(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010)የጸረ ሽብር ሕጉን እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የመገናኛ ብዙሃን ሕግን አጥንቶ የሚያሻሽል የባለሙያዎች ቡድን ተቋቋመ። ታዋቂ የሕግ ባለሙያዎችና የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች የሚገኙበት ይህ ቡድን ሕጎቹን ከሃገሪቱ ሕገ መንግስት ፣ከሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጋር በተጣጣመ መንገድ እንዲያሻሽል ሃላፊነት እንደተሰጠውም መረዳት ተችሏል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር መስራችና ፕሬዝዳንት የነበሩት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ፣ታዋቂው የሕግ ጠበቃ አቶ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010) በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በታራሚዎች ላይ ከሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ አራት ምክትል ዳይሬክተሮች በአዳዲስ ተሿሚዎች ተተክተዋል። የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት እንደሚጣስ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። በህግ ቁጥጥር ስር ባሉ ዜጎች ...
Read More »በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከግድያ ሙከራ ጀምሮ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያሴሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው
በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከግድያ ሙከራ ጀምሮ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያሴሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱ ግጭቶችን በማስተባበር እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ በዶ/ር አብይ አህመድና ሌሎችም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ላይ የግድያ ሙከራ ለማድረግ ሲያቀናብሩ ከነበሩት ሰዎች መካከል የተወሰኑት መያዝ መጀመራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓት መቀሌ ከሚገኘው ከቀድሞው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ...
Read More »በአማሮ ወረዳና በጉጂ መሃል ያለው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ታሰማ
በአማሮ ወረዳና በጉጂ መሃል ያለው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ታሰማ (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) አንድ አመት ያስቆጠረዉ ግጭት ሰሞኑን ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በዳኖ፤ ደርባ እና ቲፋቴ ግጭቱ ተባብሶ የሰዎች ህይወት አልፏል። ዳኖ በሚባል ቀበሌ ከብቱን በመጠበቅ ላይ የነበረ ደመቀ ደባሱ የሚባል የ44 ዓመት ጎልማሳ አርሶአደር ወዲያውኑ ሲገደል፣ በቲፋቴና ደርባ ቀበሌዎች ደግሞ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት እኩለ ቀን ጊዜ ...
Read More »በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ጦርነት ቢቆምም ፍጥጫው ግን እንደቀጠለ ነው
በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ጦርነት ቢቆምም ፍጥጫው ግን እንደቀጠለ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን የሱዳን የመከላከያ ሃይል በመተማ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ መሬት ላይ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ በተነሳ ጦርነት ድንበራቸውን ለማስከበር የተሰው አርሶአደሮችና የመከላከያ ሰራዊት ዛአስከሬን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። ጦርነቱ ለጊዜው ቢቆምም ፍጥጫው ግን እንደቀጠለ ነው። የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዘላለም ልጃለም ሱዳኖች ...
Read More »በነቀምት በተነሳ ተቃውሞ የሰዎች ህይወት አለፈ
በነቀምት በተነሳ ተቃውሞ የሰዎች ህይወት አለፈ (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) የነቀምት ከተማ ወጣት ከጠዋት ጀምሮ ሲያሰሙ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ በተነሳ ግጭት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ሰዓት ደርስ ቢያንስ አንድ ሰው ተገድሏል። ወጣቶቹ የቄሮ አስተባባሪ የሆነ አንድ ወጣት አዲስ አበባ ሸራተን አካባቢ ታፍኖ ተወስዷል በሚል ተቃውሞ እንዳስነሱ ታውቋል። ተቃውሞውን ለማብረድ ከወጣቶች ጋር ውይይት ቢደርግም ስምምነት ላይ ሊደረስ እንዳልቻለ የአይን ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የሚወክል መጅሊስ ለማቋቋም ምርጫ የሚያመቻች ገለልተኛ ኮሚቴ ሊቋቋም ነው
ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የሚወክል መጅሊስ ለማቋቋም ምርጫ የሚያመቻች ገለልተኛ ኮሚቴ ሊቋቋም ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ትናንት ማክሰኞ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በቤተመንግስት ውይይት ካደረጉ በሁዋላ፣ የመጅሊሱ አመራር አባላት በተገኙበት ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል ገለልተኛ አካል ለማቋቋም ስምምነት ላይ ተድርሷል። ከሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ አሕመዲን ጀበል እና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ ...
Read More »ከሃላፊነት በተነሱት የእስር ቤት አመራሮች ቦታ በአዳዲስ ሰዎች ተተኩ
ከሃላፊነት በተነሱት የእስር ቤት አመራሮች ቦታ በአዳዲስ ሰዎች ተተኩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በእስር ቤት ህገመንግስቱን በሚጥስ ሁኔታ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጸሙ የነበሩ አመራሮች ተነስተው አዳዲስ አመራሮች መሾማቸውን መንግስት አስታውቋል። ጀማል አባሱ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሾሙ፣ ረዳት ኮሚሽነር ያረጋል አደመ፣ ኮማንደር ወንድሙ ጫላ፣ ኮማንደር ሙላቱ ዓለሙ እና ኮማንደር ደስታ አስመላሽ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ...
Read More »የፕሬዝዳንት ሳልቫኪርን የስልጣን ዘመን በ3 አመታት ለማራዘም እቅድ ወጣ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 26/2010) የደቡብ ሱዳን መንግስት የፕሬዝዳንት ሳልቫኪርን የስልጣን ዘመን በ3 አመታት ለማራዘም እቅድ ማጣቱ ተሰማ። የሳልቫኪርን ስልጣን እስከ 2021 እንዲቆይ ያደርገዋል የተባለው ይህ እቅድ ከወዲሁ ከተቃዋሚዎች ዘንድ ህገ መንግስታዊ አይደለም በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል። አንደ ሀገር ራሷን ከቻለች ትንሽ እድሜን ያስቆጠረችው ደቡብ ሱዳን በተቃራኒ አንጃዎች የተነሳ የርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከገባች ቆይታለች። ይህንን የእርስ በርስ ግጭት ለማስቆምም በተደጋጋሚ የሚደረጉ ስምምነቶች ከዳር ...
Read More »በለውጡ ሂደት እጁን መሰብሰብ ያለበት ሃይል እጁን እንዲሰበስብ ይደረጋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ– ሰኔ 26/2010)በለውጡ ሂደት እጁን መሰብሰብ ያለበት ሃይል እጁን እንዲሰበስብ ይደረጋል ሲሉ በአውስትራሊያ የኢትዮያ አምባሰደር ገለጹ። የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም ኤስ ቢ ኤስ ለተሰኘ ሬዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ እንደገለጹት፡ የትግራይ ህዝብ እየተናገረ ነው። ለውጥ ያስፈልጋል። ህወሀት ውስጥም ለውጥ መደረግ አለበት ብለዋል። ህወህት እየታየ ያለውን ለውጥ ተገንዝቦ በድርጅቱ ውስጥ ተመሳሳይ ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል ...
Read More »