በነቀምት በተነሳ ተቃውሞ የሰዎች ህይወት አለፈ

በነቀምት በተነሳ ተቃውሞ የሰዎች ህይወት አለፈ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) የነቀምት ከተማ ወጣት ከጠዋት ጀምሮ ሲያሰሙ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ በተነሳ ግጭት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ሰዓት ደርስ ቢያንስ አንድ ሰው ተገድሏል። ወጣቶቹ የቄሮ አስተባባሪ የሆነ አንድ ወጣት አዲስ አበባ ሸራተን አካባቢ ታፍኖ ተወስዷል በሚል ተቃውሞ እንዳስነሱ ታውቋል። ተቃውሞውን ለማብረድ ከወጣቶች ጋር ውይይት ቢደርግም ስምምነት ላይ ሊደረስ እንዳልቻለ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ወጣቶቹ የትራንስፖርት አገልግሎቱን በማቋረጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች ለመቆም ተገደዋል።