በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ባለፉት ሁለት ዓመታት በእጅጉ ማሽቆልቆሉን <፣ያንግ ላይቭስ>> የተሰኘ ተቋም ይፋ አደረገ።

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ በሆኑት  በዶክተር አሉላ ፓንክረስ የሚመራው  <፣ያንግ ላይቭስ>> ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥናት  ኢትዮጵያ ውስጥ  የትምህርት ደረጃና ጥራት ከክልል-ክልል እንደሚለያይ ጠቁሟል።

ትምህርት ከጀመሩ ተማሪዎች መካከል  17 በመቶ ያህሉ በተለያዩ  ችግሮች እንደሚያቆሙ  ያመለከተው ጥናቱ፤ ከሚማሩት መካከልም 24 በመቶዎቹ  ወደተከታዩ ክፍል ማለፍ እየተሳናቸው እንደሚደግሙ  ይጠቁማል።

ዋና ጽህፈት ቤቱ በእንግሊዝ የሆነው<< ያንግ ላይቭስ>> የኢትዮጵያን  የትምህርት ጥራት አሰመልክቶ ያጠናውን  ይህን ጥናት ሰሞኑን  በአዲስ አበባ  ይፋ አድርጓል።

ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ  የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቀለ  እንደመጣ  በርካታ  ምሁራን  በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።