ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቅድስ ሀብት በላቸው ከአውስትራሊያ እንደዘገበው ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ትናንት ከቤኒን አቻው ጋር “ኮቶኖ” ላይ የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት በመለያየቱ ለተከታዩ ዙር ማለፉን አረጋገጠ። የኢትዮጵያ ቡድን ከማጥቃት ይልቅ በመከላከል ላይ መወሰኑ ብቻ ሳይሆን በ ዕለቱ እየጣለ የነበረው ዝናብም ጭምር የሁለቱንም ቡድኖች የጨዋታ እንቅስቃሴ ገድቦት ነበር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ በረከት ስምኦን ማንኛውንም ጣቢያ ልንታገስ እንችላለን በኢሳት ጉዳይ ግን አንደራደርም አሉ
The disagreement between Ethiopian Government and the regional satellite carrier- ArabSat- doesn’t appear to be over yet. There has been an ongoing accusation by ArabSat that strong jamming signals emanating from Ethiopia to stymie satellite transmissions of ESAT and Eritrean Government’s satellite broadcast are disturbing a whole set of other transmissions in the region. As a result ArabSat was forced to take the transmissions in the middle of the controversy off air.
Read More »በግፍ እስር ላይ የሚገኙት እነ አንዱአለም አራጌ የረሀብ አድማ እያደረጉ ነው
ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆነው ናትናኤል መኮንን፣ ክንፈ ሚካኤል በረደድ ( አቤ ቀስቶ) ፤ ምትኩ ዳምጤ እና ሌሎችም እስረኞች የረሀብ አድማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እስረኞች ምንም አይነት ምግብ አልቀመሱም፤ ...
Read More »የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የያዘ አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ገጠመው
ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 917 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድንን ይዞ ወደ ቤኒን ትላንት ሰኔ 8፣ 2004 ዓም የሁለት ሰዓታት ጉዞ ካደረገ በኃላ በአውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ምክንያት ተመልሶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ለማረፍ መገደዱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ የእግር ኳስ ቡድኑ በነገው ዕለት ለ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቤኒን ብሔራዊ ቡድን ጋር ላለበት ጨዋታ ...
Read More »ሲፒጄ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣውን አዲስ የቴልኮም አጠቃቀም አዋጅ አወገዘ
ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው አዲሱ የቴሌኮሚነኬሽን አዋጅ መንግስት ማንኛውንም የግንኙነት መንገዶች ሁሉ ለመቆጣጠር መፈለጉን የሚያሳይ ነው በማለት አውግዟል። የሲፒጄው የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ቶም ሮድስ የኢትዮጵያ መንግስት በኢንተርኔት በሚተላለፉት ነጻ መረጃዎች እና ጠንካራ ዘገባዎች ስጋት ላይ እየወደቀ መምጣቱን ተናግረዋል። ጋዜጠኞች ከመንግስት ክትትልና አፈና ለማምለጥ ሲሉ የሚጠቀሙባቸውን የመገናኛ ዘዴዎች ...
Read More »“እውነቱ ይህ ነው” በሚል ርዕስ የሕዝበ ሙስሊሙ ወቅታዊ ጥያቄዎች መፍትሔ ለማፈላለግ የተመረጠው ኮሚቴ መጽሐፉ አሳተመ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለሕዝበ ሙስሊሙ ወቅታዊ ጥያቄዎች መፍትሔ ለማፈላለግ የተመረጠው ኮሚቴ ያሳለፋቸውን ሒደቶችና ለመንግስትና ለባለድርሻ አካላት ያስገባቸው ደብዳቤዎች ያሰባሰበ 103 ያህል ገጽ የያዘና “እውነቱ ይህ ነው” የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ ዛሬ ለሕዝብ ይፋ ሆነ፡፡ የሕዝበሙስሊሙን ወቅታዊ ጥያቄዎች መፍትሔ ለማፈላለግ የተመረጠው ኮሚቴ ባሳተመው በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲመለሱ ኮሚቴው የሄደባቸውን መንገዶች፣የተጻጻፋቸውን ደብዳቤዎች ...
Read More »እነ አቶ ስብሀት ነጋ በተሳተፉበት የህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ስብሰባ ጋዜጠኞች እንዳይገኙ ተከለከሉ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የኣለም አቀፍ የሠላምና ልማት ኢንስቲትዩት ከፍሬድሪክ ኤበርት ፈውንዴሸን ጋር በመተባበር ትናንት (ጁን 14/2012) በሒልተን ሆቴል በጠራው አህጉር አቀፍ የምክክር ስብሰባ ላይ ሕገወጥ የገንዘብ ፍሰት ዓለም አቀፋዊ ችግር ቢሆንም ከሰሃራ በታች ባሉ ዜጎቻቸውን በብድርና በዕርዳታ የሚያኖሩ አገራት ያለው ውጤት እጅግ አስከፊ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጽዋል፡፡ ከመክፈቻ ፕሮግራም ውጪ ያለው የውይይት ...
Read More »በነ ሚሚ ስብሀቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለስፖርት ዘገባ የተላከ ጋዜጠኛ በዚያው ጠፋ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ሚሚ ስብሀቱ ፦”ጋዜጠኛው እኛን አይወክልም”በማለት ክደዋል። ጋዜጠኛው ቪዛ ያገኘበት መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል። ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ያለበትን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለማካሄድ ወደ ጆሀንስበርግ ባቀናበት ወቅት ነው የዛሚ ኤፍ ኤም አዲስ ጋዜጠኛ አብሮ እንዲሄድ የተደረገው:–በሮያል ባፎኬንግ ስታዲየም የተካሄደውን የባፋና ባፋና እና የዋልያዎችን ጨዋታ ከስፍራው እየተከታተለ ...
Read More »የኢትዮጵያን ወታደሮች የጫነ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በፈንጅ ተመታ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሶማሊያዋ የበለደውይን ግዛት ውስጥ ሰፍሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ትናንት በደረሰበት ከፍተኛ የመንገድ ላይ ፈንጅ ጥቃት በርካታ የሰራዊት አባላት ሳይሞቱ እንዳልቀረ ከሶማሊያ የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጥቃቱ ተፈጸመው ከርቀት በሚታዘዝ ፈንጂ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን የማቾቹን ቁጥር ይፋ አላደረገም ይሁን እንጅ የመከላከያ አባላት አካባቢውን በመዝጋት ነዋሪዎችን ሲአዋክቡና ሲፈትሹ መዋላቸው ታውቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ...
Read More »በባለሀብቶች እንቅስቃሴ ባለመርካቱ መንግስት መሬት የመስጠቱን እንቅስቃሴ መግታቱን አስታወቀ
ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰፋፊ የግብርና መሬቶችን ለውጪ ባላሃብቶች በብዛት በመስጠቱ ምክንያት ዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ወቀሳ እየቀረበበት የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት ፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን የወሰዱ ባለሀብቶች እንቅስቃሴ አርኪ ባለመሆኑ መሬት መስጠት መግታቱን አስታወቀ። ይሁን እንጅ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለባለሀብቶች ለመስጠት ዝግጅት መጨረሱን አስታውቋል። የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ዛሬ የመ/ቤታቸውን የ2004 በጀት ዓመት የ10ወራት ...
Read More »