.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሕወሃት ገለልተኛ መርማሪዎች ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ቀነ ገደብ ተሰጠው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 25/2010) የኢትዮጵያው አገዛዝ በሀገሪቱ የተፈጸመውን ግድያና እስር እንዲሁም የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያጣሩ ገለልተኛ መርማሪዎች ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ቀነ ገደብ ተሰጠው። በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገለልተኛ አጣሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ካልፈቀደ ኤች አር 128 የተባለው ረቂቅ የሕግ ውሳኔ ለኮንግረሱ እንደሚቀርብ የአሜሪካ መንግስት አስጠንቅቋል። ይህ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያው አገዛዝ እንደተገለጸለት ለማወቅ ተችሏል። ኤች አር 128 በኢትዮጵያ ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጥሪ አቀረቡ

(ኢሳት ዲሲ– ጥር 24/2018)የትግራይ ምሁራን የሕወሃትን አገዛዝ በማውገዝ ከሕዝብ ጋር እንዲቆሙ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጡት መግለጫ እንዳሉት የትግራይ ምሁራን ሀገርን እየከፋፈለና የግጭት መንስኤ የሆነውን ህወሃት ባለመውገዝ ዝምታን መምረጣቸው አግባብ አይደልም። ሕወሃትን የትግራይ ሕዝብ አንድ ባለመሆናቸውም በዘር ላይ የተመሰረተ ጥቃት እንዳይኖር ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ሁለቱ ድርጅቶች አሳስበዋል። የትግራይ ሕዝብ ...

Read More »

በኬንያ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የተላለፈው ርምጃ ታገደ

(ኢሳት ዲሲ –ጥር 24/2010) የኬንያ መንግስት በሀገሪቱ ሶስት የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የወሰደውን ርምጃ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አገደ። የተቃውሞ ፓርቲ መሪና እጩ ፕሬዝዳንት የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት መሾማቸውን ተከትሎ የተፈጠረው ውዝግብ ለጣቢያዎቹ መዘጋት ምክንያት እንደሆነም ይታወቃል። ባለፈው ማክሰኞ በኬንያ ናይሮቢ ኡሁሩ ፓርክ ራሳቸውን በፕሬዝዳንትነት ሰይመው ቃለ መሃላ የፈጸሙት ሚስተር ራይላ ኦዲንጋ የሀገር ክህደት መፈጸማቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት በመግለጽ ላይ ...

Read More »

ለስራ ወደ ውጭ ሃገራት መጓዝ የሚከለክለውን እግድ ተነሳ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) መንግስት በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ለስራ ወደ ውጭ ሃገራት መጓዝ የሚከለክለውን እግድ ማንሳቱ ተገለጸ። እግዱ የተነሳው የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ በመቅረታቸው መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ከጥቅምት 2006 ጀምሮ ታግዶ የቆየው የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ከጥር 22 ጀምሮ እንዲነሳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑ ነው የታወቀው። ምክር ቤቱ ውሳኔውን ሲያሳልፍ ደግሞ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች አልተሟሉም የሚል ምክንያትን በማስቀመጥ ...

Read More »

የሕወሃት አገዛዝ የተበደረውን ገንዘብ መክፈል አልቻለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2010) የሕወሃት አገዛዝ ከውጭ ባንኮች በከፍተኛ ወለድ በተለያዩ ድርጅቶች ስም የተበደረውን ገንዘብ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መክፈል እንደተሳነው ተዘገበ። ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የደረሰ መረጃ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ከተበደረው ገንዘብ ባለፈው ጥርና የካቲት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በውጭ ምንዛሪ መመለስ ቢኖርበትም ክፍያውን ብሔራዊ ባንክ ሊፈጽም አልቻለም። በጉዳዩ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጥበት ቢጠይቅም ብሄራዊ ባንክን ጠይቁ ብሎ ...

Read More »

እስረኞች በጉልበት ሰራተኝነት መሰማራታቸው ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2010) በአፋር ክልል በሚካሄዱ የግንባታና የማምረት ስራዎች እስረኞች በጉልበት ሰራተኝነት መሰማራታቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ይህንን በአለም አቀፍ ሕግ የተከለከለው ድርጊት የሚፈጸመው ከአማራ ክልል በሚወሰዱ እስረኞች ላይ እንደሆነም ተመልክቷል። በተለይ በዳሎል አካባቢ በፖታሺየምና በጨው ማምረት ስራ ላይ የሚገኙ የሀገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች በእስረኞቹ ጉልበት በመጠቀም ላይ መሆናቸውን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ በጨውና ፖታሺየም ማምረት የተሰማሩ የሀገር ...

Read More »

በንብረት ላይ ጉዳት ባደረሱ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ሊወሰድ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2010) የአማራ ክልላዊ መንግስት ንብረት ላይ ጉዳት ባደረሱ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ሊወስድ መሆኑን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫም ንብረት ላይ ጥፋት የፈጸሙ ሰዎችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል። በወልዲያ፣መርሳና ቆቦ የተገደሉትን ሰላማዊ ዜጎችን በተመለከተ ግን ለህግ የሚቀርብ አካል ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም። ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል በማለት የተሰጠው መግለጫ ብዙዎችን ማስቆጣቱ ተሰምቷል። የአማራ ክልል መንግስት ...

Read More »

በአዳማ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2010) በአዳማ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ተገለጸ። ህገወጥ ቤት ለማፍረስ የተጀመረውን እንቅስቃሴ በመቃወም በተደረገው ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል። መንገዶች በድንጋይና በእንጨት ተዘግተው እንደነበር የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች ወደ አመጽ የተቀየረውን የህዝቡን ተቃውሞ ለማስቆም የፖሊስ ሃይል ቁጥሩን ጨምሮ መሰማራቱን ገልጸዋል። በርካታ ሰዎች መታሰራቸውም ታውቋል። በአዳማ/ ናዝሬት ዛሬ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ህገወጥ ቤት ለማፍረስ በከተማዋ ...

Read More »

የሼህ መሀመድ አላሙዲን ቤተሰቦች ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) የሼህ መሀመድ አላሙዲን ቤተሰቦች ሳውዳረቢያ ውስጥ ታሰሩ። የቢሊየነሩ ተውልደ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች የታሰሩት ሼህ መሀመድ አላሙዲን በድርድር ገንዘብ ከፍለው ከእስር እንዲወጡ የቀረበላቸውን አማራጭ ባለመቀበላቸው እንደሆነም ተመልክቷል። የሳውዳረቢያ መንግስት በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ባለሃብቶች አንዱ የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼህ መሀመድ አላሙዲን በህዳር ወር ሳውዳረቢያ ሪያድ ውስጥ መታሰራቸው ይታወሳል። በእሳቸው የተጀመረው እስር ደግሞ በቤተሰቦቻቸውም ላይ መቀጠሉን ነው ሚድል ኢስት ሞኒተር ትላንት ...

Read More »

ሁሉን ያቀፈ ሀገራዊ ጉባዔ እንዲጠራ ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2010) በኢትዮጵያ ሁሉን ያቀፈ ሀገራዊ ጉባዔ እንዲጠራ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ማህበር ጥሪ አቀረበ። ማህበሩ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የተመለከተ ባለ 34 ገጽ ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ጠመንጃ ያነሱ የነጻነት ሃይሎች፣ በሀገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሚመለከታቸው ሁሉም የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተሳታፊ የሆኑበት ጉባዔ በመጥራት ኢትዮጵያን ከተደቀነባት ሀገራዊ ቀውስ መታደግ ይገባል ሲል ማህበሩ አስታውቋል። ሪፖርቱ በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ አፈናዎች፣ ግድያዎችንና መጠነ ሰፊ ...

Read More »