በሰሜን ሸዋ ዞን አንድነትን ወክለው በምርጫ የተወዳደሩት ግለሰብ ተገደሉ

ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ቅዱስ ሀብት በላቸው ፍኖተ ነጻነትን በምንጭነት ጠቅሶ እንደዘገበው ፍቼ አካባቢ የሚገኘው ልዩ ስሙ ግራር ጀርሶ ጊዮ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ውስጥ ይኖሩ የነበሩት አቶ ቸሩ ዘውዴ ባለፈው እሁድ በጥይት ተደብድበው በግፍ ተገድለዋል።
በምርጫ 2002 አንድነትን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የተወዳደሩት ሟች አቶ ቸሩ ዘውዴ፤ የአካባቢው ሃላፊዎች በተደጋጋሚ አባል የሆኑበትን የአንድነት ፓርቲን አውግዘው፣ የኢሕአዴግ አባል እንዲሆኑ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን የጠቀሰው ይኸው የአንድነት ልሳን፣ በዚህም የተነሳ በተደጋጋሚ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይሰነዘርባቸው እንደነበር ገልጿል።
ባካባቢው በሚንቀሳቀሱ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች የእርሻ መሬታቸውን ሳይቀር እንዳያርሱ ከመከልከላቸውም በተጨማሪ፤ በአድማ የአካባቢው ህብረተሰብ ከማህበራዊ ሕይወት እንዲያገላቸው ጥረት መደረጉን የጠቆመው ይኸው ጋዜጣ፤ በመጨረሻም በአካባቢያቸው የሚኖሩ በርካታ ሰዎች በተሰበሰቡበት ግጭት በመፍጠር ባደባባይ በጥይት ደብድበው ከገደሏቸው በኋላ፣ የአካባቢው ኃላፊዎች በሥፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ምስክርነት እንዳይሰጡ እያስጠነቀቁ መሆኑን አስታውቋል።
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide