ሆስኒ ሙባረክ ተፈቱ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል።

ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል።

ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ግብጽ አሁንም በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ብዙ የፖለቲከኛ ተንታኞች ይናገራሉ።