በሳውዲ አረብያ የታሰሩት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ሊመለሱ ይችላሉ ተባለ

የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሳውዲ አረብያ በእስር ላይ የሚገኙት 53 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን በስተቀር ሁሉም ወደ አገራቸው ሊመለሱ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያኑ መቼ እንደሚመለሱ እስካሁን ባይታወቅም በቅርቡ ከሳውዲ ሊባረሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

ከእሰረኞቹ መካከል 46ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ ፖሊሶች  ሴቶችን እየደጋገሙ በማስወጣት ለስነልቦና ጉዳት እየዳረጉዋቸው መሆኑም ታውቋል።

የአለማቀፉ ማህበረሰብ የእስረኞችን ደህንነት በተመለከተ በቂ ትኩረት አለመስጠቱ እንዳሳዘናቸው ኢትዮጵያውያኑ ተናግረዋል።