ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል። ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ግብጽ አሁንም በመስቀለኛ ...
Read More »Author Archives: Central
በቁጫ የተነሳውን ተቃውሞ አስተባብረዋል የተባሉ 32 ሰዎች ከስራ ተባረሩ
ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት የወረዳው ምንጮች እንደገለጹት ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል 2 አቃቢ ህጎች፣ 2 ዳኞች ፣ 1 ፍርድ ቤት ሬስጅስትራርና አንድ ፖሊስ ይገኙበታል። 8 ሰዎች ደግሞ ከስራ ገበታቸው ላይ ለቅቀው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰደዋል። የሚታሰሩ ሰዎች እየተበራከቱ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ 16 ሰዎች ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል። ካለፈው ወር ጀምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉት 40 ሰዎች ደግሞ በዛሬው ...
Read More »በቡሬ ግንባር በሰራዊቱ የሚደፈሩ ሴቶች ቁጥር ጨምሯል
ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሬ ግንባር የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ጊዜያት የአፋር ሴቶችን አስገድደው እንደሚደፍሩ ከስፍራው ደረሰን መረጃ አመለከተ። የሰራዊቱ አባላት ለቅኝት ወይም ለተለያዩ ስራዎች በሚወጡበት ጊዜ ግመል እና ፍየል የሚጠብቁ ሴቶች ሲያገኙ በሀይል ይድፍራሉ። ነሀሴ 3 ቀን 2005 ዓም አንዳባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሀሊማ አህመድ የሱፍ የተባለች እድሜዋ ከ45 እስከ 50 የሚጠጋ ሴት በሰራዊቱ ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚታየው የመብራት መጥፋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ
ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሳምንታት መብራት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች በማስመልከት ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን እንደሚለው በየጊዜው እየሄደ ሳይታሰብ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ሀይል፣ መንግስት ላለፉት 21 ዓመታት ገነባሁት የሚላቸው የሀይል ማመንጫዎች የት እንደደረሱ ጥያቄ የሚፈጥር ነው። ያለምንም መብራት መቋረጥ አንድ ሳምንት መድፈን ብርቅ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ በተለይ የህክምና መስጫ ተቋማት ከመብራት መጥፋት ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ችግር ...
Read More »የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች የፓርቲ ስራ እንደሰሩ መታዘዛቸውን ተቃወሙ
ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንዳንድ ሰራተኞች የኢህአዴግ የ2006 እቅድ መስሪያ ቤቱ ካለበት መደበኛ ስራ ውጪ የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስራ በልዩ ሁኔታ እንዲያስፈፅም ማስገደዱን እየተቃወሙ ነው።አብዛኛዎቹ ሰራተኞች ሚኒስቴሩ በ2006 ዓ.ም ድርጅታዊ ስራን ትኩረት ሰጥቶ እንዲተገብር መድረጉ ሰራተኛው ያለፍላጎቱ የመንግስትንና የድርጅትን ስራ ቀይጦ እንዲሰራ የሚያስገድድ ነው ብለዋል። ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ቅሬታ ያቀረቡት እነዚሁ ...
Read More »የሆስኒ ሙባረክ መፈታት ግብጽን እንደገና ሊከፍላት ይችላል ተባለ
ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሲኤን ኤን፣ ቢቢሲ እና ሌሎችም ታዋቂ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞችን በማነጋገር እንደዘገቡት የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር መፈታት ግብጽን በድጋሜ ከሁለት ሊከፍላት ይችላል። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ሙባረክን ለማውረድ የታገሉ ወጣቶች ምናልባትም ራሳቸውን ከሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር በማቀናጀት በስልጣን ላይ ባለው መንግስት ላይ ሊዘምቱ ይችላል። ይሁን እንጅ የሙርሲን መንግስት ከስልጣን በማውረድ ...
Read More »የፌስቡክ መስራች በታዳጊ አገሮች የሚገኙ 5 ቢሊዮን ሰዎችን ለመድረስ አዲስ እቅድ ነደፈ
ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቱ ዙከርበርግ እንደገለጸው ድርጅቱ ከኤሪክሰን፣ ኖክያ፣ ኦፔራ፣ ኳልኮም እና ሳምሰንግ ጋር በመተባበር በሞባይል መረጃ ላይ የሚጠየቀው ክፍያ እንዲቀነስ ያደርጋል። በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሚሰራ ዙከርበርግ ተናግሯል። አንዳንድ ባለሙያዎች በበኩላቸው የአፍሪካውያን ችግር የኔትወርክ እና የሀይል አቅርቦት ችግር መሆኑን በመጥቀስ በዚህ በኩል ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ይመክራሉ።
Read More »በዛሬው ዕለት ታስቦ ከዋለው የመለስ ሙት ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ አብዛኛው አገልግሎት ሰጪ የመንግስት መ/ቤቶች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ዝግ ሆነው ዋሉ፡፡
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዓሉን አስመልክቶም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶአል፡፡ የአቶ መለስ ሙት ዓመት ጉለሌ በሚገኘው የዕጽዋት ማዕከል የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣የጎረቤት አገር መሪዎች፣ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብርዋል፡፡ በተለይ የመንግስት ሠራተኞች በግዳጅ በመስቀል አደባባይ የሻማ ማብራት ስነስርዓት እንዲያካሂዱ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም በርካታ ሠራተኞች ዕለቱን እንደዕረፍት በመቁጠር ...
Read More »ወ/ት ሐዲያ ሙሀመድ ከሳምንታት የእስር ቤት ስቃይ በሁዋላ ተፈታች
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራር የሆነቸው ወ/ት አዲያ አህመድ ከሀምሌ 22 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እስር ቤት ውስጥ ከደረሰባት በሁዋላ በዛሬው እለት በዋስ ተፈታለች። ወ/ት ሐዲያ እንዳለችው መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ያዋሉዋት አንድነት ፓርቲ ሀምሌ 28 በሶዶ ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ህዝባዊ ስብሰባ በተመለከተ የቅስቀሳ ወረቀቶችን መበተኑዋን ተከትሎ ነው። ...
Read More »የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጠየቀ።
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ እንጠይቃለን” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ፓርቲያችን አንድነት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚታገልላቸውና ገዥው ፓርቲ ከወረቀት አልፎ ያልተገበራቸው ሀገራዊ ቁምነገሮች ውስጥ ዜጎች ሳይሸማቀቁ በነፃነት ሃሳባቸውንና አመለካከታቸውን የመግለፅ፣ በነጻነት የመደራጀት፣ በገዛ ሀገራቸው በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ በፈለጉበት አከባቢ የመኖር፣ የመደገፍ፣ የመቃወም እና ስለመብታቸው ሳይሸማቀቁ የመጠየቅ መብቶች እንደሚገኙበት አመልክቷል። ...
Read More »