(ኢሳት ዜና–ሕዳር 7/2010) በእስር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል አህመዲን ጀቢል የገጠመው የጤና ችግር አስጊ በመሆኑ አፋጣኝ ህክምና እንዲያገኝ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ጫና እንዲፈጥሩ ፈረስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ጥሪ አቀረበ። አህመዲን ጀቢል በከፍተኛ የኩላሊት ህመም በመሰቃየት ላይ መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች በመግለጽ ላይ ናቸው። የህወሃት መንግስት የደህንነት ሃይሎች በእስር ቤት ውስጥ ከባድ ድብደባና ማሰቃየት ይፈጽሙበት እንደነበርም ታውቋል። በተደጋጋሚ ህክምና ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የዩኒቨርስቲዎችን ድልድል አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ አልቀበለውም አሉ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 7/2010)የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ምደባ አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር እየተጠቀመበት ያለውን አሰራር እንደማይቀበሉት አስታወቁ። የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ የአንድ ሀገር ህዝቦችን የሚነጣጥልና የፌደራሊዝም ስርአቱን የሚያበላሽ ነው ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተነሳ ግጭት በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል።በሺዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። አሁን ላይ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትና ከቀያቸው የተፈናቀሉትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ባለበት ...
Read More »በአማራና በትግራይ አስተዳደሮች በሕዝብ ስም የተጠራው የግንኙነት መድረክ የሕወሃትን ስልጣን ለማራዘም ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 7/2010)በአማራና በትግራይ አስተዳደሮች በሕዝብ ስም የተጠራው የግንኙነት መድረክ የሕወሃትን ስልጣን ለማራዘም የታቀደ በመሆኑ እናወግዛለን ሲል የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ልሳነ ግፉአን ማህበር ገለጸ። የማህበሩ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት የአማራን ሕዝብ በጠላትነት የፈረጀው ሕወሃት ሳይወገድ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ድርድር ማድረግ ከጠላት ጋር እንደመተባበር ይቆጠራል። እናም የአማራ ሕዝብ ወልቃይትን ጨምሮ በሕወሃት የተወሰደበት መሬት እስኪመለስና በአገዛዙ የደረሰበት በደል እስኪወገድ ድረስ ትግሉን እንዲቀጥል ልሳነ ...
Read More »ሮበርት ሙጋቤ በቤታቸው በቁም እስር ላይ መዋላቸው ተሰማ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 6/2010)የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ በቤታቸው በቁም እስር ላይ መዋላቸው ተሰማ። የሀገሪቱ ወታደራዊ አዛዦች የሬዲዮና ቴሌቪዥን ማሰራጫዎችን መቆጣጠራቸው ተሰምቷል። እንደ አዝጋሚ መፈንቅለ መንግስት እየተቆጠረ ያለውን ይህን ከፊል የሀገሪቱ ነዋሪዎች እንደ መልካም ዜና ወስደውታል ተብሏል። ዚምባቡዌ ከእንግሊዝ ነጻ ከወጣችበት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1980 ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩት የ93 አመቱ ሮበርት ሙጋቤ ከዛሬ ጀምሮ በመኖሪያቸው በቁም እስር ይገኛሉ። ሙጋቤ የሀገራቸው ወታደራዊ ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ከአለም አቀፍ መመዘኛ በታች መሆናቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 6/2010) በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ከአለም አቀፍ መመዘኛ በታች መሆናቸውን አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ገለጹ። የቻይናው ዜና አገልግሎት ዥንዋ በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የፕላኒንግ ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ኤልያስ ግርማን ጠቅሶ እንደዘገበው 89 በመቶ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ከአለም አቀፍ መመዘኛ ዝቅ ያሉ ሆነው ተገኝተዋል። በሰው ሃይል፣በትምህርት አሰጣጥ፣በመሰረተ ልማት፣በተማሪዎቹ ብቃት በአጠቃላይ በሀገሪቱ በተደረገ ጥናት 30 ሺ 605 ትምህርት ቤቶች ...
Read More »የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብና ቀውስ መቀጠሉ ተሰማ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 6/2010) ከአንድ ወር በላይ የዘለቀው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብና ቀውስ ውስጥ መቀጠሉን የሕወሃት ደጋፊዎች ይፋ አደረጉ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውም ታውቋል። ውዝግቡ በሰላም እንዲቋጭ የሕወሃት ደጋፊዎች ተማጽኖ በማቅረብ ላይ ናቸው። ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት በመቀሌ እንዲሁም በሶስተኛውና በአራተኛው ሳምንት በአዲስ አበባ ያደረጉት ስብሰባ ሊቋጭ አልቻለም ...
Read More »በአዶላ ክብረመንግስት የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 6/2010) በአዶላ ክብረመንግስት ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። ተቃውሞው የወያኔ አገዛዝ በቃን በሚል የተካሄደ ሲሆን ሰሞኑን በሶማሌ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ህዝቡ በቁጣ አደባባይ መውጣቱን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በቡሌ ሆራ ሀገረማርያም ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎች ተቃውሞ ማድረጋቸው ታውቋል። በመቱ ዩኒቨርስቲ የጸጥያ ሃይሎች ከተማሪዎች ጋር መጋጨታቸውም ተገልጿል። በባሌ ሮቤም በቄሮዎች ከፍተኛ ተቃውሞ መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል። ዛሬ አዶላ ክብረመንግስት ከ10ሺህ ...
Read More »በሊቢያ አፍሪካውያን ስደተኞች ለባሪያ ንግድ የጨረታ ሽያጭ ይቀርባሉ ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 5/2010)በሊቢያ አፍሪካውያን ስደተኞች ለባሪያ ንግድ የጨረታ ሽያጭ እንደሚቀርቡ የሚያሳይ በምስል የተደገፈ መረጃ ይፋ ሆነ። ሲ ኤን ኤን ይፋ ባደረገው በዚህ መረጃ ከ10 በላይ የሚሆኑና ከኒጀር የመጡ ስደተኞች በ6 ደቂቃ ውስጥ በጨረታ መሸጣቸውን አጋልጧል። ይህ ክስተት ከዘመናት በፊት የተሻረውን የሰው ልጅን እንደሸቀጥ የመሸጥ አስከፊነት እንደገና እንዲታወስ አድርጓል ሲል ዘገባው አመልክቷል። በሊቢያ የሚገኙ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የሚሄዱ ስደተኞችን ...
Read More »እነ ንግስት ይርጋ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባሉ
(ኢሳት ዜና–ህዳር 5/2010)በጎንደሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ በሽብር የተከሰሱት እነ ንግስት ይርጋ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባሉ። እነ ንግስት ይርጋ ያቀረቡት መቃወሚያ ግምት ውስጥ ሳይገባ እንዲከላከሉ የአገዛዙ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል። ፍርድቤቱ እነ ንግስት ይርጋን ጥፋተኛ ያላቸው የሰላማዊ ተቃውሞ መገለጫ በሆኑ የሰልፍ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ነው። በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ በጎንደሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ በጸረ ሽብር ሕጉ የተከሰሱት የሰላማዊ ተቃውሞ አንቀሳቃሾች እንደ ማስረጃ የቀረበባቸው ...
Read More »ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 5/2010)በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው ለኢሳት እንደገለጸው በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉት ሁለገብ ትግሎችን ለማፋፋም ተዘጋጅቷል። የህወሃት መንግስት በዕቅዱ ላይ በአሸባሪነት ከወነጀላቸውና ስርዓቱን በማስጨነቅ ብርቱ ፈተና እንደደቀኑ ከተጠቀሱት ድርጅቶች አንዱ አርበኞች ግንቦት ሰባት ...
Read More »