.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአረብ አገራት በሚኖሩኢትዮጵያውያን ግፍ እየተፈፀመባቸው ነው

መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በአረብ አገራት በሚኖሩ ሴት ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ግፍ ህሊና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ መምጣቱ በሚነገርበት ወቅት የሊባኖስ መንግስት ግፍ በሚፈጽሙት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ በኢትዮጵያዊቱ የቤት ሰራተኛ ላይ በአደባባይ የተወሰደውን እርምጃ አውግዞ፣ ጉዳዩ ተጣርቶ እርምጃ እንደሚወሰድ የማስታወቂያ ሚኒሰትሩ ተናግረዋል። የሊባኖስ መንግስት ድርጊቱን ያወገዘው ኤል ቢሲ የተባለ የሊባኖስ ቴሌቪዥን አንድ ሊባኖሳዊ ...

Read More »

ጆሴፍ ኮኒን ለማደን የተሰራጨው ፊልም ኢንተርኔትን አጨናነቀ

መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የህፃናት ቀበኛ የሆነውን ጆሴፍ ኮኒን ለማደን የተሰራጨው ፊልም በአራት ቀናት ብቻ በ60 ሚሊዮን ጎብኝዎች በመታየት የኢንተርኔት መስመሮችን ማጨናነቁ ተዘገበ ።  ሰሞኑን የተሰራጨው ይህ ፊልም እንደሚያስረዳው፤ የኡጋንዳው የጎሬላ ተዋጊና የ”ጌታ ተጋዳይ ሠራዊት” (ሎርድ’ስ ሬዚዝታንስ አርሚ) መሪ ጆሴፍ ኮኒ፤ በኡጋንዳ ከ 60 ሺህ በላይ ህፃናትን ጠልፏል።  ኮኒን ለማደን በዩቲዩብ የተሰራጨውና በጥቂት ቀናት ወደ 60 ሚሊዮን ...

Read More »

ሰመጉ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና መታሰራቸውን አስታወቀ

የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲፈጸሙ የነበሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በማጋለጥ አለማቀፍ እውቅና ያተረፈው ቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) ወይም አሁን ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ሰመጉ) እየተባለ የሚጠራው ድርጅት ባወጣው  35ኛ መደበኛ ጉባኤ በአገሪቱ ውስጥ ባለፈው አንድ አመት የታየቱን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አውጥቷል። በሪፖርቱ መሰረት በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በቆንሴ አርኪ ገበሬ ...

Read More »

ሙስሊሞች ወደ ሁዋላ መመለስ የለም አሉ

የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው የጁማ ሶላት ስግደት ላይ የተሰበሰቡ ከ300-400 ሺ የሚጠጉ ሙስሊሞች መንግስት ከእንግዲህ መሰብሰብ አትችሉም ቢላቸውም፣ እነርሱ ግን ወደ ሁዋላ እንደማይሉና በጥያቄያቸው እንደሚገፉበት ገልጠዋል። ዛሬ የኮሚቴው አባላት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉትን ውይይት ለህዝቡ የፋ አድርገዋል። መንግስት ጥያቄዎችን በአግባቡ አለመመለሱንም እያንዳንዱ በአወልያ የተገኘው ሙስሊም ተረድቷል። መንግስት ከእንግዲህ ወዲያ በአወልያ መስጂድ የሚደረገው መሰባሰብ እንዳይቀጥል ፣ ቢቀጥል የኮሚቴው ...

Read More »

የአካል ጉዳተኞች የኤች አይ ቪ ኤድስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ተገለፀ

የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ የሚደረጉ ዘመቻዎችና ቅስቀሳዎችን ለማካሄድ በስራ ላይ የሚዉሉት የመገናኛ ስልቶች የአካል ጉዳተኞችን ግምት ዉስጥ ያላስገቡ በመሆናቸዉ በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ለበሽታዉ ያላቸዉ ግንዛቤ ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ ከበሽታዉ ጋር የተያያዙ አግልግሎቶችን ሊያገኙ እንደማይችሉ አንድ የረድኤት ድርጅት የስራ ሃላፊ ገለፁ።  ሊያ ሰሎሞን በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞችና ልማት ማእከል the Ethiopian Centre for Disability and ...

Read More »

ሼክ አላሙዲን በአፍሪካ አንደኛ ባለሀብት ተባሉ

የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሚገኙ የወርቅ ጉድጓዶችን እንዲሁም የነዳጅ ማውጫ ኩባንያ ባለቤት የሆኑት ሼክ አላሙዲን በአፍሪካ አንደኛ ባለሀብት ተባሉ የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑት ቢሊየነሩ ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ይህን ማእረግ ያገኙት ናይጄሪያዊውን ቢሊየነር አሊኮ ዳጎቴን በመተካት ነው። የሼኩ አዲሱ የሀብት መጠን 12 ቢሊዮን 500 ሚሊየን ደርሷል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ታላለቅ የንግድ ተቋማትን በርካሽ ዋጋ በመግዛት የሚወነጀሉት ሼክ አለሙዲን፣ ሚድሮክ ...

Read More »

የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ግራ ማጋባቱን ቀጥሎአል

የካቲት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ  በአ ገሪቱ የታየውን የገንዘብ ግሽበት ወደ አንድ አሀዝ እናወርዳለን ብለው በፓርላማ በተናገሩ በሳምንታት ውስጥ የምግብ ዋጋ በእጅጉ መጨመሩ ህዝቡን እያነጋገረ ነው። በአማራ ክልል ጤፍ እስከ 1400 ብር በመሸጥ ላይ መሆኑ  ህዝቡ በተለይም የመንግስት ሰራተኛው ምን እየሆነ ነው ማለት ጀምረዋል። የጤፍ መጨመር ሌሎች ምርቶችንም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምሩ አድርጓል። የባህርዳር ዘጋቢያችን እንዳለው የአማራ ...

Read More »

በጋምቤላ አለመረጋጋቱ እንደቀጠለ ነው

የካቲት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጋምቤላው ዘጋቢያችን እንደገለጠው ሰሞኑን ኤለያ በሚባለው መስመር ታጣቂዎች የአንድ የግለሰብ እርሻን ሲጠብቁ በነበሩ ሶስት ዘበኞችና የእርሻው ባለቤት ላይ ጥቃት ከፍተው 3ቱ የአኝዋክ ተወላጅ የሆኑት ዘበኞች ወዲያው ሲገደሉ የእርሻው ባለቤት የሆኑት ሴት ባለሀብት ደግሞ በጸና ቆስለው ወደ አዲስ አበባ ተወስደው በመታከም ላይ ናቸው። ታጣቂዎች የሚሰነዝሩት ጥቃት እያየለ በመጣበት በአሁኑ ጊዜ የክልሉ ባለስልጣናትም ሆኑ የአላሙዲ ንብረት ...

Read More »

መንግስት ለሙስሊሙ ጥያቄ መልስ አለመስጠቱ ተቃውሞው እንዲቀጥል ያደርገዋል ተባለ

የካቲት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላቀረበው ጥያቄ መንግስት መልስ አለመስጠቱ ተቃውሞው እንዲቀጥል እንሚያደርገው አቶ አብዩ ያሲን ተናገሩ የሉቅማን ኢትዮጵያውያን ቤልጂየማውያን ሙስሊም ማህበር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አብየ ያሲን ለኢሳት እንደገለጡት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላቀረባቸው 3 ጥያቄዎች ለአንዱም ተገቢውን መልስ አልሰጠም። “ተቃውሞው እንዳይካሄድ መንግስት አስጠንቅቋል  ከዚህ በሁዋላ የአወልያ ተቃውሞ የሚቀጥል ይመስልዎታል ለተባሉት ፣ አቶ አብዩ ተቃውሞው በመንግስት ያልተጀመረ በመሆኑ ...

Read More »

ስዊድናውያን ጋዜጠኞቹን በህገ-ወጥ መንገድ እንዲገቡ የላከው ተቋም ይከሰስ ተባለ

የካቲት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ስዊድናውያን ጋዜጠኞቹን ወደ አገራችን በህገ-ወጥ መንገድ እንዲገቡ የላከው ተቋም ቢከሰስ ፤በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሊቀጣ ይችላል”ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና የኮሙኒኬሽን ዲን ተናገሩ። በህወሀት አባልነት የሚጠቀሱትና  በዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነትና የኮሙኒኬሽን ፋኩሊቲ ዲን የሆኑት  ዶክተር ገብረመድህን ስምዖን ይህን ያሉት፤በጉዳዩ ዙሪያ ለመንግስት ጋዜጠኞች በሰጡት አስተያዬት ነው። ስዊድናውያኑን ጋዜጠኞች ለማስፈታት እየተደረገ ያለው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መፍትሔ ወደሚያገኝበት ደረጃ ላይ ...

Read More »