.የኢሳት አማርኛ ዜና

ምርጫውን ተከትሎ በኦሮምያ ብቻ ከ600 በላይ የመድረክ አባላት ታስረዋል

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብዙዎች ዘንድ አስቂኝ ተብሎ የተተቸውን የ2007 ዓም ምርጫ ተከትሎ በኦሮምያ ብቻ ከ640 በላይ የመድረክ ደጋፊዎች ሲታሰሩ፣ 66 በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣7 አባለት በጥይት ቆሰልዋል፣ 2 አባላት ደግሞ መገደላቸውን መድረክ አስታውቋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር በሺዎች እንደሚቆጠር መረጃዎች ያመለክታሉ። መድረክ እንዳለው በምርጫ 2007 ማግሥት በመድረክ አባላት ላይ የሚፈጸሙት የማዋከብና የማሰቃየት ...

Read More »

ከምርጫው ጋር በተያያዘ በምስራቅ ጎጃም የደህንነት ሃላፊ ሆኖ የተሾመው የህወሃት አባል ነው ተባለ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክረምቱ ወቅት 119 የሚሆኑ የብአዴን አባላት በድሬዳዋ ከተማ የደህንነት እና መረጃ መሰብሰብ ስልጠና ተሰጥቷቸው በክልሉ ከተሰማሩት መካካል አንዱ የሆነው ሰራተኛው እንደገለጸው፣ ማንኛውም ደህህነት ሰራተኛ የስለላ ሪፖርቱን ተክሌ ለተባለ የደህንነት ሰራተኛ ሲያቀርብ መቆየቱን ለኢሳት ተናግሯል። ስልጠናውን ከወሰዱት የደህንነት ስራተኞች መካከል አንዳንዶች በምስራቅ ጎጃም ደብረማርቆስ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሆነው በመመዝገብ መረጃዎችን ሲያስተላልፉ፣ ...

Read More »

በግል የጤና ተቋማት ላይ ትችት ቀረበ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የማህበራዊ ጥናት መድረክ በቅርቡ ባካሄደው ጥናት በአዲስአበባ የግሉ የጤና ዘርፍ ከፍተኛ የጥራት መጓደልን ይዞ የተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ እየጠየቀ መሆኑን ገልጿል። ጥናቱ በአዲስአበባ ከሚገኙ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች መካከል በ34ቱ ላይ ያተኮረ ሲሆን አገልግሎት ክፍያ (ዋጋን) በተመለከተ በመንግስት ሆስፒታሎች የካርድ ክፍያ አማካይ ዋጋ 5 ብር ሲሆን፣ በግል ክሊኒኮች አማካይ ዋጋ 100 ብር ነው፡፡ ...

Read More »

ከምርጫው በሁዋላ መንግስት “የበቀል ጅራፉን” እያሳረፈብን ነው ሲሉ የደቡብ ክልል የተቃዋሚ አባላት ተናገሩ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምርጫው በአሳፋሪ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የመድረክ ደጋፊዎችን ቤቶች መቃጠላቸውን፣ መደብደባቸውንና ማሳደዳቸውን የአርባምንጭ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ በላካ ቀበሌ ብዙ ሰዎች አካላ ጎደሎ ሆነዋል፣ ቤቶቻቸውም ተቃጥሎባቸዋል የሚሉት ነዋሪዎች፣ የቀበሌ አመራሮች ከሰኔ 15 በሁዋላ መግቢያችሁን ፈልጉ እየተባሉ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ዳዊት ጉበዜ እና አዛውንት እናቱ ወ/ሮ ሃማሜ ሃይሉ ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል ...

Read More »

ፍርድ ቤት አቶ ማሙሸት አማረን ይፈቱ ቢልም ፖሊስ ግን አለቅም አለ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ ቦርድ የታገደው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ማሙሸት አማረ ከሳምንታት እስር በሁዋላ በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢያስተላልፍም፣ ውሳኔው ለሁለተኛ ጊዜ በፓሊስ ተጥሶ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ግንቦት 26/2007 ቦሌ የሚገኘው ችሎት አቶ ማሙሸት የቀረበባቸው ክስ እንደማያስከስሳቸው በመግለጽ እንዲፈቱ ቢወስንም፣ ፖሊስ በራሱ ...

Read More »

ወጣት ሳሙኤል አወቀ በመንግስት ታጣቂዎች መገደሉን ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ” የሰማዕታት ደም ይጮሃል፤ ይጣራል” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት አካላት ናቸው ብሎአል። ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ ብሎ እንደማይጠይቅም አስታውቋል። “ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ሹፌሮች ያደረጉትን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናት እገዳ ጣሉ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ሰበብ አስባቦች የሚጣልብን ቅጣትና እገዳ ተገቢ አይደለም በሚል ሰኔ 8፣ 2007 ዓም ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ አድርገው የነበሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ሾፌሮች፣ ፣ ከአድማው በሁዋላ ችግራቸውን የሚሰማ እና መፍትሄ የሚሰጥ አካል ይኖራል ብለው ሲጠብቁ፣ በተቃራኒው ከስራ መታገዳቸውን ተናግረዋል። ሾፌሮች እና ባለሃብቶች እንደሚናገሩት “የመንግስትን ትእዛዝ አላከበራችሁም ፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊዎች ...

Read More »

በቴፒ የወረዳው አዛዥና ፖሊሶች ታሰሩ

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ለመብት የሚታገሉ የከተማዋ ወጣቶች በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል ፖሊስና የጸረ ሽብር ግበረሃይል አባላት በከተማዋ ተገኝተው እጃቸው አለበት ብለው የጠረጠሩዋቸውን የቴፒ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 7 ፖሊሶችን ይዘው አስረዋል። ባለስልጣኖቹ የከተማውን ህዝብ ያነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በነጻነት እጦት እየተሰቃየ መሆኑንና ወጣቶች እርምጃ የሚወስዱት ከዚህ ተነስተው መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአካባቢው የሚታየውን ...

Read More »

በርካታ ቁጥር ያላቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ ነው

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንት በፊት አልሸባብ የተባለው የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል በቡርካባ ግዛት ጃሚዮ በሚባል ቦታ ላይ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ከ30 በላይ ወታደሮችን ከገደለ በሁዋላ፣ በርካታ ቁስለኞች ሞቃዲሹ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ቁጥር ሁለት ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው በመታከም ላይ ናቸው። አሚሶም በመባል የሚታወቀው በሶማሊያ የሰፈረው የአፍሪካ ህብረት ጦር በአልሸባብ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል። የአፍሪካ ህብረት ...

Read More »

በጋምቤላ የመሬት ኪራይ እዳ ካልከፈሉ 150 ባለሀብቶች መካከል እጅግ አብዛኞቹ የትግራይ ብሄር ተወላጆች መሆናቸውን አንድ ሰነድ ጠቆመ

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋምቤላ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት በጋምቤላ እርሻ ስራ ተሰማርተው የሚፈለግባቸውን የመሬት ኪራይ እዳ ባልከፈሉ 150 ባለሀብቶች ላይ ያወጣው የማሳሰቢያ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፤ የጋምቤላን መሬት የተቀራመቱት ከ90 በመቶ የሚልቁት የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ባለሀብቶቹ ከ2006 እስከ 2007 ሰኔ ወር ድረስ ያለባቸውን ውዝፍ እዳ አጠቃለው እንዲከፍሉ በወጣው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ላይ ስማቸው በዝርዝር ተቀምጧል። ...

Read More »