የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአምስተርዳም ከተማ የተጠራው የኢህአዴግ ስብሰባ ከቀኑ 7፡ሰ ዓት ተኩል ላይ እንደሚጀመር መረጃ የደረሳቸው ኢትዮጵያውያን፤ ልዩ ልዩ መፈክሮችንና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በስፍራው የተገኙት፤ ከስብሰባው መጀመር 30 ደቂቃ ቀድመው ነበር። “የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!ጋዜጠኞች ይፈቱ! የመሬት ንጥቂያ በአስቸኳይ ይቁም! ሞት ለዜናዊ! መለስና ግብረ አበሮቹ ለፍርድ ይቅረቡ! እና ምዕራባውያን መለስን መደገፍ አቁሙ!”የሚሉት፤ ፤በሰልፈኞቹ ከተስተጋቡት መፈክሮች ጥቂቶቹ ናቸው። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ
Ethiopian Orthodox religious leaders Press conference February 2012
Read More »ኢብሳ አስፋው ኦሮሞንና አማራን ለማጋጨት እየሞከረ ነው ተባለ
የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቃሊቲ እስር ቤት የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነውን አንዱአለም አራጌን በመደብደብ ጉዳት ያደረሰው የእድሜ ልክ ፍርደኛው ኢብሳ አስፋው ፣ አንዱአለም ኦሮሞነቴን ጠቅሶ ስለሰደበኝ ነው የደበደብኩት በማለት የኦሮሞ ተወላጅ እስረኞችን ለማነሳሳት ሙከራ አድርጎ እንዳልተሳካለት የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ለኢሳት ገልጠዋል። ኢብሳ አንዱአለምን ከደበደበ በሁዋላ ሌላው የአንድነት የአመራር አባል ወደ ሆነው አቶ ናትናኤል መኮንን ...
Read More »በሶማሊያ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የቦንብ ጥቃት ደረሰ
የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያና የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ወታደሮች በጋራ በመግፋት ከአልሸባብ አማፅያን ዉጊያ ሳይገጥማቸዉ ከሞቃዲሾ በስተደቡብ በተቆጣጠሯት የባይዶዋ ከተማ ዉስጥ የተቀበረ ቦንብ ፈንድቶ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጥቃት መድረሱን ሸበሌ ሚዲያ ኔትወርክን በመጥቀስ ኦል አፍሪካን ኒዉስ ዘግቧል። አደጋዉ የደረሰው የመንግስት ወታደሮቹ በተቆጣጠሯት ከተማ ዉስጥ ያለዉን የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋጋት በተሽከርካሪ ሆነዉ በሚዘዋወሩበት ወቅት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በጥቃቱ በሰዉና በንብረት ...
Read More »በኦጋዴን ክልል በመፈፀም ላይ ባለው የጅምላ ግድያ የመለስ መንግሰት ላይ ጫና መደረግ አለበት ተባለ
የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት በኦጋዴን ክልል በመፈፀም ላይ ያለዉን የጅምላ ግድያ በማዉገዝ አለምአቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች በመለስ መንግሰት ላይ ጫና ማድረግ አለባቸው ተባለ አፍሪካን ራይትስ ሞኒተር የተባለዉ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሰት በኦጋዴን ሶማሌ ክልል ዉስጥ ስልታዊ በሆነ መንገድ ሰላማዊ ዜጎችን ይገድላል፤ ድብደባና ሰቆቃ ያደርሳል፤ የአስገድዶ መድፈር እንዲካሄድ ያደርጋል፤ መንደሮችን ያቃጥላል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢዉ ዜጎችን ያፈናቅላል፤ የንግድና የረዴኤት ድርጅቶችን ...
Read More »በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ከፊል አርብቶ አደር የሆኑ በመፈናቀል ላይ መሆናቸዉን በመግለፅ ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል መግለጫ አወጣ
የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ከፊል አርብቶ አደር የሆኑ ዜጎች በኢትዮጵያ መንግስት በሃይል ከይዞታቸዉ በመፈናቀል ላይ መሆናቸዉን በመግለፅ ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል መግለጫ አወጣ በጊቤ 3 የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ግንባታ ስም የኢትዮጵያ መንግሰት በደቡብ ክልል ኦሞ ሸለቆ የጀመረዉ ድሃ አርሶ አደሮችን ከይዞታቸዉ የማፈናቀል ተግባር አካባቢዉን የሸንኮራ አገዳና የዕፅዋት ነዳጅ ተክል ለሚያመርቱ የአዉሮፓና የሕንድ ከበርቴዎች ለመስጠት ተጠናክሮ መቀጠሉን አለምአቀፍ ...
Read More »መንግስት 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ገዛሁ አለ
የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ራስ ምታት የሆነበት መንግስት፣ ገበያውን ለማረጋጋት 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ገዝቻለሁ አለ ከጥር እስከ ሚያዚያ በመላው አገሪቱ የእህል ዋጋ እንደሚቀንስ ቢታወቅም፣ በዘንድሮው አመት ግን ይህ ሲሆን አልታየም። የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ያሰጋው መንግስት ገበያውን ለማረጋጋት 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ገዝቶ በማስጋባት ገበያውን ለማረጋጋት እየሞከረ መሆኑን ገልጧል። ከአንድ ...
Read More »በጋሞጎፋ ዞን ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ 7 ሰዎች ራሳቸውን አጠፉ
የካቲት 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአርባ ምንጭ ዘጋቢያችን እንደገለጠው በአለፉት 2 ወራት ብቻ ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ 7 አርሶአደሮች ራሳቸውን ሰቅለው፣ ወደ ገደል ወርውረው ወይም በአካባቢ ምልሺያ በደረሰባቸው ድብደባ ሞተዋል። በ1997 ዓም ያራ የተባለው ተራድኦ ድርጅት አቶ መለስ ዜናዊ በአገራቸው ላካሄዱት የአረንጓዴ አብዮት እንቅስቃሴ እውቅና ለመስጠት በሚል 200 ሺ ዶላር ሸልማት መስጠቱ ይታወቃል። በጊዜው የኖርዌይ አፍተን ፖስተን የተባለው ጋዜጣ ...
Read More »በለንደን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
የካቲት 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን አስተባባሪነት በለንደን የሶማሊያን ችግር ለመፍታት በሚል አጀንዳ የአንድ ቀን ጉባኤ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ ከ40 ያላነሱ አገራት መንግስታት ተገኝተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ በጉባኤው ላይ መጠራታቸውን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የሶማሊያ ተወላጆች በበኩላቸው የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ ተቃውሞአቸውን ገልጠዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate ...
Read More »መንግስት መምህራን ያቀረቡት የደሞዝ ጥያቄ ለመመለስ ቃል ገባ
የካቲት 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙት ትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በቅርቡም በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በኩል የቀረበው የደሞዝ ማስተካከያ ጥያቄ አግባብነት ያለው በመሆኑ የአገሪቷን የመክፈል አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት በጥቂት ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንሰጣለን ብለዋል። የተለጣፊው የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮሐንስ ባንቲ የመምህራን የደረጃ እና የተፈላጊ ችሎታ እድገት ጉዳይ ...
Read More »