(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 21/2011) በህክምና ባለሙያዎች ላይ የሚፈጸሙ የስራ ቦታ የመብት ጥሰቶችን ጨምሮ ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲከበር በመጠየቅ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተቃውሞ ተደረገ። የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የተነሱትን ጥያቄዎች ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ፣ በአርሲ አሰላ፣ በጂማና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች በህክምና ባለሙያዎች እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ የደምወዝ ጭማሪ፣ የስራ ሰዓት ገደብና ስራ ደህንነት ዋስትና በመንግስት በኩል እንዲሰጥ ተጠይቋል። ...
Read More »Author Archives: Central
በምስራቅ ወለጋ አንድ ሻለቃን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 21/2011) በምስራቅ ወለጋ ሻምቦ አካባቢ ከኦነግ ጋር በተካሄደ ውጊያ አንድ ሻለቃን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መገደላቸው ተነገረ። በውጊያው ሻለቃ ይበሉ ጌታቸው የተባለ ነባር የሰራዊቱ አባል በኦነግ ከተገደለ በኋላ አስከሬኑ ለቤተሰቦቹ መሰጠቱ ታውቋል። በውጊያው ሌሎች የሰራዊቱ አባላት መገደላቸውንም አስከሬኑን ያመጡት ኮሎኔል መግለጻቸውንም የሻለቃው ቤተሰቦች ለኢሳት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከኦነግ ታጣቂዎች ጋር በምስራቅ ወለጋ ውጊያ እንደሚያካሂዱ የአካባቢው ምንጮች ...
Read More »በቤንሻንጉል ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት እንዳልቆመ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 21/2011)በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉራ ወረዳ ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት እንዳልቆመ ነዋሪዎች ገለጹ። ባለፉት ሶስት ቀናት በቀስትና በተለያዩ የስለት መሳሪያዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጥቃቱ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ማነጣጠሩን የጠቀሱት ነዋሪዎች በ30 ቀበሌዎች ተስፋፍቶ ቀጥሏል ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት ገብቷል ቢባልም አሁንም በአብዛኛው ቀበሌዎች ጥቃቱ እንዳለ በመግለጽ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። ...
Read More »በቤንሻንጉል ክልል በተፈጠረ ግጭት ከ18 በላይ ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 21/2011) በቤንሻንጉል ክልል ማንዱራ ወረዳ ማምንኩክ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ከ18 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። የማቿቾች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ ይችላል ተብሏል። በሁለት ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት በተነሳው በዚሁ ግጭት ሰዎች ከመገደላቸው ሌላ ቤቶች ተቃጥለዋል ንብረትም ወድሟል ተብሏል። የአማራ ክልል ሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ኮሌኔል አለበል አማራ ለኢሳት እንደገለጹት በግጭቱ የአማራና የጉምዝ ተወላጆች የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስባቸው በአካባቢው ጥምር ...
Read More »በፕሬስ ነጻነት ኢትዮጵያ አርባ ደረጃዎችን አሻሻለች
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2011) በፕሬስ ነጻነት ኢትዮጵያ አርባ ደረጃዎችን ማሻሻሏን ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ። የአሜሪካኑ ዋሽንግተን ፓስት ኢትዮጵያ ከዓመታት አፈና በኋላ ፕሬሱን ነጻ አደረገች ብሏል። ሆኖም የፕሬስ ውጤቶቹ በሃገሪቱ ያለውን የብሔር ፍጥጫ እያባባሱት ነው ሲል ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ ገልጿል። ሪፖርተርስ ዊዘአውት ቦርደርስ ባወጣው የ2019 የዓለም የፕሬስ ደረጃ ኢትዮጵያ አምና ከነበረችበት 150 ደረጃ ወደ 110 በመውረድ መሻሻል አሳይታለች ማለቱን ...
Read More »በሃይለ ገብረስላሴና በእንግሊዛዊው አትሌት ሞህ ፋራህ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተካረረ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2011) በኢትዮጵያዊው ሃይለ ገብረስላሴና በእንግሊዛዊው አትሌት ሞህ ፋራህ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ መካረሩ ተገለጸ። በአትሌት ሃይሌ ሆቴል በነበረኝ ቆይታ ዘረፋ ተፈጽሞብኛል ላለው ሞህ ፋራህ ሃይሌ መልስ መስጠቱ ውዝግቡን እንዳከረረው ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘግቧል። አትሌት ሃይሌ እንደሚለው ሞህ ፋራህ በሆቴል ቆይታው በሰዎች ላይ ድብደባ ፈጽሟል። በስነምግባር ጉድለት ችግር ፈጥሮብኛል ሲል ሞህ ፋራን ከሷል። የሁለቱ የዓለማችን ታላላቅ አትሌቶች ውዝግብ አለምዓቀፍ ትኩረት መሳቡን ...
Read More »በጋምቤላ ክልል ጆር ወረዳ ግጭት ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2011) በጋምቤላ ክልል ጆር ወረዳ ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ። በወረዳው ምንነቱ ያልታወቀ የጦር ካምፕ መገኘቱ የፈጠረው ስጋትን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ስድስት ታጣቂዎች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በጋምቤላ ልዩ ሃይልና በካምፑ በሚገኙ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ለጊዜው ጋብ ቢልም በአካባቢው ህዝብ ላይ ስጋት መደቀኑን የአኝዋክ ሬዲዮ አዘጋጅ አግዋ ጊሎ ለኢሳት ገልጿል።
Read More »የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ተቃዋሚው ዶክተር ሪክ ማቻር በአዲስ አበባ ሊመክሩ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2011)የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ተቃዋሚው ዶክተር ሪክ ማቻር በአዲስ አበባ በሰላም ጉዳይ ላይ ሊወያዩ ነው። በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ አደራዳሪነት የሚካሄደው የሰላም ውይይት በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ችግር እንደገና ይገመግማል ተብሏል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 3/2019 በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው የሰላም ውይይት በቅድመ የሽግግር ጊዜ ይፈጸማል የተባለው ስምምነት ተግባራዊ አለመሆኑን ይመለከታል ተብሏል። ...
Read More »የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ክለሳ እየተደረገበት ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2011)የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ክለሳ እየተደረገበት መሆኑ ተገለጸ። ለ17ዓመታት ሲሰራበት የነበረው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መከለስ ያስፈለገው የዓለም ሁኔታዎች በመቀየራቸው ነው ተብሏል። ኢሳት ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ክለሳው የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የተዘጋጀና ዝርዝር ጉዳዮች የተካተቱበት ይሆናል። ኤርትራን በተመለከተ ፖሊሲው ይዞት የነበረው አቋምም ይከለሳል ሲሉ ገልጸዋል። ከኤርትራ ጋር የሚያዋስኑ ድንበሮች መዘጋታቸውን በተመለከተ በሁለቱ ሀገራት ...
Read More »የጌዲዮ ተፈናቃዮች ሁኔታዎች ካልተስተካከሉ ወደ ቀያቸው እንደማይመለሱ መናገራቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 18/2011)የጌዲዮ ተፈናቃዮች ወደ ቀያችሁ ተመለሱ የተባልንው ምንም ቅድመ ሁኔታ ባልተሟላበት ሁኔታ ውስጥ ነው ሲሉ ለኢሳት ገለጹ። እስካሁንም አንድም ተፈናቃይ ወደ ቀየው አለመመለሱንም ተፈናቃዮቹ ገልጸዋል። እርቅና ሰላም ተፈጥሯል በሚል እየተናፈሰ ያለውም ወሬ ከእውነት የራቀና ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል እየተራገበ ያለ ወሬ ነው ሲሉም ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ትላንት ከቀያችን ያፈናቀሉን፣የገደሉንና ያረዱን ሰዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ ዛሬም እነሱ የእኛ አስመላሽ ሆነው ሲሯሯጡ ማየት ወደቀያችን ...
Read More »