.የኢሳት አማርኛ ዜና

አቶ መለስ ዜናዊ የአፍሪካን የአካባቢ ጉባኤ ለመምራት የሞራል ብቃት የላቸውም ሲሉ አንድ ደቡብ አፍሪካዊት ጸሀፊ ገለጡ

 ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጃኒስ ዊንተር የተባሉት ጸሀፊ ደይሊ መቨሪክ በሚባለው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ባወጡት ጽሁፍ ፣ በደርባን የተካሄደው ኮፕ 17 የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ፣ ድንቅ የተባለ  ስምምነት አድርጓል። የስምምነቱ ዋና ድል ተ ብሎ የተቆጠረው ደግሞ፣ የአካባቢ ጥበቃ ለማካሄድ የተፈቀደው ገንዘብ ነው። መለስ ዜናዊ በጉባኤው ላይ ለአካባቢ ጥበቃ ተብሎ የተመደበው ገንዘብ አዲስ ገንዘብ አለመሆኑን ይልቁንም ከዚህ ቀደም ለእርዳታ ተብሎ ...

Read More »

ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ እነ አንዷለም አራጌ ከቀጠሯቸው በፊት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዘ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ከተመሰረተባቸው 24 ተከሳሾች መካከል አቶ አንዷለም አራጌን ጨምሮ 8 ተከሳሾች ለታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ የተሰጣቸው ቢሆንም፤ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ለታህሳስ 5 ቀን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3 ኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንደደረሳቸው የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቀጠሮ የተከሳሾቹን የ እምነት ክህደት ቃል ከሰማ በሁዋላ ...

Read More »

የመለስ መንግስት ልዩ ሀይል በአኝዋክ ህዝብ ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ 8 ኛ አመት ታስቦ ዋለ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አኝዋክ ጀስቲስ ካውንስልና ጥምረት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በጋራ ባወጡት መግለጫ የመለስ መንግሰት ልዩ ሀይል ከዲሰምበር 13እስከ 15 ባሉት ሶስት ቀናት ውስጥ 424 አኝዋኮችን ገድሏል። ከዚያ በሁዋላ በነበሩት ተከታታይ አመታት በድምሩ 1500 አኝዋኮች መገደላቸውን መግለጫው አመልክቷል። ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው የመለስ መንግስት በጊዜው በአኝዋኮች ላይ የወሰደው እርምጃ ምንክንያቱ የአካባቢውን መሬት፣ ውሀ፣ የተፈጥሮ ጋዝና ማእድናት ለመቆጣጠር ነው። ...

Read More »

“ኢህአዴግ የፖለቲካ ምህዳሩን ባያስተካክልም፤ ሕዝቡ መብቱን ለማስከበር መነሳቱ አይቀርም፡፡ ያኔ ተጠያቂ እኛና ሕዝቡ ሳንሆን፤ ራሱ ኢህአዴግ ነው የሚሆነው” ሲሉ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስጠነቀቁ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዶክተር ነጋሶ ይህን ያሉት ሰሞኑን አንድነት ፓርቲን ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ይመሩ ዘንድ በአብላጫ ድምጽ መመረጣቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው። “የሰጣችሁኝ ኃላፊነት ከባድ እንደሆነ ሁላችንም የምንገነዘበው ነው” ያሉት የቀድሞው የ አገሪቱ ፕሬዚዳንት፤ “በተለይም የፖለቲካ ምሕዳሩ ባልተስተካከለበት ሁኔታ አንድን ፓርቲ መምራት በጣም ከባድ ነው”ብለዋል። “ሆኖም ግን ፈቃደኝነቱ እንዲሁም የሚያስፈልገውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ በመሆን በቆራጥነት ...

Read More »

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ኃላፊዎች፤ የፌዴራል ፍርድ ቤት አያዘንም ማለታቸውን ሪፖርተር ዘገበ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመሠረተው የፍትሐ ብሔር ክስ- ማስረጃ እንዲልኩ ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የደረሳቸው የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአውሳ ዞን መስተዳድርና የሚሌ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፦ ‹‹ክሱ መታየት ያለበት በክልላችን በመሆኑ ኃላፊዎችንም ሆነ የምርመራ መዝገቡን ለመላክ ፈቃደኛ አይደለንም›› ማለታቸውን ፌዴራል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስታወቋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ...

Read More »

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ በገሊላ ወረዳ ሰሜን አሪ በሚባል ቦታ የመንግስት ፖሊሶች አንድ ሰው በመግደል ዝርፊያ መፈፀማቸው ተዘገበ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፖሊሶቹ ዝርፊያ ስለመፈፀማቸው ምስክርነት የሰጡ 18 የ አካባቢው ነዋሪዎችም እንዲታሰሩ ተደረገ። እንደ ፍኖተ-ነፃነት ዘገባ፤ ፖሊሶቹ ሕዳር 12 ቀን 2004 ዓ.ም በግብርና ሙያ በሚተዳደርና አቶ ለጊዜ ወርቅማ በተባለ የገሊላ ወረዳ ነዋሪ ላይ ዝርፊያ ሲፈጽም ከፍተኛ የ አካል ጉዳት አድርሰውበታል። ከማሳው ቡና ለቅሞ ወደ ቤቱ እየሄደ ሳለ በወረዳው በሚገኙ የመንግሥት ፖሊሶች ዝርፊያና ከፍ ያለ ጉዳት የደረሰበት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ቡና ገዥ የሆኑ አስር የውጭ አገር ኩባንያዎችና ማህበራት በብትን መልክ የሚቀርበውን የኢትዮጵያን ቡና እንደማይገዙ አሳወቁ

ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ቡና በብትን መልክ ብቻ ለማዕከላዊ ገበያ ይቅረብ” የሚለው መመሪያ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቡና ገዥ የሆኑ አስር የውጭ አገር ኩባንያዎችና ማህበራት በብትን መልክ የሚቀርበውን የኢትዮጵያን ቡና እንደማይገዙ አሳወቁ። ገዥ በማጣት አጣብቂኝ ውስጥ የወደቁትና መመሪያው እንዲቀየር ለንግድ ሚኒስቴር ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ የተደረገባቸው ቡና ላኪዎች፤ ለአቶ መለስ ዜናዊ አቤቱታ ለማሰማት እየተዘጋጁ ነው። የኢትዮጵያ ቡና ...

Read More »

የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲውን አመራሮች መረጠ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላለፉት ሁለት ቀናት  ጠቅላላ ጉባኤውን ካደረገ በሁዋላ፣ የፓርቲውን ሊቀመንበር፣ የብሄራዊ ምክር ቤት እና የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላትን መርጧል። የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን በሊቀመንበርነት የመረጠው ጉባኤ፣ ለብሄራዊ ምክር ቤት ከመረጣቸው 40 ሰዎች መካከል በእስር ላይ የሚገኘውን አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ፣ ዶ/ር ንጋት አስፋው፣ አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ ተመስገን ...

Read More »

ሱዳንና ኢትዮጵያ የሁለቱ አገራት ተቃዋሚዎችን በየአገሮቻቸው ላለማስተናገድና አሳልፎ ለመስጠትም ተስማሙ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው አገራቱ በየአገሮቻቸው ያሉ አማጽያንን ለማስወጣትና አሳልፎ ለመስጠት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የሁለቱ አገራት የድንበር ጉዳይ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተገኙት የሲናር ክፍለሀገር ገዢ የሆኑት አህመድ አባስ ፣ ሁለቱ አገሮች በድንበር አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን አሳልፈው ለመስጠት መስማማታቸውን አረጋግጠዋል። የመለስ መንግስት የሱዳንን መንግስት ላለማበሳጨት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረገ መሆኑን የዘገበው ሱዳን ትሪቢዩን፣ በቅርቡ ...

Read More »

በዳንግላ ወረዳ አንድ በግንቦት7 አባልነት የተጠረጠረ መምህር ታፍኖ ተወሰደ

ታህሳስ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በዳንግላ ወረዳ ነዋሪ የሆነው መምህር ምህረት በደህንነት ሀይሎች ታፍኖ የተወሰደው ከሳምንት በፊት ነው። የኢሳት የአማራ ክልል ዘጋቢ እንደገለጠው ማንነታቸው ያልታወቁ ራሳቸውን የደህንነት ሰራተኞች አድርገው ያስተዋወቁ ሲቪል የለበሱ ሰዎች መምህሩን ከክፍል አስወጥተው ወደ አልታወቀ ስፍራ ወስደውታል። መምህሩ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የማእከላዊ እስር ቤት ሳይወሰድ እንዳልቀረ ግምቶች መኖራቸውንም ገልጧል። በክልሉ መንግስትን ...

Read More »