ኦህዴድ በጨለንቆ የሰማዕታት ሐውልት አሰራ

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ መንግስት ወታደሮች የነበሩ ግለሰቦችን በማሳባሳብ በህወሃት አማካይነት የተመሰረተው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ለ25ኛ ኣመት የምስረታ በዓሉን ያሰራውን

የሰማእታት ሃውልት ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2007 ዓ.ም በጨለንቆ ከተማ ያስመርቃል።

ህወሃት እንደ ኦነግ ካሉ ድርጅቶች ጋር ግንባር ለመፍጠር የነበረው ፍላጎት ከከሸፈ በሃላ በ1982 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ደራ አካባቢ  ጥቂት በምርኮ የተያዙ የቀድሞው ጦር ወታደሮችን በማሰባሰብ  ህወሃት ድርጅት እንዲመሰረት ያደረገ መሆኑ

የሚታወቅ ሲሆን፣  ኦህዴድ በዚህ ታሪካዊ ቦታ 25ኛ ዓመት በዓሉን ሊያከብር ያልቻለው ከህወሃት ጋር የተሳሰረው ታሪኩ እንዲጎላ ባለመፈለጉ መሆኑን የኦህዴድ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ኢሳት ባለፈው ሳምንት በአሉን በትግራይ ምድር ማክበር

የሚለው ሃሳብ  የህወሃት ባለስልጣናትን ይሁንታ አለማግኘቱን ዘግቦ ነበር። ኦህዴድ በትጥቅ ትግል ወቅት ህይወታቸውን የሰው ሰማዕታተ አጽም ከተለያዩ አካባቢዎች በማሰባሰብ በጨለንቆ በተሰራለት ሐውልት እንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን ፣ ይህንኑ

ሐውልት ቅዳሜ ለመመረቅ ከፍተኛ የፌዴራልናn የክልል ባለስልጣናት፣ የኦህዴድ አባላትና ከፍተኛ ካድሬዎች፣ አምባሳደሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ድሬዳዋ ከተማ በመግባት ላይ ናቸው፡፡

25ኛ የኦህዴድ የኢዮቤልዮ በዓል አከባበር ከጨለንቆ በተጨማሪ በነቀምቴ፣ በጅማ፣ በአምቦ፣ በሻሸመኔ፣ በአዳማ እና በፊኒፊኔ ከተሞች ከመጋቢት 9 እስከ 17/ 2007 ዓ.ም የተለያዩ ግንባታዎችን በመመረቅ፣ ሲምፖዚየም በማካሄድ በመከበር ላይ የሚገኝ

ሲሆን ፣ የማጠቃለያ በዓሉ በአዲስአበባ ስታዲየም መጋቢት 17 ቀን እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

በአቶ ኩማ ደመቅሳ፣ በአቶ አባዱላ ገመዳ፣በጄኔራል ባጫ ደበሌና በሌሎችም በአጋጣሚ መመስረቱ የሚታወቀው ኦህዴድ፣ በምስረታ በአሉ ላይ  ድርጅቱ  ለነጻነታቸው ሲሉ የትጥቅ ትግል በጀመሩ ኦሮሞዎች እንደተመሰረተ ተደርጎ  ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ መሰራጨቱ

አንዳንድ የህወሃት ነባር ታጋዮችን እንደላስደሰተ ታውቋል፡፡