ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲ ለሁለት እንደተሰነጠቀ በማስመሰል ያቀነባበሩት ሴራ መጋለጡን እና መክሸፉን ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት የደረሰን ዜና ያመለክታል። ምርጫ ቦርድ “የአንድነትን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተዋል” ሲላቸው የነበሩት አቶ አየለ ስሜነህ፤ በዛሬው እለት “አንድነት አንድ ነው፤ እናት ፓርቲዬን ለማዳን ተመልሻለሁ” በማለት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በአንድነት ስም ተጠራ የተባለውን የዲ-አፍሪኩን ስብሰባም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙሉ በጥቂት ቀናት ትምህርት ብቻ ከአንድ የውጪ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ እንዲያገኙ መደረጋቸው ተመለከተ።
ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀገሪቱ የምትመራበትን ፖሊሲ ከመጠምዘዝ ጀምሮ ድርጊቱ በሀገርና በህዝብ ላይ የከፋ ተጽእኖ እንዳለው የተገነዘቡ ኢትዮጰያውያን በዩኒቨርሲቲው ላይ የተቃውሞ ዘመቻ እያስተባበሩ ነው። አዲስ አበባ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ሊደር ሺፕ ኢንስቲትዩት አማካይነት የሚቀርቡለትን ባለስልጣናት በአጭር ቀናት ኮርስ በማስተርስ ዲግሪ እያንሸበሸ ያለው ፤በእንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ነው። በአይ ኤል አይ ድረገጽ እንደተመለከተው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን ...
Read More »በምርጫ ቦርድና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ የመጨረሻው ጫፍ ላይ ደርሷል ። ፓርቲው -ጥር 17 ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው
ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምርጫ ቦርድ የውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርታችሁ የውስጥ ችግራችሁን ካልፈታችሁ በመጪው ምርጫ አትሳተፉም የሚል ውሳኔ በ አንድነትና በመ ኢአድ ፓርቲዎች ላይ ማሳለፉን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ የቦርዱን ውሳኔ ለማሟላት ከሳምንት በፊት በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱ ይታወሳል። ይሁንና በወቅቱ ድርጅቱ በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተጋብዞ ተወካዩን ለመላክ ፈቃደኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲው በአቋም ...
Read More »የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ጥሪ አቀረበ
ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ጥሪ ያቀረበው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር፤ <<ምህዳሩ ካልተስተካከለ ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረውም ቢሆን ከምርጫ ልንወጣ እንችላለን›› ሲል አስታወቀ። ትብብሩ ፡<<ነፃነትን የማስመለስ ትግሉን አጠናክረን እንቀጥላለን>> በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ፤ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አፈና እና ጫና እያደረጉ ቢሆኑም ነፃነትን ለማስመለስ የያዘውን ግብ ለማሳካት ወደኋላ እንደማይል አረጋግጧል፡፡ ‹‹የኢህአዴግ ጨካኝነትና የምርጫ ቦርድ ...
Read More »የመኢአድ አባላት በጅምላ እየታፈሱ ነው
ጥር ፲፫(አስራ ሦስት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት አባላት በብዛት እየታሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው አንድ የመኢአድ አመራር ገለጹ። የድርጅቱ የ አዲስ አበባ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አወቀ አባተ ለኢሳት እንደገለጹት፤በምራብ ጎጃም ዞን በዳንግላ ወረዳ ጫራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የመኢአድ አባላት ወጣት ታጀለ አለኸኝ እና ወጣት የዋንስ ገደቡ፣ እንዲሁም የቡሬ ወረዳ የ መ ኢአድ ወኪል ...
Read More »በመላ ትግራይ የምርጫ ኣስፈፃሚ ለተባሉ ሚሊሻዎች የተኩስ ልምምድ ስልጠና እየተሰጠ ነው ፤ በምስራቅ ጎጃም የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች ስኳር እንዳይወስዱ ተከለከሉ
ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ በመላ ትግራይ ክልል <<ምርጫ አስፈጻሚ>>የተባሉ ተኳሽ ሚሊሻዎች ከፍተኛ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ በለክልሉ ያሉ ወኪሎቻችን ዘግበዋል። ይህ የሚሊሻዎች ስልጠናው ፤ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሗላ በዓይነቱም ሆነ በሰልጣኞቸ ብዛት ለየት ያለ ሲሆን፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የህወሓት ኣባላት ብቻ የተሳተፉበት መሆኑ ታውቋል። ሚሊሻዎቹ በኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ ፣ሓየሎም ቀበሌ <ቓፀሎ ...
Read More »በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ባለፉት ሁለት ዓመታት በእጅጉ ማሽቆልቆሉን <፣ያንግ ላይቭስ>> የተሰኘ ተቋም ይፋ አደረገ።
ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ በሆኑት በዶክተር አሉላ ፓንክረስ የሚመራው <፣ያንግ ላይቭስ>> ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት ደረጃና ጥራት ከክልል-ክልል እንደሚለያይ ጠቁሟል። ትምህርት ከጀመሩ ተማሪዎች መካከል 17 በመቶ ያህሉ በተለያዩ ችግሮች እንደሚያቆሙ ያመለከተው ጥናቱ፤ ከሚማሩት መካከልም 24 በመቶዎቹ ወደተከታዩ ክፍል ማለፍ እየተሳናቸው እንደሚደግሙ ይጠቁማል። ዋና ጽህፈት ቤቱ በእንግሊዝ የሆነው<< ያንግ ...
Read More »<<ኢትዮጰያ ውስጥ ያለው ችግር የዘር ፉክክር ነው>>ሲሉ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ተናገሩ።
ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ያሉት ሰማያዊ ፓርቱ እና በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ በመተባበር ያዘጋጁትን ውይይት ሲከፍቱ ነው። <<ሁላችንም ስንለወጥ ነው ለውጥ የሚመጣው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ከጣሊያን ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ባንዳው፣ፖሊሱ፣ባለስልጣኑ ሁሉ በመሸጦነት ማለፋቸውን በማውሳት፤ አንድ ትውልድ ይህን የመሸጦነት ባህል እየተባበረ ከሄደ ለውጥ እንደማይመጣ በአንጽንኦት ተናግረዋል። ተከታዩ ተናጋሪ ...
Read More »የታዋቂው የሬጌ አቀንቃኝ የቦብ ማርሌይ ሐውልት በአዲስ አበባ ሊቆም ነው።
ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሐውልቱ ስራ አስተባባሪዎች መካከል የጃኖ ባንድ መስራች የሆነው አርቲስት አዲስ ገሰሰ ለታዲያስ አዲስ እንደገለጸው፤ የቦብ ማርሌይ ሐውልት ከሶስት ሳምንት በሁዋላ በገርጂ ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ይቆማል። በምርጫ 97 ዋዜማ የቦብ ማርለይ 60ኛ አመት በመስቀል አደባባይ ሲከበር፤ በወቅቱ የመዲናዋ ከንቲባ የነበሩት አቶ አርከበ እቁባይ በበአሉ የተገኙትን የቦብ ማርለይ ቤተሰቦችን ሐውልቱ ይቆምበታል ወደተባለው ...
Read More »<<ዝም ብላችሁ ጥሩ ነገር ብቻ ብትናገሩ አንሰማችሁም፤ እንደውም አጭበርባሪ ነው የምንላችሁ>> ሲሉ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል -አርቲስቶችን ተናገሩ።
ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን- ከአርቲስቶች ጋር ባደረጉት ዝግ ስበሰባ የተናገሩት ነገር ተቀርጾ በይፋ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀ ሲሆን፤ በንግግራቸው አርቲስቶችን ሲመክሩና፣ ሲያባብሉ እና ሲገስጹ ተሰምተዋል። <<በፌስ ቡክ የሚነገረንን ነገር እንሰማለን፤አርቲስቶች ሆዳሞች እንደምትባሉ እናውቃለን!>> ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፤ <<መለስን ሳይቀር የሚሳደቡ አሉ፤ መለስን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ሲሰድቡን አይተናል>> ብለዋል። <<እናንተም የፈለጋችሁትን ነገር ንገሩን፤ ...
Read More »