የፌስቡክ መስራች በታዳጊ አገሮች የሚገኙ 5 ቢሊዮን ሰዎችን ለመድረስ አዲስ እቅድ ነደፈ

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቱ ዙከርበርግ እንደገለጸው ድርጅቱ ከኤሪክሰን፣ ኖክያ፣ ኦፔራ፣ ኳልኮም እና ሳምሰንግ ጋር በመተባበር በሞባይል መረጃ ላይ የሚጠየቀው ክፍያ እንዲቀነስ ያደርጋል።

በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሚሰራ ዙከርበርግ ተናግሯል።

አንዳንድ ባለሙያዎች በበኩላቸው የአፍሪካውያን ችግር የኔትወርክ እና የሀይል አቅርቦት ችግር መሆኑን በመጥቀስ በዚህ በኩል ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ይመክራሉ።