ሱዳን በአሜሪካ ላይ ያላትን ተቃውሞ ገለጸች

የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አሜሪካ ደቡብ ሱዳንን ለመደገፍ በሚል ለጋሾችን በአንድ ጉባኤ ላይ ለማናገር የምታደርገውን ጥረት ሰሜን ሱዳን ታቀወመች።

የሰሜን ሱዳን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አሊ ኦቤድ ማርዊ  አሜሪካ በኢኮኖሚ ቀውስ የተነሳ ለመፈራረስ ጫፍ ላይ የደረሰችውን ደቡብ ሱዳንን ለመደገፍ የምታደርገው ጥረት ፣ ደቡብ ሱዳን ከሰሜን ሱዳን ጋር የገባችውን ውል እንዳታከብር ያደፋፍራታል ሲሉ ተናግረዋል።

የአሜሪካ የደቡብ ሱዳን ልዩ ልኡክ ፕሪስተን ለይማን አገራቸው ለደቡብ ሱዳን መንግስት እርዳታ ለማፈላለግ ለጋሾችን ለማሰባሰብ ጥረት እንደሚጀመሩ ካስታወቁ በሁዋላ ነው ሱዳን ተቃውሞአዋን የገለጸችው።

አሜሪካ የደቡብ ሱዳን መፈረካከስ በአካካቢው አገሮች ላይ ተመሳሳይ ችግር ይፈጥራል የሚል እምነት አላት።

አቶ  ሐይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሁለቱን አገሮች መሪዎች አዲስ አ=   በባ በመጋበዝ ማነጋገራቸውን እና ከፍተኛ የዲፐሎማሲ ድል እንደተገኘ በይፋ ቢገልጹም፣ በሁለቱ መንግስታት መካከል ያለው አለመግባባት እየጨመረ ሄዷል።