በኦጋዴን ክልል በመፈፀም ላይ ባለው የጅምላ ግድያ የመለስ መንግሰት ላይ ጫና መደረግ አለበት ተባለ

የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት በኦጋዴን ክልል በመፈፀም ላይ ያለዉን የጅምላ ግድያ በማዉገዝ አለምአቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች በመለስ መንግሰት ላይ ጫና ማድረግ አለባቸው ተባለ

አፍሪካን ራይትስ ሞኒተር የተባለዉ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሰት በኦጋዴን ሶማሌ ክልል ዉስጥ ስልታዊ በሆነ መንገድ ሰላማዊ ዜጎችን ይገድላል፤ ድብደባና ሰቆቃ ያደርሳል፤ የአስገድዶ መድፈር እንዲካሄድ ያደርጋል፤ መንደሮችን ያቃጥላል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢዉ ዜጎችን ያፈናቅላል፤ የንግድና የረዴኤት ድርጅቶችን እንቅስቃሴ በመገደብ ሰብአዊ ሁኔታዎችን ያባብሳል በማለት ገልጿል።

በቅርቡ በደገሀቡር አካባቢ የኢትዮጵያ መንግሰት ወታደሮችና ልዩ ፖሊስ ተብሎ የሚጠራው ሚሊሺያ 16 ሰዎችን መግደሉን፤ ከ20 በላይ የሆኑትን ማቁሰሉንና አንድ መቶ የሚሆኑ ሰዎችን በማሰር ወዳልታወቀ አካባቢ እንደወሰዳቸዉ ድርጅቱ አስታዉቋል።

ጉና ጋዳ በተባለዉ አካባቢ አብሽር እና ማድሄድ በተባሉ መንደሮች የተገደሉ የ17 ሰዎችን የስም ዝርዝር ይፋ ያደረገዉ አፍሪካን ራይትስ ሞኒተር፤ የመንግስታቱ ድርጅትና ለጋሽ አገሮች በተለይም የአዉሮፓ ህብረት፤ ዩናይትድ ስቴትስ እና ብሪታኒያ  ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ርዳታ ከአገሪቱ የሰብአዊ መብት አያያዝ አንፃር ሊመለከቱት እንደሚገባና የመለስ መንግሰት በኦጋዴን ህዝብ ላይ የፈፀመዉ ወንጀል ሊመረመር እንዲችል ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide