ሲፒጄ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣውን አዲስ የቴልኮም አጠቃቀም አዋጅ አወገዘ

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው አዲሱ የቴሌኮሚነኬሽን አዋጅ መንግስት ማንኛውንም የግንኙነት መንገዶች ሁሉ ለመቆጣጠር መፈለጉን የሚያሳይ ነው በማለት አውግዟል።

የሲፒጄው የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ቶም ሮድስ የኢትዮጵያ መንግስት በኢንተርኔት በሚተላለፉት ነጻ መረጃዎች እና ጠንካራ ዘገባዎች ስጋት ላይ እየወደቀ መምጣቱን ተናግረዋል። ጋዜጠኞች ከመንግስት ክትትልና አፈና ለማምለጥ ሲሉ የሚጠቀሙባቸውን የመገናኛ ዘዴዎች ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስት በደህንነት ስም ወንጀል ማድረጉን ሲፒጄ ገልጧል።

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያወጣው አዲስ የቴሌ ህግ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንንን ትኩረት ስቧል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide