Author Archives: Central

በተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞች ታፍሰው እየታሰሩ ነው

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት በ ኢድ አል ፈጥር እለት የፌደራል ፖሊሶች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎ ሌሊቱንና ዛሬም በርካታ ሙስሊሞች ከቤታቸው እየተወሰዱ ታስረዋል። በአሁኑ ጊዜ በትክክል የታሰረውን ህዝብ ቁጥር ለማወቅ ባይቻልም   በሺዎች እንደሚቆጠር ይገልጻሉ። በዛሬው እለትም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር ተፈተዋል።  ድምጻችን ይሰማ እንደገለጸው ደግሞ በትናንትናው ተቃውሞ አንዲት ...

Read More »

የጦር መሳሪያ የጫነ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አውሮፕላን ወድቆ ተከሰከሰ

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጦር አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ላይ ነው። ሶቭየት ሰራሹ አንቶኖቭ አውሮፕላን መሬት ላይ እንደወደቀ በእሳት ጋይቶ 4 ቱን አብራሪዎች ገድሎአዋቸል። አውሮፕላኑ በአየር ላይ እያለ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከሳምንት በፊት አንድ የመከላከያ ንብረት የሆነ ሄሊኮፕተር ወድቆ መከስከሱ ይታወቃል።

Read More »

በቁጫ ወረዳ ውጥረቱ እንደገና ተባብሶአል

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በወረዳው የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በትናንትናው እለት አልፋ እየተባለ ወደ ሚጠራው ቀበሌ ያመሩ የፖሊስ አባላትና ካድሬዎች ምሽቱን መደብደባቸውን የተመለከተ መረጃ የደረሰው ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ከፍተኛ ቁጥር አላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል። በዛሬው እለት በዙሁ ቀበሌ ያለው ውጥረት የጨመረ ሲሆን፣ በካድሬዎቹ እና በፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም ተይዘው ታስረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ...

Read More »

ወደ ኮሪያ ለስልጠና የተላኩት አብዛኞቹ ወጣቶች ጥገኝነት ጠየቁ

ነሃሴ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኮሪያ ዘማች ቤተሰቦች ተውጣጥው ወደ ደቡብ ኮሪያ ለትምህርት ከተላኩት 59 ኢትዮጵያውያን መካከል 38ቱ ጥገኝነት ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ለ8 ወራት የተሰጣቸውን ስልጠና ሊያጠናቅቁ የቀናት እድሜ ሲቀራቸው ነው ጥገኝነቱን የጠየቁት። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ መበላሸት፣ ወጣቱ በአገሩ የሚሰራበት ሁኔታ ሊመቻች ባለመቻሉ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደተገደዱ ወጣት ሲሳይ ወልደገብረኤል ለኢሳት ገልጿል።

Read More »

በአዲስ አበባና በመላው አገሪቱ ሙስሊሞች 1434ኛውን የኢድ አልፈጥርን በአል ለማክበር በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ሙስሊሞች በፌደራል ፖሊሶች በተወሰደበባቸው እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶዋል።

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢ ከጥቁር አንበሳ እንደገለጸው በዛሬው ድብደባ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ተደብድበዋል፣  እየታፈሱም ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች ተግዘዋል። ኢሳት በራሱ ዘጋቢዎች ባያረጋገጥም፣ ያነጋራቸው ሰዎች አንድ ነፍሰጡርና አንድ ታዳጊ ልጅ መሞታቸውን ጠቁመዋል።  

Read More »

በደሴ የተካሄደው የኢድ ተቃውሞ ላይ ፖሊስ ሕዝቡ ላይ በቀጥታ ጥይት ሲተኩስ አርፍዷል፣ከፍተኛ ድብደባም ፈጽሟል።

ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢው በከፍተኛ አስለቃሽ ጭስ ታፍኖ አርፍዷዋል፡፡በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።  የደሴ ህዝብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። እስካሁን የሞቱትን እና የቆሰሉትን ለማወቅ በፊድራል ፖሊስ ሐይሎች ሆስፒታሎች በመከበቡ ለማወቅ አልተቻለም። በደሴ የሚኖሩ ሙስሊሞች 2 ሰዎች መገደላቸውን ለኢሳት ተናግረዋል በአማራ ክልል በወረባቡ ከተማ ፤ እና መርሳ አካባቢ ክፍተኛ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በሙስሊሙ እና በፖሊሶች መካከል በስምንት ሰዎች ላይ ...

Read More »

የወልድያ ነዋሪዎች አገራችሁንና ባንዲራችሁን አድኑ የሚል ጥሪ ቀረበላቸው

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድምጻችን ይሰማ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባው መንግስት ፣ በካድሬዎቹ አማካኝነት ” የአገርህ ባንዲራ ተደፍራለችና ስልፍ ውጣ እያለ” ትናንት ህዝቡን ሲያስፈርም መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። አንዳንድ ካድሬዎች “ጊዮርጊስ አድዋ ድረስ ሄዶ ተዋግቷል፣  አንተም አገር ሊያጠፉ የመጡትን ተነስትህ ተዋጋ”የሚሉ ቅስቀሳዎችን መዋላቸውንም እነዚሁ እማኞች ተናግረዋል። በእድሜ ለገፉት ደግሞ አሸባሪዎችን ለመቃወም ከወጣችሁ እርዳታ እንሰጣችሁዋላን በማለት ...

Read More »

በአዲስአበባ የኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን ዋጋ ጨመረ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ባልጨመረበት ሁኔታ በአዲስ አበባ ብቻ የኢታኖል ቤንዚን ድብልቅ ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በ0.16 ሳንቲም ከፍ በማለት በሊትር 18 ብር ከ94 ሳንቲም እንዲሸጥ የንግድ ሚኒስቴር መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ እንዳመለከተው የዓለም የነዳጅ ዋጋ የመዋዥቅ ሁኔታ ማሳየቱን ተከትሎ ጭማሪ ለማድረግ መገደዱን ይግለጽ እንጂ በዓለም ገበያ በዚህ ወቅት ነዳጅ ዋጋ የተለየ ጭማሪ አለማሳየቱን የዜና ...

Read More »

ከ192 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት ከሾላ ገበያ ለም ሆቴልን የሚሻገረው አዲስ መንገድ በከፊል ሊፈርስ ነው ተባለ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለቀላል ባቡር ፕሮጀክቱ ግንባታ በሚል ሰበብ ከዚህ ቀደም እንዲፈርሱ ከተደረጉት ከመስቀል አደባባይ ቃሊቲ የሚዘልቀው መንገድ የመሀል ክፍልና ከደሴ ሆቴል ወደ ፑሽኪን አደባባይ ከተዘረጋው አዲስ ከፊል የአስፓልት መንገድ በተጨማሪ ፣ ከ192 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጐበት ከሾላ ገበያ በለም ሆቴል እስከ አንበሳ ጋራዥ የተገነባው መንገድ የተወሰነ ክፍሉ በቅርቡ እንደሚፈርስ ሪፖርተር ዘግቧል። ከ20 ዓመታት በላይ አገልግሎት ...

Read More »

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ የፀረ ሽብር ህጉን የመቃወም እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከእስር ቤት ሆና ባስተላለፈችው መልዕክት ጠየቀች

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሰኔ 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ እየተካሄደ ያለው የፀረ ሽብር ህጉን የመቃወም እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከእስር ቤት ሆና ባስተላለፈችው መልዕክት ጠየቀች፡፡ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ጋዜጠኛ ርዩት አለሙ ገዥው የኢህአዴግ መንግስት የፀረ ሽብር ህጉን ለስልጣኑ ማራዘሚያነት ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ እየተጠቀመበት እንደሚገኝ ገልጻ እየተደረጉ ያሉት የተቃውሞ ሰልፎችና ሌሎችም ሰላማዊ የተቃውሞ ...

Read More »