መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሱት የመንግስትን ፖሊሲ በመቃወም ነው። ጉዳዩን በማስመልከት ቃለመጠይቅ ያደረግንለት አቶ ሙሉጌታ ፈለቀ “ኢትዮጵያኑ መንግስት በድብቅ ስብሰባ ማዘጋጀቱን እንደሰሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰባስበው በመቃማቸው የመንግስት ባለስልጣናት ስብሰባውን በመሰረዝ አዳራሹን ለቀው መውጣታቸውን እና መንግስት ከፍሎ በተከራየው አዳራሽ የራሳቸውን ስብሰባ ማካሄዳቸውን” ገልጸዋል። በተቃውሞም ግጭት አለመነሳቱንም አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል
Read More »Author Archives: Central
በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ
መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሞ የውይይት መድረክ አዘጋጅነት ሚኒሶታ ውስጥ ሲካሄድ የሰነበተውን ውይይት ተከትሎ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ። የፓርቲው ስያሜ፦” የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር” እንደሆነ በምስረታው ጊዜ ይፋ ሆኗል። ይፋ ከተደረገው የፓርቲው ዓላማና ፕሮግራም ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመታገል የኦሮሞ ህዝብ ነፃነቱን እንዲቀዳጅና ራሱን በራሱ ማስተዳደር እንዲችል ይሠራል። በ አቶ ሌንጮ ...
Read More »አለማቀፍ መንግስታዊ ድርጅቶች ባደረጉት ጫና ካራቱሬ ገንዘብ ለመበደር አለመቻሉን አስታወቀ
መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ እንደዘገበው ኦክላንድ የምርምር ድርጅቶችን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት ባሰረፉት ጫና ኩባንያው ከአለማቀፍ ድርጅቶች ገንዘብ ለመበደር ባለማቻሉ ከህንድ መንግስት ለመውሰድ ሳይገደድ አይቀርም። የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሳይ ራካማራሺና እንደተናገሩት በ100 ሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከሌላ ወገን ለማግኘት ፈቃድ አግኝተዋል። ካራቱሬ በኢትዮጵያ ሰፊ የእርሻ መሬት በመውሰድ ሩዝ በማምረት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። ድርጅቱ 6 ሚሊዮን 500 ...
Read More »ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀዋል
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከ3 እስከ 4 ሺ የሚሆኑ ከቤንሻcccጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ከመስተዳድሩ ፊት ለፊት ባለ ሜዳ ላይ ያለምንም መጠለያ እንዲሰፍሩ ተደርጓል። ከከተማው ነዋሪዎች ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ተፈናቃዮቹ ቀን በጸሀይ፣ ሌሊት በብርድ እየተሰቃዩ ነው። እጅግ በርካታ ህጻናትና ሴቶች ከተፈናቀሉት መካከል ይገኙበታል። ተፈናቃዮች ከአካባቢያቸው ይዘውት የመጡትን ዱቄት እየጋገሩ በበመገብ ...
Read More »መንግስት እና ነጋዴው በዶላር አቅርቦት ዙሪያ ያላቸው ውዝግብ ጨምሯል
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረውን ከፍተኛ የዶላር እጥረት ተከትሎ ነጋዴዎች ላለፉት 8 ወራት ኤልሲ ከፍተው እቃዎችን ለማስገባት ሳይችሉ ከመቅረታቸውም በተጨማሪ አብዛኛው የውጭ ምንዛሬ መንግስት ለሚያስገነባቸው ግንባታዎች አቅርቦት መግዢያ ብቻ እንዲፈቀድ አድርጎ ቆይቷል። ሰሞኑን መንግስት ለነጋዴዎች ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ማንም በውጭ ንግድ ላይ የተሳተፈ ሁሉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት እንደሚችል ግልጽ አድርጓል። ይሁን እንጅ አዲሱ ...
Read More »መንግስት ለአባይ ግድብ ግንባታ ከህዝብ ለመሰብሰብ ያወጣውን እቅድ ሳይተወው አይቀርም ተባለ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የአባይ ግድብን በሕዝብ ተሳትፎ ለመገንባት ባቀደው መሰረት ከመንግስት ሰራተኞች፣ባለሃብቶች፣አርሶአደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እያካሄደ ያለውን የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ዘንድሮም ለመቀጠልም አቅዶ ቢንቀሳቀስም ከህዝቡ የታሰበውን ያህል ምላሽ ባለመገኘቱ ለማቋረጥ ሳይገደድ እንደማይቀር ምንጮቻችን ገለጡ። የአባይ ግድብ ከተጀመረ በኋላ በተለይ ባለፈው ዓመት የመንግስት ሰራተኞች ሳይወዱ በግድ የአንድ ወር እና ከዚያ በላይ ደመወዛቸውን በአንድ ዓመት ...
Read More »ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው ከሚጓዙት ሰዎች መካከል 2 ህጻናት ታፍነው ሞቱ
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው እለት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሀይል ተፈናቅለው ወደ ክልላቸው በመጓዝ ላይ ከነበሩት የአማራ ተወላጆች መካከል ሁለት ህጻናት ታፍነው መሞታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የአካባቢው ነዋሪ ለኢሳት ገልጸዋል። እያንዳንዳቸው ከ70 እስከ 80 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆችን የጫኑ 6 አይሱዙ መኪኖች ወደ አማራ ክልል የተጓዙ ሲሆን፣ ሁለቱ ህጻናት በመንገድ ላይ የሞቱት አየር አጥሯቸው ነው። እናታቸው ልጆቿን ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድርና አቶ አንዱለአም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቃሊቲ ማረሚያ ቤት፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና አቶ አንዱአለም አራጌን ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ቀርቷል። የፍርድ ቤቱ ፖሊስ ለእስር ቤቱ ሀላፊዎች ደብዳቤ ማድረሷን ገልጻለች። የፌደራል ጠ/ፍርድ ቤት በ አቶ አንዱ አለም አራጌ የክስ መዝገብ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ወንጀል የተፈረደባቸውን የ አንድነት ፓርቲ ም/ል ሊ/መንበር እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ ፣ ...
Read More »አቶ አዲሱ ለገሰ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን በሀሜተኝነት ነቀፉ፤ አስጠነቀቁም
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ስለዴሞክራሲያዊ ድርጅትም ስናወራ በአስተሳሰብም በተግባርም ወደ አንድ መምጣት መቻል አለብን። አሁን ባለው አቀራረብ ከሄድን ግን መቀራረቡ አይደለም የሚጨምረው”ሲሉ አቶ አዲሱ ለገሰ የ ኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን አስጠነቀቁ። የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራር የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ አባል ድርጅቶቹን ያስጠነቀቁት “መተካካቱ በብአዴን ውስጥ በተቀመጠው እቅድ አልተተገበረም” በማለት እርሳቸውና ድርጅታቸው በሌሎቹ ድርጅቶች አመራሮች በመታማታቸው ...
Read More »ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ 60 የአማራ ተወላጆችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ 59 ሰዎች ሞቱ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአካባቢው ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አደጋው የተፈጠረው፣ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው መኪና ትክሻ በምትባል ቀበሌ ውስጥ ጀዴሳ በሚባል ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው። ከትናንት ወዲያ በተፈጠረው አሰቃቂ አደጋ ለሞቱት ሰዎች የደረሰላቸው ሰው አለመኖሩን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገልጽ የፈለጉ ተፈናቃይ አርሶደሮች ተናግረዋል። ከሞቱት መካከል ህጻናትና ሴቶችም ይገኙበታል። በአደጋው ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ...
Read More »