በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ከኢትዮጵያ ለቆ ወጣ

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ የተቋረጠውን የሰላም ድርድር በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ለማስጀመር የነበረው እቅድ ሳይሳቃ በመቅረቱ የልኡካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ለቆ ወጥቷል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ላለፉት 2

አመታት ሲደረግ የነበረው ጥረት፣ ለወደፊቱም ይቀጥላል። ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች የሚለው መግለጫው፣ የአገሪቱን ችግር ፈትቶ ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ ለመውሰድ ገዢው ፓርቲ የተለየ ሃላፊነት አለበት ብሎአል።

የልኡካን ቡድኑ ኢትዮጵያ በደረሰ በአጭር ሰአታት ውስጥ መመለሱ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።