በኢትዩጱያ የኩፍኝ በሺታ ወረርሺኝ በስፋት እየተሰራጨ ነው፡፡

ግንቦት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የአለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እንዳመለከተው በአገሪቱ ባሉ 146 ወረዳዎች በሺታው ሙሉ በሙሉ መሰራጨቱን አረጋግጧል።  ኩፍኝ በአየር የሚዛመት በሃገሪቱ ቁጥር አንድ ገዳይ ነው ያለው ሪፖርቱ ከ 2.6 ሚሊዩን በላይ ህጻናት አደጋ መሆናቸውንም ጠቁሟል።

የበሺታው የስርጭት መጠን ከ 75-80 በመቶ የደረሰ ሲሆን አሀዙም ከፍ ሊል እንደሚችል ይገመታል። የበሺታው መኖር በሃገሪቱ የጤና ላብርቶሪ የተረጋገጠ ሲሆን ወረርሺኙ 146 ወረዳዎች ላይ ይገኛል፡፡

ይህን በጣም አጣዳፊ እና በፍጥነት የሚዛመትን በሺታ ለመከላከል  መንግስት ከቢልጌትስ ፋውንዴሺን እርዳታ ቢያገኝም በሺታው በአሁኑ ስዓት በመስፋፋት ላይ ያለበት ደረጃ፣ ከ15 ዓመት በታች የእድሜ ክልል የሚገኙ  ከ19 ሚሊዩን በላይ ዜጎች ከህክምናው ውጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

መንግስት ባገኘው አነስተኛ እርዳታ ለ2.5 ሚለዩን ሃጻናት መዳህኒቱን ለማደል ቢታሰብም፣ ቀሪው የህበረተሰብ ክልል እጣ ፈንታው በሞት እና በህይዎት መካከል ሆኖ እድሉን መጠበቅ ሁኖዋል፡፡

መንግስት ወርሺኙን ለፖለቲካ ፍጆታ ይውልብኛል ሲል የዜጎቹን ሞት ለመደበቅ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ዩኒሴፍ ባጠናው ጥናት መረጃዎን ይፋ አድርጓል፡፡