩ ...

Read More »

በሸኮ መዠንገር ታጣቂዎችና በፌደራል ፖሊሶች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከ50 በላይ የፌደራልና የመከላከያ አባላት ተገደሉ።

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት  ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ከ10 ያላነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ 4 ታጣቂ ሚሊሺያዎችና 3 የወረዳ ፖሊሶች ተገድለዋል። የሟቾቹ አስከሬን በሚዛን አማን ሆስፒታል እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ዘመድ ያላቸው ወደ ዘመዶቻቸው ሲሸኙ፣ የቀሪዎቹ የቀብር ...

Read More »

ኢህአዴግ አመራሮች በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት እንደተከፋፈሉ ነው

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በፕሬዚዳንቱና በ7 የስራ አስፈጻሚ አባላት መካከል ተፈጥሮ የቆየውን ውዝግብ ለመፍታት ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁሉንም ወገኖች አዲስ አበባ ቢጋብዙም፣ ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሙሃመድ የጠ/ሚሩን ጥሪ ውድቅ በማድረግ የራሳቸውን ጉባኤ በመጥራት አዲስ የስራ አስፈጻሚዎችን ሾመዋል። ባለፈው መስከረም 24 ቀን በፊቅ ከተማ በተደረገው ጉባኤ፣ ፕሬዚዳንቱ የራሳቸውን ደጋፊዎችና ዘመዶቻቸውን  በስራ አስፈጻሚነት አስመርጠዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ አቶ በላይ በፈቃዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሾመ

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚሰጡት ደካማ አመራር ከፍተኛ ትችት ሲድርስባቸው የቆዩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ፣  ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ካሳወቁ በሁዋላ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ በላይ ፈቃዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል። ኢ/ር ግዛቸው በተመረጡ በወራት ውስጥ በርካታ የስራ አስፈጻሚ አባላት በመሪው አመራር ደስተኛ ባለመሆን ራሳቸውን ከሃላፊነት አግለለው ቆይተዋል፡፤ በውጭ የሚኖሩ ደጋፊዎቻቸውም ቅሬታቸውን ...

Read More »

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው 10ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በቦሌ ክፍለከተማ የሚገኝ 403 ካሬሜትር ባዶ ቦታ በ22 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ሸጠ፡፡

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደሩ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ቅዳሜ ዕለት ይፋ ባደረገው የጨረታ ውጤት መሠረት በቦሌ ክፍለከተማ ለአንድ ካሬሜትር መሬት ቦታ አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ለካሬሜትር 55ሺህ 597 ብር ከ65 ሳንቲም የሰጠ ሲሆን ግለሰቡ አሸናፊ የሆኑበት 403 ካሬሜትር ገንዘብ ሲሰላ 22 ሚሊየን 405ሺህ 852 ከ95 ሳንቲም ሆኗል፡፡ በዚሁ ክፍለከተማ ለጨረታ ከቀረቡት 38 ቦታዎች መካከል በዝቅተኛ ዋጋ ያሸነፈው ...

Read More »