ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የጌዲዮ ተወላጆች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል

ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የጌዲዮ ተወላጆች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል
(ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ከምዕራብና ከምስራቅ ጉጂ ዞኖች የተፈናቀሉ ከ500,000 በላይ የሚሆኑ የጌዲዮ ተወላጆች በቂ የምግብ እርዳታ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው ይገኛሉ። ሰሞኑን በይርጋጨፌ ወረዳ አንድ የ65 ዓመት አባት በረሃብ ሕይወታቸዉ ማለፉን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል።
በመንግሥት በኩል የተሰጡት እርዳታዎች በቂ አለመሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የደቡብ ክልል ባለስልጣናት በአካባቢው ያለው ችግር እንደተቀረፈ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቢቆዩም፣ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ግን ችግሩ መኖሩን በማመን አፋጣኝ መልስ እንሰጣለን ብለዋል።