ግንቦት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 20 አመታት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከሞላ ጎደል ጥሩ የሚባል ግንኙነት የነበረው የአለም ባንክ በሀይል ከሚፈናቀሉ ዜጎች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ታውቋል። ሂውማን ራይትስን ጨምሮ ሌሎች አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በጦር ሀይል በመታገዝ ከ45 ሺ በላይ የጋምቤላ ተወላጆችን በግዴታ ማስፈሩን ተቃውመው ነበር። የአለም ባንክ አንድ ገለልተኛ ቡድን በማቋቋም ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጽያ የማጅራት ገትር ወረርሽን ተከስቷል፤መንግስት ግን ጉዳዩን አፍኖታል
ግንቦት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባና በአንዳንድ ክልሎች የማጀራት ገትር ወረርሽኝ መከሰቱንና መንግስት ጉዳዩን በከፍተኛ ምስጢር ከመያዝ ባለፈ ስርጭቱን ለመግታት ተገቢው የክትባት አገልግሎት እየሠጠ አለመሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጸዋል፡፡ በማጅራት ገትር ወረርሽኝ ሰዎች እየተያዙ መሆኑንና የሞቱ ሰዎች ከየሆስፒታሉ ሪፖርት እየተደረገ ነው ያሉት ምንጮቹ ነገር ግን የኢትዮጽያ መንግስት በተለይ 50ኛውን የአፍሪካ ህብረት በዓል ያስተጓጉላል በሚል በከፍተኛ ምስጢር እንዲያዝ ...
Read More »የባህር ዳር ነዋሪዎች ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ አንዝቦብናል አሉ
ግንቦት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ዓመት ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም የጣለው ከባድ ዝናብ ከ 3000 በላይ ኖሪዋችን ማፈናቀሉንና ከ 15 ሰዎች በላይ መግደሉን ያስታወሱት ነዋሪዎች ፣ የከተማው አስተዳደር ከአምናው ትምህርት ለመውሰድ ባለመቻሉ ማዘናቸውን እየገለጹ ነው። የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሺን ችግሩን ለማስወገድ ለከተማ አስተዳደሩ ሩብ ሚሊዩን ብር ቢለግስም ገንዘቡ የት እንደገባ እንደማይታወቅ ምንጮች ገልጸዋል። ችግራችንን ለማሰወገድ ...
Read More »በጉንዶ መስቀል ከተማ ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች ቆሰሉ
ግንቦት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ጉንዶመስቀል ከተማ ሶራ ካፌ ውስጥ 4፡30 አካባቢ በፈነዳ ቦንድ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከተጎዱት መካከል 3ቱ ክፉኛ ቆስለው ወደ ፍቼ ሆስፒታል ሲወሰዱ አንዱ ደግሞ በከተማው ጤና ጣቢያ በመታከም ላይ ነው። ከቆሰሉት መካከል አንድ ፖሊስ፣ አንድ ነጋዴና እና ሁለት አርሶአደሮች ይገኙበታል። የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ ...
Read More »በኢትዩጱያ የኩፍኝ በሺታ ወረርሺኝ በስፋት እየተሰራጨ ነው፡፡
ግንቦት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እንዳመለከተው በአገሪቱ ባሉ 146 ወረዳዎች በሺታው ሙሉ በሙሉ መሰራጨቱን አረጋግጧል። ኩፍኝ በአየር የሚዛመት በሃገሪቱ ቁጥር አንድ ገዳይ ነው ያለው ሪፖርቱ ከ 2.6 ሚሊዩን በላይ ህጻናት አደጋ መሆናቸውንም ጠቁሟል። የበሺታው የስርጭት መጠን ከ 75-80 በመቶ የደረሰ ሲሆን አሀዙም ከፍ ሊል እንደሚችል ይገመታል። የበሺታው መኖር በሃገሪቱ የጤና ላብርቶሪ የተረጋገጠ ሲሆን ...
Read More »ግንቦት7 አመታዊ ጉባኤውን አካሂዶ መሰረታዊ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታወቀ
ግንቦት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለኢሳት እንደገለጹት ንቅናቄው ላለፉት 4 ቀናት ባካሄደው 4ኛ አመታዊ ጉባኤ ድርጅቱ ባለፉት 2 አመታት የተጓዘበትን እንዲሁም ከመስረታው ጀምሮ የተጓዘበትን መንገድ ገምግሟል። የድርጅቱ የኦዲት ሪፖርት ” ንቅናቄው ሲጀመር ካስቀመጠው አላማ አንጻር ግቡን አለመምታቱን” መግለጹን አቶ ኤፍሬም ገልጸዋል። ግንባሬ መሰረታዊ የሚባል የመዋቅር ለውጥ ማድረጉንም አቶ ኤፍሬም ...
Read More »ኢትዮጵያ ሆቴል እንዲፈርስ የተላለፈው ውሳኔ ተቃውሞ ገጠመው
ግንቦት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢትዮጵያ ሆቴልና ከጎኑ የሚገኘው የበጎ አድራጎት ሕንፃ ፈርሰው፣ በቦታው ላይ 60 ፎቅ ያለው ሆቴል እንዲገነባ የተወሰነው ውሳኔ ተቃውሞ ገጥሞታል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነው። ተቃውሞውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቀረቡት ከ 81 ዓመት በፊት በተገነባውና አሁን ከ ኢትኦጵያ ሆቴል ጋር እንዲፈርስ በተወሰነበት በፖላስሪያቴሪ በጎ አድራጎት ሕንፃ ላይ የሚኖሩ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ ነጋዴዎቹ ተቃውሟቸውን ለከንቲባ ኩማ ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣናት በፈጠሩት ችግር በአፋርና በአማራ ድንበሮች ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሮ ሰዎች ተገደሉ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሰሜን ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ በአፋር እና በአማራ ተወላጆች መካከል በመንግስት ባለስልጣናት በተቀሰቀሰ ችግር ባለፉት 2 ወራት ብቻ ከ15 ያላነሱ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል፣ ከብቶችም ተዘርፈዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ሀሙስ እና አርብ በተፈጠረው ግጭት አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ቆስሏል። ግጭቱን የፈጠሩት የታጠቁ የአፋር ...
Read More »በጎንደር የተቃውሞ ሰልፍ አደራጅተዋል የተባሉ 14 ወጣቶች ታሰሩ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ባለፈው ሳምንት የጎንደር ቀበሌ 6 እና 7 ወጣቶች ያደረጉትን ተቃውሞ ተከትሎ ከ14 በላይ ወጣቶች በዜኖ 1 እና ዜሮ 2 ጣቢያዎች መታሰራቸውን የአካባቢው ወኪሎች ገልጸዋል። ሰልፉን አስተባብረዋል የተባሉት ወጣቶች በየቤታቸው እየታደኑ መያዛቸውን የገለጹት ወኪሎች፣ ፍርድ ቤት ይቀርቡ አይቅረቡ ለማወቅ አለመቻሉን ተናግረዋል። ከቀናት በፊት በጎንደር የቀበሌ6 እና 7 ነዋሪዎች የመብራት፣ ውሀ እና ሌሎችንም ...
Read More »የባለራይ ወጣቶች ህዝብ ግንኙነት ከሌሎች 5 ሰዎች ጋር በግንቦት7 አባልነት ተከሰሰ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ በደህንነቶች ከተወሰደ በሁዋላ በማእከላዊ እስር ቤት መታሰሩን ወንድሙ ሙሉጌታ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጿል። ሀሙስ እለት ፍርድ ቤት የቀረበው ወጣት ብርሀኑ ከእርሱ ጋር ሌሎች በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ 5 ወጣቶች ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። አምስቱ ወጣቶች እርስ በርስ የማይተዋወቁ እና ...
Read More »