የኢትዮጵያን ወታደሮች የጫነ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በፈንጅ ተመታ

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሶማሊያዋ የበለደውይን ግዛት ውስጥ ሰፍሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ትናንት በደረሰበት ከፍተኛ የመንገድ ላይ ፈንጅ ጥቃት በርካታ የሰራዊት አባላት ሳይሞቱ እንዳልቀረ ከሶማሊያ የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጥቃቱ ተፈጸመው ከርቀት በሚታዘዝ ፈንጂ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን የማቾቹን ቁጥር ይፋ አላደረገም ይሁን እንጅ የመከላከያ አባላት አካባቢውን በመዝጋት ነዋሪዎችን ሲአዋክቡና ሲፈትሹ መዋላቸው ታውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተዳከሙ የሚነገርላቸው የአልሸባብ ታጣቂዎች የመንገድ ላይ ፈንጂዎችን በማጥመድ ጥቃት እያደረሱ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአራት ወራት በፊት አካባቢውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንደሚወጣ አቶ መለስ ለፓርላማ አባላት መናገራቸው ቢታወስም፣ ሰራዊቱ አሁንም በበለደውይን ይገኛል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide