በሲዳማ ዞን በአለታ ጭኮ ከተማ በተደረገው ተቃውሞ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ተቃውሞው የተነሳው ከአዋሳ እጣ ፋንታ ጋር በተያያዘ ነው። የኢሳት ምንጮች እንደተናገሩት በአለታ ጭኮ በተነሳው ተቃውሞ አንድ ፖሊስ የታረደ ሲሆን ሁለት ነዋሪዎች በፖሊሶች ሳይገደሉ አልቀረም አራት ተማሪዎችም በጽኑ ቆስለዋል።

በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ የገለጠው ዘጋቢአችን በነገው እለት ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመጽ ሊነሳ ይችላል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነው። የመከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸውም ታውቋል። ከትናንት ጀምሮ “አዋሳ ለወላይታ አትጨጥም” የሚል በራሪ ወረቀት ሲበተን እንደነበር የአይን እማኞች ገልጠዋል። አንድ የአዋሳ ነዋሪ በከተማው ያለው ውጥረት አስፈሪ እንደሆነና በማንኛውም ጊዜ ግጭት ሊነሳ እንደሚችል ተናግሯል።

አዋሳ ከተማን ወደ ፌደራል መንግስቱ ለማዞር በፌደራል መንግስት እና በሲዳማ ዞን ባለስልጣናት መካከል ባለፈው ሳምንት ውይይት ተደርጎ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

ከ10 አመታት በፊት በአዋሳ በተመሳሳይ ምክንያት በተነሳ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide