Author Archives: Central

በሳውዲ አረብያ የታሰሩት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ሊመለሱ ይችላሉ ተባለ

የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳውዲ አረብያ በእስር ላይ የሚገኙት 53 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን በስተቀር ሁሉም ወደ አገራቸው ሊመለሱ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ መቼ እንደሚመለሱ እስካሁን ባይታወቅም በቅርቡ ከሳውዲ ሊባረሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ከእሰረኞቹ መካከል 46ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ ፖሊሶች  ሴቶችን እየደጋገሙ በማስወጣት ለስነልቦና ...

Read More »

የውጭ ምንዛሬ እጥረት በእህልና በእቃዎች ዋጋ ላይ ጭማሪ እያስከተለ ነው

የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የተከሰተው አሳሳቢ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ነዳጅን ጨምሮ በተለያዩ ከውጭ ተገዝተው በሚመጡ እቃዎች እና በእህል ዋጋ ላይ ጭማሪ እያሳየ መምጣቱ ታወቀ ዘጋቢያችን እንደገለጠው ካለፉት 7 ወራት ጀምሮ የተከሰተው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ከውጭ በሚገቡ በተለይም ከትራንስፖርት ጋራ ተያያዢነት ባላቸው እቃዎች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው። የፍጆታ እቃዎች ባልሆኑት ላይ የታየው ጭማሪ በእህል ...

Read More »

በኦሮሚያ ለአባ ገዳ የተሰበሰበው ገንዘብ በባለስልጣናት ተመዘበረ

የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጉጂ ኦሮሞ ባህል አንድ አባገዳ ስልጣን በተረከበ በስድስተኛው አመት ጉማታ ወይም ስጦታ ከህዝቡ ይሰበስባል። ስልጣኑን የሚያስረክበው በስምንተኛው አመት ሲሆን፣ ለሁለት አመታት የሚሰራበትን ገንዘብ፣ እህል ወይም የቤት እንስሳ ከህዝቡ በስጦታ መልክ ይቀበላል። በዚህ አመት አባገዳው ጉማታውን ለመሰብሰብ ዝግጅት በሚጀምርበት ጊዜ የቦረና ዞን የመንግስት ባለስልጣናት ከአሁን በሁዋላ ጉማታው መሰብሰብ ያለበት በመንግስት ነው በሚል ምክንያት፣ ...

Read More »

አቡነ ሳሙኤል ለፓትሪያርክነት ለመመረጥ ቅስቀሳ መጀመራቸው ተዘገበ

የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን  አወዛጋቢውን ጳጳስ አቡነ ጳውሎስን የሚተካ ስድስተኛው ፓትሪያሪክ ለማስመረጥ በዝግጅት ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት ከዚህ የፓትሪያሪክ ምርጫ ጋር በተያያዘ የቤተ ክርስትያኒቷ የተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስና ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነበሩበት ወቅት ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው የነበሩት አቡነ ሳሙኤል በቀጣዩ ምርጫ ...

Read More »

ሱዳን በአሜሪካ ላይ ያላትን ተቃውሞ ገለጸች

የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካ ደቡብ ሱዳንን ለመደገፍ በሚል ለጋሾችን በአንድ ጉባኤ ላይ ለማናገር የምታደርገውን ጥረት ሰሜን ሱዳን ታቀወመች። የሰሜን ሱዳን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አሊ ኦቤድ ማርዊ  አሜሪካ በኢኮኖሚ ቀውስ የተነሳ ለመፈራረስ ጫፍ ላይ የደረሰችውን ደቡብ ሱዳንን ለመደገፍ የምታደርገው ጥረት ፣ ደቡብ ሱዳን ከሰሜን ሱዳን ጋር የገባችውን ውል እንዳታከብር ያደፋፍራታል ሲሉ ተናግረዋል። የአሜሪካ የደቡብ ሱዳን ...

Read More »

ጣሊያን ኢትዮጵያውያንን በግፍ የጨፈጨፈችበት 76ኛ አመት በመላው አለም ታስቦ ዋለ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረች ማግስት፣ አገራቸውን ከወረራ ለመታደግ ሞገስ አስገዶምና አብረሀ ደቦጭ የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን፣ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒቶ ሙስሎኒ የኢትዮጵያ ልኡክ የነበረውን ሮዶልፎ ግራዚያኒን ለመግደል  ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ወራሪው ሀይል ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ቀን በግፍ መጨፍጨፉ ይታወሳል። ኢትዮጵያውያን በእየአመቱ የካቲት 12 የሚያከብሩት ይህ የሰማእታት ቀን  በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ...

Read More »

ጄነራል ሳሞራ የኑስ በ80 ሚሊዮን ብር ህንጻ አሰርተው እያከራዩ ነው

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በቄራ መብራት ሀይል አካባቢ በ80 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ህንጻ ማሰራታቸውን በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ውስጥ አዋቂዎች ለኢሳት ላኩት መረጃ ያመለክታል። የጄኔራል ሳሞራ ህንጻ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም መከራየታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ጄኔራል ሳሞራ መከላከያ ሚኒስቴር በወር 10 ሺ ዶላር የሚከፍልበት በልዩ የደህንነት መሳሪያዎች በየሚጠበቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ...

Read More »

የተመራጭ እጩዎች ምዝገባ በተጠናቀቀ በሳምንቱ ዛሬም ምዝገባ እየተካሄደ ነው

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባና አካባቢ ምርጫ፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቁን አውጆ ነበር። ኢሳት ባለው የመረጃ መረብ ለማረጋጋጥ እንደቻለው በቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ የተማራጮች ስም ዝርዝር አለመተላለፉን ምርጫ ቦርድ ለኢህአዴግ ከገለጸ በሁዋላ ከክልልና ከዞን የተውጣጡ የኢህአዴግ አመራሮች ወደ ወረዳው በመሄድ አቶ ሀይሌ አየለ የተባሉትን የኦህዴድ ኢህአዴግ የፖለቲካ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ፖለቲካዊና ማኀበራዊ ይዘት ያላቸው መፅሔቶችና መፅሐፎች እንዳይሸጡ ታገደ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍኖተ ነጻነት እንደዘገበው  መጽሄቶችንና መፅሀፎችን አዙረው የሚሸጡ  ወጣቶችም ከየካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ  የያዙዋቸው መጽሀፎችና መጽሄቶች ተወርሶባቸዋል። በተለይ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 11 ልዩ  ስሙ አባጃሌ በሚባል አካባቢ ያሉ የደንብ  አስከባሪዎች እዚህ ጎንደር ውስጥ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን   መፅሔቶች፣ ጋዜጦችና መፅሐፎች  መሸጥ አትችሉም በሚል በተደጋጋሚ  ጊዜ ከአዙሪዎች እየወረሱ ቅጣት እያሉ   ያስከፍሏቸው ...

Read More »

በአዲስ አበባ ምርጫ ከ99 በመቶ በላይ በእጩነት የተመዘገቡት ኢህአዴግ ናቸው

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወኪል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች= በመዘዋወር ያጠናቀረው ዘገባ እንደሚያመለክተው በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ የወረዳና የአካባቢ ምርጫ፣ ተወዳዳሪ ሆነው በእጩነት የቀረቡት 99 በመቶ የሚሆኑት የኢህአዴግ አባላት ናቸው። አብዛኞቹ ተመራጮች የመንግስት ሰራተኞችና በጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ተመድበው የሚሰሩ ናቸው። በእጩዎች ስም ዝርዝር ላይ እንደሚታየው ከ40 በመቶ በላይ ተመራጮች ከ3ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የሚሸፍን የትምህርት ...

Read More »