(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ያሳለፉትን ውሳኔ አሜሪካ አደነቀች። የአሜሪካ መንግስት ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያና ኤርትራ ልዩነቶቻቸውን በማስወገድ ውይይት ለማድረግ የጀመሩትን ጥረት አድንቋል። የአሜሪካ መንግስት ያወጣው መግለጫ ኢትዮጵያና ኤርትራ ባለፉት 20 አመታት የነበራቸውን አለመግባባት ለመፍታትና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መወሰናቸውን አድንቋል። ቀደም ሲል የነበረው ግጭትና አለመግባባት በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሰላም ላይ አሉታዊ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የምህረት አዋጁ በቅርቡ እንደሚጸድቅ ተነገረ
የምህረት አዋጁ በቅርቡ እንደሚጸድቅ ተነገረ (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም) በሚቀጥለው ሳምንት ፓርላማው ያጸድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው የምህረት አዋጅ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ምህረት እንደሚደረግላቸው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ገልጸዋል። አዋጁ ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ቀድም ብሎ የተመራ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ እስካሁን መልስ አልሰጠበትም። ይሁን እንጅ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ አዋጁ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አርበኞች ግንቦት7 በዶ/ር ...
Read More »በነዳጅ እጥረት የሚሰቃዩ የወልድያ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
በነዳጅ እጥረት የሚሰቃዩ የወልድያ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም)አሸክርካሪዎቹ በየጊዜው በሚጨምረው የነዳጅ ዋጋ መማረራቸውን ሲገልጹ ከቆዩ በሁዋላ ዛሬ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ ቶታል ነዳጅ ማደያ፣ ኦይል ሊቢያ እና ኖክ የነዳጅ ማደያዎች መታሸጋቸው ታውቋል። አጋጣሚውን በመጠቀም በሰልፉ ላይ የተቀላቀሉ ወጣቶች፣ “በዶ/ር አብይ ሙስና የለም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል።
Read More »ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የጌዲዮ ተወላጆች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል
ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የጌዲዮ ተወላጆች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ከምዕራብና ከምስራቅ ጉጂ ዞኖች የተፈናቀሉ ከ500,000 በላይ የሚሆኑ የጌዲዮ ተወላጆች በቂ የምግብ እርዳታ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው ይገኛሉ። ሰሞኑን በይርጋጨፌ ወረዳ አንድ የ65 ዓመት አባት በረሃብ ሕይወታቸዉ ማለፉን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። በመንግሥት በኩል የተሰጡት እርዳታዎች በቂ አለመሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የደቡብ ክልል ባለስልጣናት በአካባቢው ...
Read More »የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ገተርስ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመካከላቸው የነበረውን ውዝግብ ለመፍታት እና ወደ ሰላም ለመምጣት መስማማታቸውን አደነቁ።
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ገተርስ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በመካከላቸው የነበረውን ውዝግብ ለመፍታት እና ወደ ሰላም ለመምጣት መስማማታቸውን አደነቁ። (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም)ዋና ጸሀፊው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በመካከላቸውና በአጎራባች ሀገራት ጭምር ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ስምምነት ለማምጣት እያደረጉ ያለውን ጥረትም አወድሰዋል።. ከዋና ጸሀፊው ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንደሚለው፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሱ፣ ...
Read More »የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲስ መመሪያ አወጡ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010)የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሕጻናትን ከወላጆቻቸው እንዳይነጠሉ የሚያደርግ አዲስ መመሪያ ማውጣታቸው ተሰማ። ፕሬዝዳንቱ መመሪያውን ያወጡት 2 ሺ 3 መቶ ያህል ሕጻናት ከወላጆቻቸው ተነጥለውና በአጥር ተከልለው እንዲቀመጡ መደረጉ የቀሰቀውን አለምአቀፍ ቁጣ ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም መመሪያ መሰረት የተለያዩ ወላጆችና ሕጻናት እንዲገናኙ ተወስኗል። ድንበራችንን ከሕገወጥ ስደተኞች መጠበቃችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሆኖም ሕጻናትና ወላጆቻቸው በአንድ ላይ እንዲሆኑ እንፈልጋለን ብለዋል ዶናልድ ትራምፕ። የነበረውን ሁኔታ ...
Read More »በድሬዳዋ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010) የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዒሌ ከስልጣን እንዲወርድ በመጠየቅ በድሬዳዋ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። በከተማዋ ሶስት ቀበሌዎች በተካሄደው በዚሁ ተቃውሞ አብዲ ዒሌ በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቅ ተጠይቋል። በሶማሌ ክልል ወጣቶች የተጀመረው ተቃውሞ በድሬዳዋ ቀጥሎ አብዲ ኢሌ ከሌላው የኢትዮጵያ ወገናችን ጋር ለማጋጨት እየፈጸመ ያለውን ሴራ እናወግዛለን የሚሉ መልዕክቶች የተሰሙበት መሆኑ ታውቋል። ሶማሌ ክልል የተጀመረው ተቃውሞ የአብዲ ዒሌን ከስልጣን መውረድ በመጠየቅ ...
Read More »የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምህረት አዋጁን በቅርቡ ያጸድቃል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምህረት አዋጁን በቅርቡ እንደሚያጸድቅ የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለጸ። ምክር ቤቱ ለዕረፍት ከመበተኑ በፊት የምህረት አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ገልጸዋል። በሚኒስትሮች ምክርቤት ተመክሮበት ወደ ፓርላማው የተላከው አዋጅ በቀጣዮቹ ቀናት በፓርላማ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ይሕንኑ ተከትሎም ተቋማቸው አዲስ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ...
Read More »ኮለኔል ጎሹ ወልዴ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፉ ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010) የቀድሞው መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኮለኔል ጎሹ ወልዴ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፉ ገለጸ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎናቸው እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርበዋል። “ዝምታዬን የሰበርኩት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ራዕይ እንዲሁም የለውጥና የተሃድሶ አጀንዳ ለመደገፍና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቼም እንዲደግፉት ለማሳሰብ ነው።”በማለት የ6 ደቂቃ የድምጽ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እግዚአብሔር ግዜውን ጠብቆ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያጫቸውና የመረጣቸው ግለሰብ ናቸው ብዬም ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያና ኤርትራን የሰላም ሂደት እደግፋለሁ አለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 14/2010)የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያና ኤርትራ ለጀመሩት የሰላም ሂደት ድጋፉን እንደሚያደርግ ገለጸ። የመንግስታቱ ድርጅት ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ለጀመሩት ስራ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዩ ጉተሬዝ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል የጀመሩት በጎ ስራ የሚደነቅ ነው ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሁለቱን ወንድማማች ሀገራት ...
Read More »