ጄነራል ሳሞራ የኑስ በ80 ሚሊዮን ብር ህንጻ አሰርተው እያከራዩ ነው

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በቄራ መብራት ሀይል አካባቢ በ80 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ህንጻ ማሰራታቸውን በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ውስጥ አዋቂዎች ለኢሳት ላኩት መረጃ ያመለክታል።Samora house 4Samora house 1

የጄኔራል ሳሞራ ህንጻ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም መከራየታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

ጄኔራል ሳሞራ መከላከያ ሚኒስቴር በወር 10 ሺ ዶላር የሚከፍልበት በልዩ የደህንነት መሳሪያዎች በየሚጠበቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይኖራሉ። አብዛኞቹ የህወሀት ጄኔራሎች በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚያሰሩዋቸውን ህንጻዎች በፎቶግራፍ በማስደገፍ መዘገባችን ይታወሳል።

ጄኔራል ሳሞራ በፎቶ ግራፍ ከሚታየው ህንጻዎች በተጨማሪ ሌሎች ህንጻዎች እንዳሉዋቸውም ለማወቅ ተችሎአል።