.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢህዴድ በሐረርጌ በጨለንቆ ከተማ ያስገነባው የሰማዕታት ሐውልት የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ባልተገኙበት   መመረቁን ምንጮች ጠቆሙ፡፡

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅዳሜው የሐውልት ምረቃው ላይ ያልተገኙት ጠ/ሚኒስትሩ፣  በማግስቱ በጅማ ከተማ በተካሄደው የስታዲየም ሰልፍ ላይ ተገኝተው ኦህዴድን የሚያወድስ ንግግር ቢያደርጉም እርሳቸውም ሆኑ የህወሃት ባለስልጣናት በሃውልቱ ምርቃት ላይ አልተገኙም። የህወሃት ከፍተኛ አዛዦች በሐውልት ምረቃው ላይ ያልተገኙት “ኦህዴድን  የፈጠርነው እኛ ነን” ከሚለው የህወሃቶች ትምክህት ወይም  ኦህዴድ ሰማዕታት አሉኝ በማለት የሚናገረውን ላለመቀበልና ዕውቅና ላለመስጠት ሊሆን እንደሚችል ምንጮች ...

Read More »

2ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎች ሰፖርታዊ ውድድር በመጋቢት ወር መካሄዱ በትምህርት ጊዜቸው ላይ ተጽእኖ እንዳሳደረባቸው ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው 2ኛው የትምህርት ቤቶች ውድድር ተገኙት ተወዳዳሪዎች እንደተናገሩት በውድድሩ በርካታ አዳዲስ ተተኪ ወጣቶች ለማፍራት የሚያስችል  ቢሆንም ወቅቱን የጠበቀ አለመሆኑ በትምህርታቸው  ላይ ጉዳት እንደሚያደርስባቸው ተናግረዋል፡፡ ከመጀመሪያው መንፈቅ አመት ፈተና በኋላ በቀጥታ ወደ ስፖርት ውድድር ልምምድ በመግባታቸው፣  ከትምህር ገበታቸው ላይ ለሁለት ወር ያህል መለየታቸውንና ከዛም  ለውድድር ወደ ባህርዳር መምጣታቸውን ...

Read More »

በኤርትራ የወርቅ ማውጣት ስራ ላይ የተሰማራው ኩባንያ ጥፋት እንደተፈጸመበት አስታወቀ

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢህአዴግ መንግስት ቅርበት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ አየር ሃይል ኤርትራ ውስጥ የሚገኘውን ቢሻ የማእድን ማውጫ ኩባንያን መደብደቡን ቢዘግቡም፣  በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በይፋ የተሰጠ ማረጋጋጫም ሆነ ማስተባበያ አልተገኘም። ይሁን እንጅ የኩባንያው 60 በመቶ የአክሲዮን ባለቤት የሆነው ተቀማጭነቱ ካናዳ የሆነው ኩባንያ ፣ በማእድን ማውጫው ላይ  ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መጠነኛ ጥፋት ወይም በእንግሊዝኛ ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዙ

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች ...

Read More »

ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በ አባይግድብ ዙሪያ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን ውዝግብ ይፍታል የተባለ ስምምነት መፈራረማቸውን  የግብጹ አህራም ኦንላይን ዘግቧል።

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስቱ ሀገራት የፈረሙት ስምምነት በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት በግድቡ ምክንያት በግብጽና በ ኢትዮጵያ መካከል  የነበረውን ውጥረት የሚያስቀር ነው ብሏል-አህራም። “የዓባይ ወንዝ ለሺህዎች ዓመታት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሲፈስ ኑሯል”ብለዋል የግብጹ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ -ስምምነቱን ለመስማት በካርቱም ለተሰባሰቡ የተፋሰሱ ሀገራት ልኡካን ባደረጉት ንግግር። አል ሲሲ አክለውም፦”በመተባበር ትልቅ ነገር መፈጸም አለያም ባለመስማማት እርስበርስ መጎዳዳት እንችላለን፤ ...

Read More »

በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ከኢትዮጵያ ለቆ ወጣ

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ የተቋረጠውን የሰላም ድርድር በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ለማስጀመር የነበረው እቅድ ሳይሳቃ በመቅረቱ የልኡካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ለቆ ወጥቷል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ላለፉት 2 አመታት ሲደረግ የነበረው ጥረት፣ ለወደፊቱም ይቀጥላል። ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች የሚለው መግለጫው፣ የአገሪቱን ችግር ፈትቶ ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ ለመውሰድ ገዢው ፓርቲ የተለየ ሃላፊነት አለበት ብሎአል። የልኡካን ቡድኑ ...

Read More »

በጎንደር ከተማ አንድ የሚሊሺያ አዛዥ ተገደለ በርካታ ሰዎችም ታሰሩ

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጎንደር ከተማ የሚሊያሻዎች ሃላፊ ኮማንደር መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 15 ወይም ፋሲለደስ ትምህርት ቤት አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድሏል። ገዳዮቹም መሳሪያውን ማርከው ከእነ ትጥቃቸው ወደ አርማጭሆ ጫካ መግባታቸው ታውቋል። የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ግንባሩ አካባቢ በጥይት የተመታ ሲሆን ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል። ድርጊቱን ተከትሎ ...

Read More »

ኦህዴድ በጨለንቆ የሰማዕታት ሐውልት አሰራ

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ መንግስት ወታደሮች የነበሩ ግለሰቦችን በማሳባሳብ በህወሃት አማካይነት የተመሰረተው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ለ25ኛ ኣመት የምስረታ በዓሉን ያሰራውን የሰማእታት ሃውልት ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2007 ዓ.ም በጨለንቆ ከተማ ያስመርቃል። ህወሃት እንደ ኦነግ ካሉ ድርጅቶች ጋር ግንባር ለመፍጠር የነበረው ፍላጎት ከከሸፈ በሃላ በ1982 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ደራ አካባቢ  ጥቂት በምርኮ የተያዙ ...

Read More »

በአብርሃ ጅራ አለመረጋጋቱ ጨምሯል

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው። እስካሁን በተደረገው አፈሳ የወረዳው ምክር ቤት  የህዝብ ግንኙነት ...

Read More »

በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ፖለቲከኞች የሽብር ክሱን አጣጣሉት

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ የተከሰሱ የቀድሞው የአንድነት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣  ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም የአረና ፓርቲ አመራር መምህር አብራሃ ደስታ ከሌሎች 6 ተከሳሾች ጋር መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ...

Read More »