ግንቦት7 አመታዊ ጉባኤውን አካሂዶ መሰረታዊ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታወቀ

ግንቦት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለኢሳት እንደገለጹት ንቅናቄው ላለፉት 4 ቀናት ባካሄደው 4ኛ አመታዊ ጉባኤ ድርጅቱ ባለፉት 2 አመታት የተጓዘበትን እንዲሁም ከመስረታው ጀምሮ የተጓዘበትን መንገድ ገምግሟል።

የድርጅቱ የኦዲት ሪፖርት ” ንቅናቄው ሲጀመር ካስቀመጠው አላማ አንጻር ግቡን አለመምታቱን” መግለጹን አቶ ኤፍሬም ገልጸዋል።

ግንባሬ መሰረታዊ የሚባል የመዋቅር ለውጥ ማድረጉንም አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል።

ከአቶ ኤፍሬም ማደቦ ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ ሙሉውን በሚቀጥሉት ቀናት እንደምናቀርብ ለመግለጽ እንወዳለን።