(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010)በኦሮሚያ ክልልና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የማጣራት ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑንም ሃላፊው ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በጎረቤት ሶማሌ ላንድ የሚኖሩ ከሶስት ሺ የሚበልጡ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን መንግስት በይፋ አስታውቋል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የብአዴን አጠቃላይ ስብሰባ በገጠመው የከፋ ተቃውሞ ወደ ዋናው የስብሰባ አጀንዳ መግባት እንደተሳነው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) የብአዴን አጠቃላይ ስብሰባ በ4ኛ ቀን ውሎው በገጠመው የከፋ ተቃውሞ ወደ ዋናው የስብሰባ አጀንዳ መግባት እንደተሳነው ታወቀ። የራያ ጉዳይ ተጨምሮበት ስብሰባው በጭቅጭቅና ሃይለቃል በተሞላበት ምልልስ በቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የግጨው፣የወልቃይትና የራያ ጉዳይ እያለ ሌላ አጀንዳ አያስፈልገንም ያሉት ተሳታፊዎች የብአዴንን መሪዎች በጥያቄ ወጥረው መያዛቸው ተሰምቷል። በተለይ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ የሚወረወሩት ተራ የሚባሉ አይነት ስድቦች ስብሰባውን የከፋ እንዲሆን ማድረጉን ...
Read More »ከባሌ ዞን ለተፈናቀሉ ከሶስት ሺ በላይ የሲዳማ ተወላጆች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) ከባሌ ዞን ለተፈናቀሉ ከሶስት ሺ በላይ የሲዳማ ተወላጆች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ። በህወሃት መንግስት የእጅ አዙር ትዕዛዝና ግፊት በኦህዴድ አስፈጻሚነት በታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለው ማፈናቀል ሕጻናትን ጨምሮ ነፍሰጡር እናቶችና ደካማ የሆኑ አዛውንቶች ከፍተኛ ጉዳት ላይ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ወገናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቀው የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈናቀሉት የሲዳማ ብሔር ተወላጆችን ቀይ መስቀል ለጊዜው እየረዳቸው ...
Read More »የደመራና የመስቀል በአል በድምቀት ተከበረ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010) በኢትዮጵያና በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ምዕመናኑ የደመራን በአል በድምቀት አከበሩ። የመስቀልም በአልም በመላው ኢትዮጵያ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ውሏል። በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በከፍተኛ ድምቀት የተከበረው የደመራ በአል ከኢትዮጵያ ውጪ በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ብዙ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል። ከአሜሪካ ርዕሰ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ በተጨማሪ በሌሎች የአሜሪካ ከተሞች ሎስአንጀለስ፣ ...
Read More »የትነበርሽ ንጉሴ የስዊዲን አማራጭ የኖቤል ሽልማትን ተቀዳጀች
(ኢሳት ዜና–መስከረም 16/2010) የሰብአዊ መብት ጠበቃና የሕግ ባለሙያ የትነበርሽ ንጉሴ የስዊዲን አማራጭ የኖቤል ሽልማትን ተቀዳጀች። ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ የተባለውን ሽልማት ያገኘችው የትነበርሽ ንጉሴ ከሁለት ሌሎች የአማራጭ ኖቬል አሸናፊዎች ጋር 374 ሺህ ዶላር ገንዘብ ትካፈላለች። የትነበርሽ ንጉሴ ሽልማቱን ያገኘችው ከ5 አመት የልጅነት እድሜዋ ጀምሮ ሊከላከሉት በሚችሉት በሽታ ምክንያት አይነ ስውር ብትሆንም በጥረቷ ስኬታማና ሌሎችንም የአካል ጉዳተኞች በመረዳት ላበረከተችው አስተዋጽኦ ነው። ገና ...
Read More »በሌብነት የተጠረጠሩ አራት የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤቶች ከሀገር ማምለጣቸው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 16/2010) በሌብነት የተጠረጠሩ አራት የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤቶች ከሀገር ማምለጣቸው ታወቀ። ሆኖም በሌሉበት በአራቱም ላይ ባለፈው ሳምንት ክስ መመስረቱ ታውቋል። የኮንስትራክሽን ድርጅቶቹ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሃላፊዎች ጋር በመሆን በ2 ቢሊየን 150 ሚሊየን ብር ዘረፋ ተጠያቂ መሆናቸው ተመልክቷል። በሌብነት ተጠርጥረው ሲፈለጉ ከሀገር በማምለጣቸው ፍርድ ቤት ያልቀረቡት የሳትኮን ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ተክላይ፣የገምሹ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ እንዲሁም የዲ ኤም ...
Read More »መንግስት የብርን ዋጋ በመቀነስ የገጠመውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመከላከል የመጨረሻ ጥናት ማዘጋጀቱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 16/2010) በኢትዮጵያ የተደቀነውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና አመታዊ የዕዳ ክፍያ በተመለከተ መንግስት የብርን ዋጋ በመቀነስ ለመሻገር የመጨረሻ ጥናት ማዘጋጀቱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በዚህ አመት መንግስት ሊከፍለው የሚገባውን ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ እዳ ለመሸፈን የኢትዮጵያ ሒልተን ሆቴልን ለመሸጥ ሃሳብ መቅረቡም ተመልክቷል። ኢትዮ-ቴሌኮምን ለኬንያው ሳፋሪ ኮም 50 በመቶ ለመሸጥ አንዳንድ ባለስልጣናት በሚስጥር መነጋገራቸውንም የደረሰን ዜና ያስረዳል። የብር ዋጋ ቢቀንስ የወጭ ...
Read More »በብአዴን ድርጅታዊ አመራር አባላት መካከል የተከሰተው ውዝግብና አለመግባባት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/20015) በብአዴን ድርጅታዊ አመራር አባላት መካከል የተከሰተው ውዝግብና አለመግባባት ተባብሶ መቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። የድርጅቱ ማእከላዊ አባላት እና የክልሉ ምክር ቤት ሳይስማሙበት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተፈራረሙት የግጨው ስምምነት ለውዝግቡ ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ ተገልጿል። የሞባይል ስልክ እንዳይገባ ተደርጎ በሚስጥርና በጭቅጭቅ የተካሄደው የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባላት ስብሰባ የቃላት ልውውጥ ደርሶናል። የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ፕሬዝዳንቶች የተፈራርሙት የግጨው ስምምነት በተወሰኑ ሰዎች ...
Read More »የ2019 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010) የ2019 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚጀምር ታወቀ። ብሪታኒያ፣ካናዳና ቻይናን ጨምሮ ከ20 የሚበልጡ ሀገራት ዜጎች በእድሉ እንዳይጠቀሙ ዕገዳ ተጥሏል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነውና ከቀደመው የቀጠለው ፕሮግራም ከአፍሪካ ናይጄሪያን አስቀርቷል። እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መስከረም 23/2010 በዋሽንግተን ዲሲ ሰአት አቆጣጥር እኩለ ቀን ላይ የሚጀምረው ፕሮግራም እስከ ጥቅምት 28/2010 ድረስ እንደሚቀጥልም ታውቋል። በ2019 የዲቪ ...
Read More »በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ እየቆሰቆሰና እየፈጠረ ካለው ግጭት እንዲቆጠብ የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ገለጹ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010)በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በጎሳዎችና በብሔሮች መካከል ሆን ብሎ እየቆሰቆሰና እየፈጠረ ካለው ግጭት እንዲቆጠብ የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ባወጡት መግለጫ አሳሰቡ። በዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ላይ አተኩሮ በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደውና በቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ትብብር የተዘጋጀው ሀገራዊ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች አገዛዙ ሰዎችን ከመግደልና ከማንገላታት እንዲሁም የግለሰብ ነጻነትን ከመድፈር እንዲቆጠብ ጠይቀዋል። ሕዝቡም አንድነቱን እንዲጠብቅ ጉባኤተኞቹ ጥሪ አቅርበዋል። 4ኛ የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ አሁን ...
Read More »