ከሃላፊነት በተነሱት የእስር ቤት አመራሮች ቦታ በአዳዲስ ሰዎች ተተኩ

ከሃላፊነት በተነሱት የእስር ቤት አመራሮች ቦታ በአዳዲስ ሰዎች ተተኩ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በእስር ቤት ህገመንግስቱን በሚጥስ ሁኔታ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጸሙ የነበሩ አመራሮች ተነስተው አዳዲስ አመራሮች መሾማቸውን መንግስት አስታውቋል። ጀማል አባሱ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሾሙ፣ ረዳት ኮሚሽነር ያረጋል አደመ፣ ኮማንደር ወንድሙ ጫላ፣ ኮማንደር ሙላቱ ዓለሙ እና ኮማንደር ደስታ አስመላሽ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተሹመዋል።
በእስር ቤት ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ የነበሩ ባለስልጣናት ምርምራ ተካሂዶባቸው ለፍርድ እንደሚቀርቡ ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል።