.የኢሳት አማርኛ ዜና

ዶ/ር ኢሌኒ ገብረመድህን ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዶ/ር ኢሌኒ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እርሳቸውና አብረዋቸው ሢሰሩ የነበሩት የሥራ ባልደረቦቻቸው በፈቃዳቸው ሀላፊነታቸውን እንደለቀቁ አስታውቀዋል። ሀላፊነታቸውን የለቀቁትም፤ ቦታውን በዘርፉ ልምድ ላካበቱ ሙያተኞች ለመልቀቅ በመፈለጋቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ዶ/ር ኢሌኒ ሥራ መልቀቃቸውን ፦”የመተካካት ሂደት ነው” ቢሉትም፤ ሁኔታው  በገዥዎቹ መንደር ሳይቀር ድንጋጤ መፍጠሩን ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተሉ ጋዜጠኞች ጠቁመዋል። እንደ ምንጮች መረጃ ፤ሁኔታው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ...

Read More »

በሲዳማ ዞን ከፍተኛ የሆነ የዘር ግጭት ሊነሳ ይችላል በማለት የአካባቢው ሰው በስጋት ወድቋል

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአዋሳ ዘጋቢዎች እንደገለጡት ትናንት በአለታ ጩኮ የተነሳውን ተቃውሞ ተክትሎ በዛሬው እለትም ከአዋሳ በ 10 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ቱላ ከተማ ውስጥ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውንና መኪኖችን አግተው ለመስክ ስራ የሄዱ ሰራተኞች ስራ ሳይሰሩ እንዲመለሱ ማድረጋቸው ታወቋል። ተማሪዎች በየመኪኖች ውስጥ እየገቡ የወላይታ ተወላጆችን እንዲወርዱ ሲጠይቁ እንደነበር የገለጠው ዘጋቢያችን ትናንት ማታ 2 የወላይታ ተወላጆች ...

Read More »

የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ የፍርድ ውሳኔ ተራዘመ

ሰኔ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በእነ አቶ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል ከ10 ወራት በፊት ከተከሰሱት 24 የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላት ፣ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት 8 ተከሳሾች ዛሬ የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስማት በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም በድጋሜ ቀጥሮ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል። ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰአት ከ35 ደቂቃ ላይ በችሎቱ ...

Read More »

በያዝነው ክረምት ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች መካከል የሚታሰሩ እንዳሉ ታወቀ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከፌደራል ፖሊስ የኢሳት ምንጮች በተገኘው መረጃ የፍርድ ቤቶችን መዘጋት አስታኮ በክረምቱ ወራት ከአንድነት ፓርቲ፣ ከፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ እና ከፍትህ ጋዜጣ የሚታሰሩ መንግስት ስጋቴ ናቸው ያላቸው ሰዎች ይኖራሉ። እንደመረጃ ምንጮች ሰዎችን በክረምት ለማሰር የተፈለገው ግለሰቦችን በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ለማሰቃየት እንዲያመች ነው። እስካሁን ድረስ እነማን ይታሰሩ እንማን ይቅሩ በሚለው ላይ የፖለቲካ ውሳኔ አልተሰጠም፣ ...

Read More »

ከ47 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አለቁ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቢቢሲ እንደዘገበው ከታንዛኒያ ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በማላዊ ሀይቅ ላይ ሰምጠዋል። ሟቾቹ የሶማሊያ ዜጎች መሆናቸው የተገለጠ ቢሆንም፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር ሰራተኞች አካባቢውን ከጎበኙ በሁዋላ እንዳረጋገጡት በርግጥም ስደተኞች የሶማሊያ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው። መርከቧ ከአቅም በላይ በመጫኗ ሳትሰምጥ እንዳልቀረች የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። እስካሁን ድረስ የ47 ሰዎች ...

Read More »

በሰሜን ሸዋ ዞን አንድነትን ወክለው በምርጫ የተወዳደሩት ግለሰብ ተገደሉ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቅዱስ ሀብት በላቸው ፍኖተ ነጻነትን በምንጭነት ጠቅሶ እንደዘገበው ፍቼ አካባቢ የሚገኘው ልዩ ስሙ ግራር ጀርሶ ጊዮ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ውስጥ ይኖሩ የነበሩት አቶ ቸሩ ዘውዴ ባለፈው እሁድ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተገድለዋል። በምርጫ 2002 አንድነትን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የተወዳደሩት ሟች አቶ ቸሩ ዘውዴ፤ የአካባቢው ሃላፊዎች በተደጋጋሚ አባል የሆኑበትን የአንድነት ፓርቲን አውግዘው፣ የኢሕአዴግ ...

Read More »

በፍርድ ቤት ዳኞች ቁጣ ሕብረተሰቡ መማረሩ ተገለፀ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአገራችን በሚገኙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ውስጥ የተሰየሙ ዳኞች በባለጉዳዮች ላይ በሚያሰሙት ቁጣና ሃይለ ቃል በመረበሽ ባለጉዳዮች በችሎት ውስጥ ባግባቡ ሃሳባቸውን ባግባቡ ሳይገልፁ መመለሳቸው እውነት መሆኑን የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ፕሬዚዳንት አመኑ። እንደ ሪፖርተር ዘገባ፤- ከትናንት በስቲያ በፓርላማው ተገኝተው የ2004 ዓመት ሪፖርት ያቀረቡት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ፤ ይህንኑ አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ...

Read More »

በሲዳማ ዞን በአለታ ጭኮ ከተማ በተደረገው ተቃውሞ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ተቃውሞው የተነሳው ከአዋሳ እጣ ፋንታ ጋር በተያያዘ ነው። የኢሳት ምንጮች እንደተናገሩት በአለታ ጭኮ በተነሳው ተቃውሞ አንድ ፖሊስ የታረደ ሲሆን ሁለት ነዋሪዎች በፖሊሶች ሳይገደሉ አልቀረም አራት ተማሪዎችም በጽኑ ቆስለዋል። በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ የገለጠው ዘጋቢአችን በነገው እለት ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመጽ ሊነሳ ይችላል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነው። የመከላከያ ሰራዊት እና ...

Read More »

በሽብር ወንጀል በተከሰሱት በእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ላይ ነገ ፍርድ ይሰጣል

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፣  ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበረሰብ አባለት በነገው እለት የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጣቸው ሲሆን ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ የፖለቲካ አጋሮቻቸው ከፍርድ ቤቱ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። በእነ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌ እና አቶ ናትናኤል መኮንን፣ የመኢዴፓ አመራር ...

Read More »

አሜሪካ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለኢትዮጵያ ልትለግስ ነው

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገንዘብ ልማት ሚኒስቴር ዲኤታ የሆኑት አቶ አህመድ ሼዲ እና የአሜሪካ አለማቀፍ የልማት ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ሚ/ር ቶማስ ስታል  ስምምነቱን ፈርመዋል። ገንዘቡ ለትምህርት ለጤናና ለመልካም አስተዳዳር ግንባታ እንደሚውል የልማት ድርጅቱ ዳይሬክተር ተናግረዋል። አሜሪካ ይህን ያክል ገንዘብ ለኢትዮጵያ ስትለግስ የአሁኑ የመጀመሪያ ነው። ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት አያያዙዋ በስቴት ዲፓርትመንት ሳይቀር ክፉኛ ብትተችም፣ አሜሪካ መንግስት አሁንም ለኢትዮጵያ ...

Read More »