.የኢሳት አማርኛ ዜና

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2012 የፔን የፅሁፍ ነፃነት አለምአቀፍ ተሸላሚ ሆነ

ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኒዉ ዮርክ ከተማ የሚገኘዉ የፔን አሜሪካ ማእከል በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነትና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲከበር በፅናት የሚታገለዉና ካለፈዉ መስከረም ወር 2011 ጀምሮ በመለስ መንግሰት በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘዉ ጋዜጠኛና ፀሃፊ እስክንድር ነጋ የዘንድሮዉ የ2012 አለምአቀፍ የባርባራ ጎልድ-ስሚዝ ተሸላሚ  እንዲሆን ወሰነ።  የፀረ ሽብር ህጉ መንግሰት “ሽብርተኛ” በማለት የሚገምታቸዉን ቡድኖች “ያበረታታሉ” ወይንም “ የሞራል ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በየወሩ 45ሺህ የቤት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ እንደሚልክ ተገለፀ

  ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳዑዲ አረቢያ/ ጄዳ  የኢትዮጵያ ኤምባሲ  የሚገኝ የዉስጥ አዋቂ ምንጭን በመጥቀስ በቀረበዉ በዚሁ መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ሠራተኞቹን ለመላክ የሚያስችሏትን መሰናዶዎች በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል። አሻ-አርክ አል አዉሳት ጋዜጣ እንደገለፀዉ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኬንያን ጨምሮ ከአራት መንግስታት ጋር የቤት ሰራተኞችን ለመመልመል የጀመረዉ ስምምነት አጥጋቢ ባለመሆኑ ዉለታዉን ካቋረጠ በሁዋላ ኢትዮጵያዉያን የቤት ሰራተኞችን ለመቅጠር ያለዉ ፍላጎት ...

Read More »

በደባርቅ ወረዳ የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ 9 መምህራን ደሞዛቸውን ተቀጡ

ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ መምህራን እንደተናገሩት መንግስት የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርግ ለማስገደድ የስራ ማቆም አድማ አድርገው እንደነበረ አስታውሰው፣ ይሁን እንጅ  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መንግስት የበቀል እርምጃ እየወሰደባቸው ነው። እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል መምህርት ሀያት ሙሀመድ፣ መምህር ግርማ ሀይሌ፣ ደገፋው ዘላለም፣ አገር በለው ፣ ደስታ ገብረ እግዚአብሄር፣ አየለ መልካሙ እና ሌሎች ሶስት መምህራን የወር ደሞዛቸውን ተቀጥተዋል። ሰሞኑን ...

Read More »

የአልሸባብ ተዋጊዎች ሶማሊያን ለቀው ወደ ፑንትላንድ እየተጓዙ ነው ተባለ

ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው ተዋጊዎቹ ወደ ፑንትላንድ የተጓዙት ከኢትዮጵያ ፣ ከኬንያና ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይል የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ለመከላከልና ራሳቸውን ለማደራጀት ነው። አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእየ አቅጣጫው በሚሰነዘርበት ጥቃት እየተዳከመ መምጣቱ ይነገራል። የፑንትላንድ መንግስት የአልሸባብ ወደ ግዛቱ መግባት እንዳሳሰበው እየገለጠ ነው። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ታዋጊዎቹ ወደ ፑንትላንድ ማምራታቸው በየመን ከሚገኘው የአልቃይዳ ሀይል ጋር በቀላሉ ለመገናኘት ...

Read More »

የአማራ ተወላጆች ከቤንች ማጂ ዞን እንዲወጡ ማዘዛቸው ኢህአዴግ ደቡቡንና አማራውን ለማጋጨት የቀየሰው ሴራ ነው ተባለ

  ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአማራ ተወላጆች ከቤንች ማጂ ዞን እንዲወጡ ማዘዛቸው ኢህአዴግ ደቡቡንና አማራውን ለማጋጨት የቀየሰው ሴራ ነው ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ ገለጡ የአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባልና የደቡብ ተወካይ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለኢሳት እንደተናገሩት በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተጻፈው መመሪያ አንድን ብሄር ነጥሎ ለማጥቃት ያለመ ነው ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ እንደነበረው ...

Read More »

እስክንድር ነጋና አንዱ አለም አራጌ የቪዲዮ ማስረጃቸውን አቀረቡ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቃቢ ህግ በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አንዱአለም አራጌን ሆን ብሎ ለመወንጀል የቪዲዮ ማስረጃዎችን ቆራርጦ አቅርቧል በማለት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ የቆዩት እስረኞች ዛሬ ሙሉ ቪዲዮ በማቅርብ እንዲታይላቸው አድርገዋል። አቃቢ ህግ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት አቶ አንዱአለም አራጌ የመለስ መንግስት እንዲወገድ የአመጽ ጥሪ መቀስቀሳቸውን ያሳይልኛል ያለውን ቪዲዮ ቀደም ብሎ ...

Read More »

የሰሜን ሱዳን ፓርላማ አገሪቱ ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት ሙሉ ዝግጅት እንድታደርግ ወሰነ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሰሜን ሱዳን ፓርላማ አገሪቱ ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት ሙሉ ዝግጅት እንድታደርግ ወሰነ የኢትዮጵያ ጦር እጣ ፋንታ አልታወቀም ደቡብ ሱዳን ሰሞኑን ሄግሊግ እየተባለ የሚጠራውን ዋነኛ የነዳጅ ጉድጓዶችን ከሰሜን ሱዳን ማስለቀቁዋን፣ የሱዳን መንግስት ጦርም  ተሽንፎ አካባቢውን መልቀቁን የመገናኛ ብዙሀን ሲዘገቡ ሰንብተዋል። የሱዳን የመካላከያ ሚኒስትር የሆኑት አብደል ራሂም ሁሴን ለፓርላማው ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ ነው አገሪቱ ለሙሉ ጦርነት ...

Read More »

የኬንያው ምክትል አፈጉባኤ በኢትዮጵያው አምባሳደር ላይ ተሳለቁ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፋራህ ማሊም የተባሉት የኬንያ ፓርላማ ምክትል አፈጉባኤ ምጸታዊ ጽሁፋቸውን ያሰፈሩት በኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ላይ ነው። አፈ ጉበኤ ፋራህ ለትችታቸው መነሻ የሆናቸውም በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሸምሰዲን ሮቤል እርሳቸው የሰጡትን ቃለምልልስ የሚተች ጽሁፍ በማውጣታቸው ነው። ምክትል አፈ ጉባኤው በጽሁፋቸው ” ኬንያ በአካባቢው ጠንካራ የሆነ ዲሞክራሲ ያላት አገር ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ተቃራኒውን ናት ” ካሉ ...

Read More »

ሜትረ አርቲስ አፈወርቅ ተክሌ አረፉ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው ሰአሊ ሜትረ አርቲስ አፈወርቅ ተክሌ በተወለዱ በ80 አመታቸው ማረፋቸውን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። በሸዋ ክፍለ ሀገር አንኮበር ወረዳ የተወለዱት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፣ በስእሉ አለም ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅ ልጆች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። አርቲስቱ በእኤአ በ1947 ኢንጂነሪነንግ ለመማር ወደ እንግሊዝ አገር  ቢላኩም ፣ በመጨረሻ ግን ስነ ስእል አጥንተው መመለሳቸው ታውቋል። አርቲስት አፈወርቅ በጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ህይወታቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ ነው

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በፍትህ ፣ በመልካም አስተዳዳር እጦት ና በችጋር ህይወታቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ ነው የኢሳት የክልል ወኪሎች አጠናክረው የላኩት መረጃ እንደሚያሳየው በተለይ በደቡብ ክልል ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ፣ በመልካም አስተዳዳር እጦትና የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም የተሳናቸው ዜጎች ራሳቸውን ማጥፋት እንዳማራጭ አድርገው እየተጠቀሙ ነው። በያዝነው ወር ብቻ በዳውሮ ዞን ውስጥ ሁለት አርሶአደሮች የማዳበሪያ እዳ መክፈል ...

Read More »