በሶማሊያ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የቦንብ ጥቃት ደረሰ

የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያና የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ወታደሮች በጋራ በመግፋት ከአልሸባብ አማፅያን ዉጊያ ሳይገጥማቸዉ ከሞቃዲሾ በስተደቡብ በተቆጣጠሯት የባይዶዋ ከተማ ዉስጥ የተቀበረ ቦንብ ፈንድቶ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጥቃት መድረሱን ሸበሌ ሚዲያ ኔትወርክን በመጥቀስ ኦል አፍሪካን ኒዉስ ዘግቧል።

አደጋዉ የደረሰው የመንግስት ወታደሮቹ በተቆጣጠሯት ከተማ ዉስጥ ያለዉን የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋጋት በተሽከርካሪ ሆነዉ በሚዘዋወሩበት ወቅት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በጥቃቱ በሰዉና በንብረት ላይ ስለደረሰዉ ጉዳት በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።

ይሁንና አደጋዉን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በአካባቢዉ በሚንቀሳቀሱ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ቁጥራቸዉ በትክክል ያልታወቀ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ ወታደሮቹ በፍንዳታዉ አካባቢ የሚደረገዉን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መዝጋታቸዉን ለማወቅ ተችሏል።

በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ይህ የቦንብ ጥቃት የደረሰዉ በሶማሊያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመነጋገር ከ40 ያላነሱ መሪዎችና ድርጅቶች በለንደን አለምአቀፍ ስብሰባ እያካሄዱ ባለበት ጊዜ ነው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide

ጥቃቱን በተመለከተ የአማፅያኑ ቡድን አልሸባብ የገለፀዉ ነገር እንደሌለ የመረጃ ምንጩ በተጨማሪ አስታዉቋል።